Wednesday, 28 October 2015

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡



ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡:
እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡ በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ፍርድ ቤቱ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም አቶ አንዳርጋቸው እሱ ጋር እንደሌሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ መግለፁ ይታወሳል፡፡
ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ 
ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ከአቶ ምንዳዬ ጥላሁን በተጨማሪ 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲመሰክሩለት በመፈለጉ፤ እና ፍርድ ቤቱም አቶ አንዳርጋቸው ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲመቸው ተከሳሾቹ እንዲጠቁሙት በገለፀው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ተቋማት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
ሁለቱ ተከሳሾች ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ለፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በፃፉት ደብዳቤ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንክ ኮርፖሬት መግለጫ መስጠቱን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2007 ዓ.ም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዝ፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያ መንግስት ፍርዱን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን አስታውሰዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ዜግነታቸው እንግሊዛዊ የሆሉትን አቶ አንዳጋቸው ጉዳይ ላይ ክትትል እንደሚያደርግ በደብዳቤው አስታወስዋል፡፡
በመሆኑም ከእነዚህ ሶስት አካላት በላይ አንዳርጋቸው ፅጌ ስላሉበት ቦታ የሚያውቅ ስለሌለ ለሶስቱም አካላት አቶ አንዳርጋቸው የት እንዳሉ እንዲገልፁና አቶ አንዳርጋቸውም ምስክር እንዲሆኑላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

Tuesday, 20 October 2015

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 ሽልማት አሸናፊ ሆነ



ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 ሽልማት አሸናፊ ሆነ
18 የእስር አመታት በግፍ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 አሸናፊ ሆነ መመረጡን ድርጅቱ አስታውቋል።
ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የጽናት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ቤት አሳልፏል። የእስክንድር ስራዎቹ ድንበር እና ባህል ተሻጋሪ ናቸው በማለት ያወደሰው ድርጅቱ፣ 5 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ሽልማት በ36ኛው የአለማቀፍ ጻሃፊዎች ቀን ላይ ይበረከትለታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ቡድን የእስክንድርን መታሰር አለማቀፍ ህግን የጣሰ መሆኑን በመጥቀስ እንዲፈታ መጠየቁን መግለጫው አውስቷል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ከሶስት አመታት በፊት የፔን ባርባራ ጎልድ ስሚዝ ፍሪደም ቲ ራይት ፣ አምና ደግሞ ጎልደን ፔን አዋርድ ኦፍ ፍሪደም አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል። በምርጫ 97 ወቅት እስክንድር ከቅንጅት መሪዎች ጋር አብሮ ታስሮ የተለቀቀ ሲሆን፣ ቀድም ብሎም ከስራው ጋር በተያያዘ ከ5 ጊዜ በላይ ታስሯል። በስልጣን ላይ ያለው ገዢ ፓርቲ የጋዜጣ ፈቃድ የከለከለው እስክንድር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የስርዓት ለውጥ አይቀሬ መሆኑን ማስረጃዎችንና ምልከታውን ተንተርሶ የተለያዩ ጽሁፎችን በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ጽፏል።

