የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በዋስ ተፈቱ
10 የፓርቲው ሴት እና ወንድ አመራሮች ያለፉትን 11 ቀናት በእስር ቤት ካሳለፉ በሁዋላ ፖሊስ እያንዳንዳቸውን በ3 ሺ ብር ዋስ ለቋቸዋል። ምንም እንኳ አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ የለኝም ቢልም፣ ፖሊስ እስረኞችን በነጻ ከመልቀቅ በዋስ መልቀቅን መርጧል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃ እንደሚሉት እስረኞቹ በነጻ ካልሆነ በዋስ አንፈታም የሚል አቋም ቢይዙም፣ የፍትህ ስርአቱን መበላሸት እስካሳዩ ድረስ ትግሉን ለመቀጠል ሲባል በዋስ እንዲፈቱ ለማግባባት ተሞክሮ መፈታታቸውን ገልጸዋል


No comments:
Post a Comment