Thursday, 9 October 2014

'ባንዲራችንን አትድፈሩት እኛ እንድፈረው''፤
ከትላንት በስትያ እኛ ሀገር ሰላም ብለን ትምህርታችን ላይ አንገታችንን ደፍተን በነበረበት ወቅት በዋሽንግተን ዲሲ ከሁለት ወገን በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን ተፋጠው ነበር።
በዚህ ወገን ያሉት ኢትዮጵያውያን ባለፈው ጊዜ ከኛ በላይ ተኳሽ ላሳር ያለውን የደደቢት ጓድ አሜሪካ ''ኪቻ'' ብላ ስላባረረችው ገለታ ለማለት የተገኙ ሲሆን፤
በሰለሞን ተካ የተመራው የመንግስት ከንፈር ወዳጅ ሰልፈኞች ደግሞ (በቅንፍም፤ እነዚህን ሰልፈኞች ከምንላቸው ሰይፈኞች ብንላቸው ይሻላል መሰል) እና እነርሱ በሌላ በኩል ''ወዲ ወይኒ እንኳንም ተኮሰ'' እንደውም የጥይት ጩህት ናፍቆን ነበር ብለው ሊመሰክሩ ሰልፍ ወጥተው ነበር።
ከዚህ በተጨማሪ በሰልፉ ላይ የተገኙት እንዚህ የኢህአዴግ ብልግና ደጋፊዎች ''ባንዲራችንን አትድፈሩት እኛው እንደፍረዋለን'' ሲሉ ልክ አቶ መለስ ዜናዊ የደፈሩት አይነት አደፋፈር ባንዲራው ላይ ፈጽመዋል።
እኛም በሩቁ ነገሩን የተመለከትን ሰዎች ባንዲራ የምትገለብጪ ወዮልሽ ....ትገለበጫለሽ... ወዮልሽ!!! ስንል ለትዕቢተኞቹ ትንቢት ተናገረናል!

No comments:

Post a Comment