የተመስገን ደሣለኝ ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ

የተመስገን ደሣለኝ ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሣለኝ ተመስገንን ረቡዕ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ዝዋይ ሄዶ መጎብኘቱንና፣ ወንድሙ የግራ ጆሮው ሙሉ በሙሉ እንደማይሰማ፣ ጀርባው ላይ ያለው እብጠት እየባሰበት መሆኑን በጀርባው መተኛትም እንደማይችል አስረድቷል፡፡ ተመስገን ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ሕክምና እንደማያገኝና ቤተሰቡም ለማሳከም ቢጠይቅም ፍቃድ መነፈጉን፣ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ይዘው ሄደው “በማረሚያ ቤቱ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም” የሚል መልስ ማግኘታቸውን ታሪኩ ለቪኦኤ ገልጿል፡፡ ተመስገን ያዘጋጃቸው ከነበሩት መፅሔቶች በአንዱ ላይ አምደኛ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምም ከጥቂት ወራት በፊት ከፕሮፌሰር መስፍንና ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው እዚያው ዝዋይ ድረስ ሄደው እንዳዩትና በወቅቱ የግራ ጆሮው ይደማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ የተመስገን ደሣለኝ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንንም የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ዝዋይ ሄደው ያዩት መሆናቸውንና በቦታው ርቀት ምክንያት ከዚያ በኋላ በአካል እንዳላገኙት ገልፀው ከቤተሰቦቹ ግን አሁን ያለበትን ሁኔታ እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት፣ መንግሥቱ ባወጣቸው ደንቦችና በዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችም መሠረት ማንም እሥረኛ ጤንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መያዝ እንደሚገባው፤ አስፈላጊ በሆነ ጊዜም ሕክምና የማግኘት መብት እንዳለው፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርም ሆነ የወህኒ ቤቱ ሃኪም ታራሚው ሕክምና ማግኘቱን የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤቱ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ ተመስገን አዲስ አበባ ድረስ ተወስዶ ሕክምና ማግኘቱን፤ በማረሚያ ቤቱ ውስጥም እየታከመ መሆኑን፣ ጤናማና እየተንቀሣቀሰ ያለ መሆኑን ገልፀው ጤንነቱ ታውኳል፤ ሕክምና ማግኘት አልቻለም የተባለው ሃሰት መሆኑን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡ ጠበቃው አቶ አምሃ ግን አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ አለመታከሙን፣ ሄዶ ቢሆን ኖሮ እርሣቸው ያውቁ እንደነበር ተናግረዋ የማረሚያ ቤቱን የሥራ ኃላፊ መግለጫ አስተባብለዋል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

Sunday, 18 October 2015

የአብዱ ኪያር “አልተለያየንም” ዘፈን በመንግስት ሚድያዎች እንዳይተላለፍ ታገደ

Sunday, October 18th, 2015 | ዘ-ሐበሻ
የአብዱ ኪያር “አልተለያየንም” ዘፈን በመንግስት ሚድያዎች እንዳይተላለፍ ታገደ
(ዘ-ሐበሻ) ድምፃዊ አብዱ ኪያር “አልተለያየንም” በሚል በአዲሱ የ”ጥቁር አንበሳ” ሲዲው ላይ ያቀረበው ዘፈን በመንግስታዊ ሚዲያዎች ላይ እንዳይተላለፍ ዕግድ መተላለፉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስታወቁ::
“በካርታ ብንለያየም – ኢትዮጵያም ኤርትራም አንድ ናቸው”… “አዲሱ ማንነቴን መቀበል አቃተኝ”… “በወላይታ ሙዚቃ ይጨፈራል በአስመራ”… የሚሉ መል ዕክቶች ያሉት በአንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይኸው የአብዱ ኪያር ዘፈን በኢትዮጵያ ሁሉም ከተሞች ባሉ ሙዚቃ ቤቶች; በምሽት ክለቦችና መዝናኛ ቦታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::...
መንግስታዊ ሚድያዎች እንዳያሰሙት የተከለከለው ይኸው “አልተለያየንም” የሚለውን ዘፈኑን ዘ-ሐበሻ እዚህ ጋብዛችኋለች:: ያድምጡት:: ለወዳጅ ዘመድዎም ያካፍሉት::





ድል ለአርበኞች ግቦት7! ሞት ለዘረኞች!

