Saturday, 8 March 2014

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሴቶች ክፍል በዛሬው እለት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8, 2014 ምክንያት በማድረግ ዝግጅቱን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።

ዝግጅቱ ከቀኑ 11፡00በዲሞክራሲያዊ ለውጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሊቀመንበር አጭር ንግግር አድርገዋል። ሴቶቹም በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች እህቶቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የሰብአዊ መብት እረገጣ በማጋለጥና በመቃወም ገንቢ ውይይት ያደረጉ ሲሆን የድርጅቱ የሴቶች ክፍል ሰብሳቢ የመግቢያ ንግግር እና ጣይቱ ቡጡልን የሚያስታውስ ግጥም አቅርበዋል በመቀጠል ምክትል ሰብሳቢዋ እንዲሁ አድዋን በተመለከት አጠር ያለ ግጥም እና አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ አጭር ገለፃ አቅርበዋል በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ግጥሞች እና ንግግሮች እንዲሁም አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ጭውውቶች ፤ የጥያቄና መልስ ጊዜም ነበር። በተጨማሪ የምሳና እና ሻይ ቡና ግብዣ አድርገዋል በዚህ ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በእንግድነት ታዳሚያችን ነበረች።

መቀጠል ከ14፡00 ጀምሮ አጠቃላይ ኖርዌጅያን እና በኖርዌ የሚኖሩ ሴቶች በሙሉ በአሉን በጋራ በሚያከብሩበት ቦታ በመሄድ በተለያዩ የአረብ ሃገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ ህይወታቸው ላለፈውና ለሚሰቃዩ ሴቶች እህቶቻችንን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ እና የሻማ ማብራት ስነስርአት የተከናወነ ሲሆን ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ በዝግጅቱ ላይ በእንግድነት ተገኝተው ሴቶችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል የተለያዩ ሴቶች እህቶቻችንም በቦታው በመገኘት ንግግርና አስተማሪ ግጥሞችን አሰምተዋል። ኢትዮጵያውያን ሴቶቹ በሃገራችን በሴቶች እህቶች ላይ የሚደርሰውን ያላግባብ እንግልት እና እስር እንዲቆም በተለይ ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ከእስር እንድትለቀቅ እና በቂ ህክመና የማግኘት መብቷ እንዲከበር የርዮትን ምስልና በተለያዩ አረብ ሃገራት እድሜያቸው ለስራ ያልደረሱ ሴቶችን ለሽያጭ ማቅረቡን የኢትዮጵያ ገዢው መንግስት እንዲያቆም እንዲሁም በየአረብ ሃገራቱ በግፍ ህይወታቸው ላለፈው ዜጎቻችን እና እየተሰቃዩ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተጠያቂው የወያኔ መንግስት መሆኑን የሚያጋልጡ መፈክሮችምን በመያዝ በኢዮጵያ ውስጥ በሴቶች ላይ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለአለም በማጋለጥ የመጨረሻውን የእግር ጉዞ ፕሮግራም በመካፈል ዝግጅቱ በ17፡00 ተጠናቋል።

No comments:

Post a Comment