Monday, 27 October 2014


ዓረና በዓዲግራት....!
===========
ከአንዶም ገብረስላሴ
...
ዓረና ትግራይ ባለፈው ዓመት በዓዲግራት ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበርና የህወሓት ፋሺሽታዊ ተግባር በጠራራ ፀሃይ የተጋለጠበት ኣጋጣሚ መፍጠሩ ያሚታወስ ነው።
በህዝባዊ ስብሰባው እኔ ‪#‎Amdom‬,‪#‎abraha‬ ፣ato asgede ና ሌሎች ኣባሎቻችን በፖሊሶች ፊት ተደብድበን ህዝቡ በህወሓት መሪዎች የነበረችው ትንሽ ተስፋ ጨርሶ ያጣበት ኣጋጣሚ ነበር።
ዓረና ከዛ ፋሽሽታዊ የህወሓት ተግባር በሗላ በዓዲግራት ከተማ ትልቅ የሚባል ህዝባዊ ማነሳሳት ኣላካሄደም ነበር።
ዛሬ ሰኞ 17 / 02 / 2007 ዓ/ ም የዓረና ኣባላት የፓርቲው ኣማራጭ ፖሊሲዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች የያዘ በራሪ ፅሁፍ ሲያድል ወለዋል።
በዛሬው ቀን የዓጋመና የዓዲግራት ህዝብ በከተማው የተፈፀመው የህወሓት ፋሽሽታዊ ተግባር ክፉኛ እንዳሳፈረውና እንዳናደደው በራሪው ፅሁፍ ስንሰጠው ይሰጠን የነበረ ኣስተያየት ኣመላካች ነበር።
ኣንድ ምሳሌ ልጥቀስላቹ ኣቶ ፀሃዬ የተባለ የድሮ ታጋይና የሰለሞን ሆቴል ባለበት የዓረና ኣባላት በሆቴሉ ኣልጋ ይዘው ኣደሩ።
ጥዋት በራሪ ፅሁፋችን ለማደል ኣዲሱ የዓረና ብርቱኳናማ ቲሸርት ለብሰን ስንንቀሳቀስ ዝምብሎ ያየን ነበር። ትንሽ ረፈድ ሲል ከህወሓት ካድሬዎች ስልክ ተደዉሎ የተለያዩ ዛቻዎች ወረዱበት።
በካድሬዎቹ ዛቻ ክፉኛ የደነገጠው ፀሃየ በሆቴሉ ሻይ ኣዝዞ ለነበረው የዓረና ኣባል በማዋከብና የስድብ ውርድብኝ በማዝነብ ከሆቴሉ ኣስወጣው። ከዚህ ኣልፎም "..ንዓረና ቦታ ኣይንህቦን(ለዓረና ቦታ ኣንሰጠውም)፣ ቃልስና ነዊሕን መሪርን እዩ ዓወትና ናይ ግድን እዩ ( ትግላችን ረዥምና መራራ ነው፣ ድላችን የግድ ነው።.." የሚል በሆቴሉ ደጃፍ ለጠፈ።
ይህ ሁሉ ይከታተሉ የነበሩ ወጣቶች ፀሃየን ክፉኛ በመውቀስ "...እኛ ኣማራጭ እንፈልጋለን፣ እነዚህ ሰዎች የራሳችን ወገኖች ናቸው፣ ከየትም ኣልመጡም የት እንዲሄዱ ነው የምትፈልገው? ባለፈው ዓመት የሰራቹት ኣፀያፊ ተግባር ኣሁንም ለመድገም መሞከራቹ ነው?.." ወዘተ የሚሉ ምክሮች በመለገስና ኣቋሙ እንዲያስተካክል ጥረት ኣድርገዋል።
የህዝቡ ጥያቄ "...ዓረና በዓዲግራት ህዝባዊ ስብሰባ እንዲያካሂድ..." የሚል ነበር። ዓረናም ኣማራጭ ሃሳቡ ለዓጋመና ዓዲግራት ህዝብ በማቅረብ ጠቃሚ የውይይት መድረክ እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብተንላቸው ተመልሰናል።
በዓዲግራት ከተማ በራሪው ፅሁፍ እያደሉ ከነበሩ 3 ቡድኖች የኣንዱ ክንፍ በምስሉ የሚታዩት ናቸው።
በዓዲሱ ዓመት የዓረና በራሪ ፅሁፍ በኣላማጣና ሌሎች 4 የራያ ዓዘቦ ቀበሌዎች፣ ውቕሮ፣ ዓብይ ዓዲ፣ መቐለ፣ ኲሓ፣ ኣይናለም ዛሬም በዓዲግራት ከተሞች ለህዝቡ ኣዳርሷል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው...!
IT IS SO...!

No comments:

Post a Comment