በ17/10/15 በሚኖሶታ ከተማ ለአርበኞች ግቦት7 የተደረገው የገዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማረና በደመቀ፣ኢትዮጲያዊ ጨዋነትና ቁርጠኝነት የታየበት ነው በድጋሚ ሚነሶታዎች ኮርተንባችኃል በርቱ፣ ለወገን ኩራት ፣ለጠላት ራስምታት ሆናችኃል ኢትዮጲያዊነት በተግባር ታይቷል። የፑስት ሮድ ታክሲ ሹፊሮች ከነፃነት ታጋዮች ከታጋይ ትግስት፣ከታጋይ ዘመነ ካሴና ከሊሎችም ታጋዮች ጉን መሰለፋችሁን በተግባር አሳይታችኃል በርቱ በርቱ።ሴቶች እህቶቼ የወገን ግፍና ሰቆቃ እረፍት እደነሳችሁና ግፍና ግፈኞችን ለመታገል ያደረጋችሁት ቁርጠኝነትና ያስመዘገባችሁት ስኬት የጣይቱ ልጆች ያስብላችኃል በርቱ በርቱ፣ አባቶችና እናቶችም በሳያችሁት አኩሪ ተግባር የብዙ ወጣቶችን ልብ አንፃችኃል በርቱ በርቱ።ዲያቆናት፣ቄሱች፣ሼህሁች በዝግጁቱ ላይ ተገኝታችሁ ለሐይማኖታችሁናለአገራችሁ በፅናት ...መቆማችሁን አስመስክራችኃል በርቱ በርቱ።አበሳው ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየው/ዘሀበሻ/ለወገንህ መረጃን ማድረስ ብቻ ሳይሁን ግዜህን ፣ጉልበትህን፣ገንዘብህ ለኢትዩጲያ ነፃነት ሁሉንም ነገርህን ከነቤተሰብህ መስጠትህን በቃል ብቻ ሳይሁን በተግባር ማሳየትህ ጋዜጠኛ ብቻ ሳትሆን አርበኛም ጭምር መሆንህን በማየቴ እስርቤት ያሉት የሙያ ጓደኞችህ በመንፈስ ሀሴትንና ደስታን እደሚያደርጉ ምንም ጥርጥር የለኝም በርታ አባሳዩ የኢትዩጲያ አምላክ ብድራቱን ይክፈልህ !በአጠቃላይ በሚኖሶታ አኩሪ ታሪክ ተመዝግቧል። ኢትዩጲያ በቆራጥ ልጆቹ ሀይማኖትና ባህሏ፣ተሪክና ክብሯ ነፃነቷ ተጠብቆ ለዘላለም ይኖራል።ድል ለአርበኞች ግቦት7! ሞት ለዘረኞች!

