Wednesday, 8 October 2014

በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተኩስ የከፈቱት ዲፕሎማት ላይ የእስር ማዘዣ ወጣ
ባለፈው ሰኞለት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለተቃውሞና ለአቤቱታ የተሰባሰቡ ሰዎች ላይ ሽጉጥ በመምዘዝ የተኮሰው የኢምባሲ የጥበቃና ደህንነት ክፍል ሰራተኛ፤ የዩናይትድ ስቴይትስ አቃቢ ህግ ቢሮ እስከ 30 ዓመት በሚያስቀጣ ወንጀል ክስ ከፍርድ ቤት እስር ማዘዥ እንደተሰጠው አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥበቃና ደህንነት አታሼ የ46 ዓመቱ አቶ ሶሎሞን ታደሰ ገ/ስላሴ የተከሰሱበትና የእስር ማዘዣ የወጡበት ህግ “ለመግደል በማሰብ ጥቃት ማድረስ” የሚል ነው። የወንጀል ደረጃውም እስከ 30ዓመት የሚደርስ ከፍተኛ ቅጣት የሚጣልበት እንደሆነ በዩናይትድ ስቴይትስ አቃቢ ህግ ቢሮ የዋሽንግተን ዲሲ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ዊሊያም ሚለር ለቪኦኤ በጽሁፍ ገልጸዋል። ሰኞ መስከረም 19 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለተቃውሞ ሰልፍና ለአቤቱታ የወጡ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ኢምባሲው ቅጥር ግቢ ከገቡ በኋላ በተፈጠረ ሁኔታ አቶ ሰሎሞን ተኩስ ከፍቷል። በዚህ የወንጀል ምርመራ፤ የዝግጅት ክፍላችን ከዚህ ቀደም ለፍትህ ምንስቴርና ለውጭ ጉዳይ ምንስቴር ባቀረበው ጥያቄ፤ የምርመራው አትኩሮት በተኳሹ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው? ለሚለው ጥያቄ የዲሲ አቃቢ ህግ ቢሮ ሲመልስ ዝርዝሩ የሲክሬት ሰርቪስ ቢሆንም “በዚህ ክስተት ላይ ሌላ ክስ የቀረበበት ሰው የለም” ብለዋል።
http://amharic.voanews.com/

No comments:

Post a Comment