ስለ ተመስገን ደሳለኝ
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
(ቀደም ብዬ መፃፍ የነበረብኝ ሀሳብ)...
ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት የተመስገንን መታሰር ስሰማ አዘንኩ ። "በምንና እንዴት ታሰረ? መታሰሩ አግባብ ነው? " የሚለውን አላነሳም ። ምክንያቱም ከግምት የተሻለ እውቀት የለኝም ። አሁንም በቀጠሮው ቀን ምን እንደሚል አላውቅም ። ይህ ሀሳቤም አሁን ተመስገን ካለበት ሁኔታ ጋር አይገናኝም ። ይሁንና ቀደም ሲል መፃፍ የነበረብኝን ሀሳብ ላንሳ ።
ተመስገን ፋክት መጽሔት ላይ እንድጽፍ ሲያነጋግረኝና ከዚያ በፊት ለእሱ የነበረኝ ግምት የተለያየ ነው ። አራት ኪሎ አግኝቼ ያናገርኩትና ፋክት እስክትቆም ያየሁት ተመስገን ለእኔ እንዲህ ነው ።
የሚጮህ ጽሁፍ የሚጽፈው ተመስገን በጣም ጸጥተኛ ነው ። ደፋሩን ጸሀፊ የትህትና ፍርሀት ያለበት ሆኖ ነው ያገኘሁት ። ለስላሳነቱ የውስጥ ባህሪው ነው ። ከሁሉም በላይ በግል እንደራሴም ይሁን እንደ ሙያውን ወዳድ ጋዜጠኛ ፍጹም ነጻነት የሰጠኝ ከሁሉም በላይ ተመስገን ደሳለኝ ነው ። አብረን ለመስራት ተስማምተን ስለጽሁፍ ይዘት ስናወራ "ምን አይነት ይዘት ያለው ጽሁፍ እንድጽፍ ነው የምትፈልገው?" ስለው የሰጠኝ መልስ መቼም የማልረሳውና በአንዱ የመጽሔቱ እትም ላይ የጻፍኩት ነው ። " እንዲህ ጻፍ አልልህም ። የፈለከውን ጻፍ ። ኢህአዴግ በአለም ላይ ታይቶ የማይታው ዲሞክራሲ አምጥቷል ብለህ ካመንክ የመጻፍ መብት አለህ ። አንተ ስም ስላለህ ድጋፉንም ተቃውሞውንም የምትቀበለው ራስህ ነህ " አለኝ ። ይህ ለአንድ ጋዜጠኛ ፍፁማዊ ነጻነት ነው ። ተመስገን ደሳለኝ ከጥሩ የብር ክፍያው ጎን ይህን ከፍሎኛል ። የትም ብሄድ ይህን ነጻነት አላገኘውም ። በፋክት መጽሔት ቆይታዬም ከቃለመጠይቅ ጀምሮ እስከ መጣጥፎች በዚህ ነጻነት ነው የሰራሁት ። አንድም ቀን በዚህ ርዕስ ላይ ብትፅፍ ያላለኝና በሀሳቤ ጣልቃ ያልገባ ሰው ይህ ሰው ነው ። መጻፍ ሲገባኝ ያልጻፍኩት ወይም ያልተገባ ሀሳብ ጽፌ ከተገኘሁ በራሴ ግፊትና ሀሳብ ነው ። ለጻፍኩት ሁሉ ሀላፊነቱን የምወስደው እኔ ብቻ ነኝ ። ማንም ሌላ የለም ። ይህን የጋዜጠኛ ነጻነት ሌላ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አላምንም ። በዚህ ተመስገንን ሁሌም አከብረዋለሁ ። እውነት ለመናገር መቼም ወደ ፕሬስ ስራ ቢመለስ አብሬው ለመስራት የማላመነታው አንድ ሰው ይህ ዛሬ ታሰረ የተባለው ተመስገን ደሳለኝ ነው ። ለእኔ ለጋዜጠኛው ከመጽሔቱ ሰውየው ተመስገን ይበልጥብኛል ። እጄን ይዞ ሊያጽፈኝ የማይሞክር የነጻነት አለቃዬ ነው ። አክባሪዬም ነው ተመስገን ። ለእኔ ግን ከማክበሩም በላይ ነጻነቱ ይበልጥብኛል ። አሁንም ልድገመውና ተመስገን ነፃ ወጥቶ ወደ ፕሬስ ስራ ቢመለስ እስከ ነጻ ባለ ክፍያ አብሬው ለመስራት የምፈልገው ሰው ነው ። ነጻነት በራሱ ክፍያ ነው ። ተመስገን ደግሞ ይህን እንደሚከፍለኝ አምናለሁ ።
አምላክ በድጋሚ በስራ እንደሚያገናኘን ፀሎቴ ነው ።

No comments:
Post a Comment