Saturday, 17 October 2015

#Obang Metho#
My Fellow Ethiopians: We, the freedom lovers, justice seekers and unity defenders have just won the Battle but not the Victory.
It is joyful to see our heroes, the Zone 9 bloggers hugging their family and friends. We can't wait to see all the others heroes, the tens of thousands Ethiopian political prisoners do the same to their family too soon.
We, the people of Ethiopia are rejoicing, wherever we are—in or outside of Ethiopia, at the release of the four Ethiopian bloggers, who were arrested in 2014 after writing posts critical of the ethnic apartheid regime of the TPLF/EPRDF, have been acquitted by the country’s high court yesterday of terrorism charges.
After they (Zone 9 bloggers) spent 539 days in prison and 39 court hearings they were acquitted and set free but we should never forget that freedom of speech is still on trial in Ethiopia. Their released should reminded us that justice and freedom will always prevail, no matter whether it is done today or not.
October 16, 2015, will forever mark a great day that will go down in history books for all freedom loving Ethiopians, but please remember, as we are celebrating a beginning victory, it is only one battle in a war for justice, freedom, peace and liberty.
Until tens of thousands of other Ethiopian political prisoners who continue to languish in the prisons of Afar; Amhara; Benishangul/Gumuz; Dire Dawa; Gambella; Harari; Oromiya; Somali region; Southern Nations, Nationalities, and People's; Addis Ababa; and Tigray are free, we are not free as a people and our victory cannot be claimed.
Until all our Ethiopian institutions, now being used against us instruments of repression, are released from the tight controls of the ethnic apartheid regime, we can take hope and encouragement from this unexpected achievement, but it is only the beginning. Until Ethiopians can live, breathe and move freely about within our society—without fear of reprisals for simply thinking for ourselves—we are not free!
So right now, let us pause to thanks the family of the Zone 9 Bloggers and their supporters who never lost hope and never give up fighting until justice prevails. Th victory of releasing the Zone 9 Bloggers is about being consistent and a true freedom fighters and if we are patient we can accomplished more than we can imagine.
I also want to thank our heroes, the Zone 9 Bloggers released and for those still stuck in prisons and detention centres throughout Ethiopia for being examples of courage for Ethiopia. It is you who have built a foundation for freedom that will fan the flames of fire within our hearts. Many of you are yet unknown by name to many of us, yet you have inspired all of us by your examples.
It is brave Ethiopian men and women from every ethnic and religious groups like this of whom the rest of us are so proud. As people of principle, true to themselves and to what is right, they have been targeted as enemies of the ruling ethnic apartheid regime. Their examples create serious problems to the ethnic apartheid regime, while encouraging and motivating us in the Diaspora to carry on our advocacy work in the United States, Canada, Europe, Africa, the Middle East and Australia.
Yet, we remember, the real heroes of the struggle are these people like the Zone 9 Bloggers and others standing up for truth, justice, equality, virtue, love and freedom that are living in all the corners of Ethiopia.
We must also give credit to those Ethiopians in the Diaspora who through their persistence from the beginning, have worked so diligently on making those in the international community aware of this crisis, even to the point where western governments have responded with action.
My fellows’ Ethiopian brothers, and sisters do not focus on the pain and ethnic hatred inflicted on each other by the narrow-minded, ethnocentric politicians and their sick ideology of Nations, Nationalities and Peoples that denied the Humanity of others and history of Ethiopia.
We need unity and national reconciliation more than ever before. Three things are holding freedom from coming to Ethiopia. As I have said it before these three things are: Lack of our UNITY of propose, the GUNS of the TPLF/EPRDF and the support of ethnic apartheid regime by the USA or WESTERN COUNTRIES.
The guns and the support of ethnic apartheid regime from the players like the US, Canada and Europe, will dissolve if we have a truly unified movement of the PEOPLE based on respect, tolerance and inclusion.
May God help us!

Tuesday, 13 October 2015

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አያያዙ አስከፊ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ገለጹ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አያያዙ አስከፊ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ገለጹ

የ18 ዓመት እስር ተበይኖበት ከ4 አመታት በፊት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የወረደው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አያያዝ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ 

‹‹እስክንድር ነጋ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ምንም አይነት መጽሐፍ እንዳያነብ ተከልክሏል፡፡ ከባለቤቱ ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል እናትና ከአንድ የቅርብ ዘመዱ ውጭ ማንም እንዳይጠይቀው ታግዷል፡፡ እስክንድር ከአንድ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከአምስት ሰዎች ጋር ብቻ ነው የታሰረው፡፡ ማንም ጋር አይገናኝም፡፡ መቀመጫ ወንበሩ ተወስዶበት የቆሻሻና ውሃ ማጠራቀሚያ የነበረ ባልዲን ባፉ ደፍቶ ጨርቅ ደልድሎ ነው ለመቀመጫነት የሚጠቀመው›› ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የእስክንድር ነጋ የቅርብ ሰው ለቀለም ቀንድ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብኣዊ መብታቸው የመጠበቅ መብት እንዳላቸውና ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሀይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሀኪማቸው፣ ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡

(የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቅጽ 3 ቁጥር 12)

Sunday, 11 October 2015

Human rights award for Helawit, daughter of Andargachew Tsige

Helawit at the award ceremony with Shami Chakra­barti, director of Liberty
Helawit Hailemariam, 16, from Clerkenwell, was awarded the Christine Jackson Young Person Award by the charity Liberty in recognition of her ongoing battle for the release of her father, the Ethiopian-born democracy activist Andargachew Tsege, 60.
Liberty honoured a number of activists, young campaigners, artists and lawyers who champion “fundamental freedoms” at its annual Human Rights Awards last month.
“We need help for our campaign to get my father back,” Helawit, who is studying for her A-levels at City and Islington College in Angel, said. “I really did not expect to to win the award. It defin­itely helps our campaign, it makes my father’s story more real and it validates it.”

ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያዊነት
ኢትዮጵያዊነት ብዙ የተለያዩ ኅብረተሰቦች የተዋኅዱበት አካል ክፍል መሆን ነው። ኢትዮጵያዊነት ከጎሠኝኛት በላይና ውጭ የሆነ አጠቃላይ ማንነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት የዚች ውጥንቅጥ መሬት ባለቤትነት ነው፣ ኢትዮጵያዊነት የደጋው ብርድና የቆላው ሙቀት የሚገናኙበት፣ የደጋው ዝናም ከቆላው ወንዝ ጋር የተዛመደበት ኃይል ነው።
...
ኢትዮጵያዊነት ለሙሴ፣ ለክርስቶስና ለመሐመድ የሚጨሰው ዕጣን በእርገት መጥቶ የሚደባለቅበት እምነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት በቄጤማ ጉዝጓዝ ላይ የሚታየው መተሳሰብና መፈቃቀር ነው።
ኢትዮጵያዊነት የአስተዋይነት፣የሚዛናዊነት የጨዋነት ባሕርይ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ረዢምና ተጽፎ ያላለቀ ታሪክ ነው፤ ብዙ ሰዎችም የተሰዉለት ስሜት ነው።
ኢትዮጵያዊነት ስቃይና መከራ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብርም ነው።
ኢትዮጵያዊነት ጭቆናና ጥቃት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት አሻፈረኝና እምቢ ባይነትም ነው።
የኢትዮጵያዊነት ዓላማ ያለችውንና የኖረችውን ኢትዮጵያን እንደገና ለመፍጠር አይደለም። የኢትዮጵያ ዓላማ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ የሚስማማ እድገታቸውንም የሚያፋጥንና፣ኅብረታቸውን የሚያጠነክር ሥርዓትን መፍጠር ነው። የኢትዮጵያዊነት ችግር ኢትዮጵያ አይደለችም፣ችግሩ የሥርዓት ችግር ነው። የቤቴ መቃጠል ለትኋኑ በጀኝ እንዳለው ቂል እንዳንሆን።
ኢትዮጵያዊነትን መካድ የራስን ማንነት መካድ ብቻ አይደለም። አባቶችንና እናቶችን፣ቅድም አያቶችን ከነቅርሳቸው መካድ ነው። በእንደዚህ ዓይነቱ ክህደት ላይ የተመሰረተ ማንነት የት ይደርሳል?ከበሽታ በቀርስ ትርፉ ምን ይሆናል? ክህደት ራሱን የቻለ በሽታ ሲሆን ማስካድ ደግሞ የባሰ ነው። ክዶ ማስካድ ታምሜያለሁኝ፣ ታመሙ እንደማለት ነው። አስታማሚ እንኳን እንዳይገኝ የማድረጉ ጥረት የበሽታውን ምለዓትና ጽናት ያመለክታል።
ሆኖም የኢትዮጵያ ታሪክ ሊያስተምረን እንደሚችለው ኢትዮጵያዊነት እንደ ላስቲክ ነው። ሲስቡት ይሳባል፣ሲለቁት ይሰበሰባል። ማለት-ይሳብና ይሳሳል እንጂ አይበጠስም።
ከፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ኢትዮጵያ ከየት፣ወዴት? ገጽ 31-32 1986 ዓ.ም. መጽሀፍ የተወሰደ
‪#‎ኤርሚያስ_ቶኩማ‬

ቻይንዬ ቻይንዬ ፣ ቻይኑካ ፣ ቻይንሻ

ቻይንዬ ቻይንዬ ፣ ቻይኑካ ፣ ቻይንሻ (ሄኖክ የሺጥላ )
አቶ ኢሳያስ በታዲያስ አዲስ ጋዜጠኞች ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለምን ቻይና እንደቀጠረ ሲጠየቁ ፣ በፈረንጅኛ እንዲህ ነበር ያሉት <<China is the biggest humanity >> ፣ በመጀመሪያ ይህ አርፍተ ነገር ምን ማለት ነው ? ብሎ መጠየቅ አይቻልም ። ሁለተኛ ምንም ማለት ቢሆን ፣ እነሱ እንደሆነ ቻይና ቀጥረዋል ።
ስለ ደሞዛቸው ሲጠየቁ ደሞ << ያው ባለም ገበያ መሰረት ነው ፣ እነዚህ ሰዎች ባሮች አይደሉም >> ይላሉ ። ምን ማለት ነው ? ኢትዮጵያውያን ሆስተሶች ባሮች ናቸው ማለት ነው ? ወይስ ኢትዮጵያዊ ከዓለም ጠርዝ ዳር ሄዶ ቁጭ ያለ አንደርቢ ነው ? አልገባኝም ።
ስለ ጥቅሙ ሲጠየቁ << ይህ ነገር ቱሪዝምን ያስፋፋል ፣ አበባ ያመጣሉ እና ወዘተ >> ። ባንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ስለ 11 % እድገት ለማስረዳት ፣ ጃፓንን ብናያት ፣ ኮሪያን ብናያት ፣ እንትናን ብናያት ፣ ብናያት ብናያት ፣ ያለው ትዝ አለኝ ።
ቆይ ግን ቻይና ለምን ቀጠራችሁ ምክንያታችሁ ምንድን ነው ሲባሉ << ቻይንኛ የሚናገር ሆስተስ ስለሌለ!>> ይላሉ። ግሩም መልስ ነው ። እስኪ ይህንኑ ጥያቄ ለአዲስ አበባ እና ክፍለሃተ ሃገራት ዩንቨርስቲ ( ወይም ባጭሩ ለትምህርት ሚንስቴር ልጠይቅ ) << ለምንድን ነው የህንድ ሌክቸረር በዩንቨርስቲው ውስጥ የቀጠራችሁት ፣ የራሳችን ሰው ጠፍቶ ነው ? መልስ << የዩንቨርስቲ መምህሮች ህንድኛ ስለማይችሉ >>! እሺ ሌላ ጥያቄ << ለምንድን ነው አብዛኛውን የመንገድ ግንባታ ለቻይና ኮንትራክተሮች ከመስጠት አልፎ ፣ የጉልበት ሰራተኞቹ ሳይቀሩ ከቻይና ተጭነው መጥተው የሚሰሩት ? በኛ ሀገር ለጉልበት ሥራ የሚሆን ሰው ጠፍቶ ነው ? መልስ << መንገዱ ቻይና ካልሰማሁ ፣ መንገድ አልሆንም ስላለ !>>።
እሺ ለምንድን ነው በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ የሩሲያ የጦር ጀት አብራሪዎች እና መምህሮች በአሁኑ ሰዓት ተቀጥረው የሚሰሩት ? << ምክንያቱም ይህንን ሕዝብ በሰማይ ናዳ ( ቦምብ ) ልናፈነዳው ስናቅድ ፣ ቦምቡን በሩሲያኛ ብንወረውረው ገድሉን ማራኪ ስለሚያደረገው ። ሌላ ጥያቄ << አቶ ሰውነት ቢሻውን የተካው የእግር ኳስ አሰልጣኝ ፣ ምን አዲስ ወይም የተሻለ ነገር አመጣ ? መልስ << ምንም ባያመጣም የውጭ ሀገር አሰልጣኝ ስለሆነ ታላቅ ፣ ዘላለማዊ ክብር ይሰማናል >>። እና ወዘተ አይነት መሳ ለመሳ የሚሄዱ መልሶች ናቸው ።
ለማንኛውም ፣ ምን ታመጣላችሁ ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናዊ ሆስተሶች ቀጥሯል ። እነ ከበቡሽ አረብ ሀገር ሄደው ገረድ ይሁኑ ፣ እነ ሮማን ፣ አማሪካ እና አውሮፓ የፈረንጅ ዳያፐር ይቀይሩ ፣ እነ ተሎሳ እና አንቃንቀው በራሳቸው ላይ ቦድነው አንተ አማራ ፣ አንተ ኦሮሞ እያሉ ይቧጨቁ ፣ ሀገርሽን ግን ጉግ ማን ጉግ ተቀባብሎሻል ።
ስለዚህ እንዲህ እንላለን
ቻይና በሰማይ ላይ
ቻይና በምድር
ክንፍ አውጥቶ ሲከንፍ
አየሁት ሲበር ።
ቻይና ጉዱ ካሳ
ቻይንዬ ቴዎድሮስ
በመተከል አርገህ ፣ ኃሙሲት ድረስ !
ቻይና በአላማጣ ፣ ቻይና በጨጨሆ
ውሻ ያበላሃል ፣ እንደ አንበሳ ጩሆ !
ቻይና ነን ፣ ቻይና ነን ፣ ቻይና ነን ያላችሁ
ሳቁ ፣ ሳቁ ፣ ሳቁ ፣ ሳቁ እንያችሁ !
አይናችሁ ሲጨፈን ፣ በፈገግታ ሰክሮ
እናሾፍ ነበር ያኔ ድሮ ድሮ !
አሁንማ ቻይና ፣ ነገሰ ባገሬ
ሺን ሿ እና ኩን ፉ
ያዙት ባለ ክንፉን
በአይናቸው ስቀው ፣ በልብ እያሾፉ !
ቻይንዬ ቻይንዬ ፣ አንቺ የኔ ደርባባ
ሀገሬን ቀማሽኝ
ስራዬን ቀማሽኝ
አረ ወዴት ልግባ ?
አሞራ በሰማይ ፣ አሞራ በምድር
እኛ ብሎ ሀበሻ አቤት ስንደብር !
ቻይንዬ ፣ ቻይንዬ ፣ ቻይኑካ ፣ ቻይንሻ
ሼም የለሽም አሉ ፣ ለኔ አይነት አበሻ  

Saturday, 10 October 2015

LET'S STAND TOGETHER TO STOP VIOLENCE AGAINST WOMEN!!

«አሳዛኝ ዜና»
ይህቺ ፎቶዋን የምትመለከቱት ወጣት ማኅደር ጫኔ ትባላለች፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪ ስትሆን፣ ለእረፍት ተወልዳ ያደገችበት አጋሮ ከተማ ቆይታ ወደ ጎንደር ከተመለሰች 2 ሳምንት አልሞላም፡፡ ከትላንት ወዲያ (መስከረም 26፣ 2008 ዓ.ም.) ምሽት ላይ ጎንደር፣ ኤምባሲ ሆቴል አካባቢ ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች በሚኒባስ መኪና መጥተው በስለት ወግተዋት በመጡበት መኪና በማምለጣቸው ሕይወቷ አልፏል፡፡ ማኅደር መልካም ባህሪ ያላት ወጣት እንደሆነች የሚያውቃት ሰው ሁሉ ይመሰክራል፤ ለቤተሰቧ ብቸኛ ሴት ልጅ እንደመሆኗ በተለይ ከእናቷ ጋር ልዩ ፍቅር የነበራት ልጅ ነች፡፡ ለቤተሰቦቿ፣ ለጓደኞቿ እና ለሚያውቋት ሁሉ መጽናናትን እየተመኘን፣ ይህን ማስታወሻ “ሼር” በማድረግ ፍትሕ እንዲሰፍን የበኩላችንን እናበርክት፡፡
LET'S STAND TOGETHER TO STOP VIOLENCE AGAINST WOMEN!!
በንፁኃን ላይ የሚፈፀም የግፍ ግድያ ይቁም!!
ፋስት መረጃ ዶት ኮም / በእዮብ ሙላቱ
ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛለን።

Friday, 9 October 2015

አዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄን የትግል ጥሪ ባዘሉ በራሪ ወረቀቶች ተጥለቅልቃለች!

አዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄን የትግል ጥሪ ባዘሉ በራሪ ወረቀቶች ተጥለቅልቃለች!
ዛሬ ደግሞ የትግል ጥሪ ወረቀቶቹ የክልል ዋና ዋና ከተሞችን ጨምሮ በአንዳንድ የዞን ከተሞች እየተሰራጩ መሆኑ ታውቋል!
የነፃነት ትግሉን የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን የትግል ጥሪዎችን በመተኑ ላይ እንዲሳትፉ ከንቅናቄው ጥሪ ቀርቧል!
በአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የተዘጋጁት ከታች የምትመለከቷቸው የትግል ጥሪ ያዘሉ በራሪ ወረቀቶች አዲስ አበባን አጥለቅልቀዋታል። በራሪ ወረቀቶቹ ዛሬ ደግሞ የክልል ዋና ዋና ከተሞችን ጨምሮ በአንዳንድ ታላላቅ የዞን ከተሞች በስፋት እየተሰራጩ ነው። በወረቀት ስርጭቱ ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 ትን የነፃነት ትግል የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን በስፋት እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል። በራሪ ወረቀቶቹ የሚደርሷቸው ኢትዮጵያውያን በጥንቃቄ በ ...5 ኮፒ በማባዛት (ወይም የትግል ጥሪዎቹን በወረቀት ላይ በፓርከር በመገልበጥ) እንዲያሰራጩና የነፃነት ትግሉን እንዲያፋጥኑ ከንቅናቄው ጥሪ ቀርቧል።
በባህር ዳር የተደራጁት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ከጥቂት ሳምንታት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ከተማዋን የትግል ጥሪዎችን ባዘሉ ወረቀቶች አጥለቅልቀዋት እንደነበር አይዘነጋም።
ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ወደ ፊት!


Thursday, 8 October 2015

በእውነት ታላቅ ሰው አጣን

የዘመናችን ታላቁ ቤተ መጻህፍት ተቃጠለ የአንድ ሽማግሌ ሞት የአንድ ታላቅ ቤተ መጻህፍት ቤት የመቃጠል ያክል ኪሳራ ነው ይባላል::
(በስሜነህ ጌታነህ)
ይሃው ይሄ አዲስ አመት ከገባ በኋላ ይሄው መአተኛ መስከረም ሌላዉን ታላቅ የታሪክ ምሁር ዘዉዴ ረታን ነጠቀን::አምባሳደር ዘዉዴ ረታ በእዉነት ለመናገር እስከ ዛሬ ካነበብኳቸው የታሪክ መጽሃፍት ሁላ እጅግ በመረጃዎች እና በዶክመንቶች የበለጸገ እንዲሁም ማራኪ የቃላት ፍሰትን በዉስጡ ያጨቀ መጽሃፍ ጽፈው ያበረከቱልን ታላቅ ጸሃፊ ነበሩ::
ዘዉዴ ረታ በተለይ የኤርትራ ጉዳይ በተሰኘ መጽሃፋቸው የዛሬይቷ ኤርትራን ለመገልጠል ያበቃትን ምክንያት እና ኤርትራን ከእናት ሃገሯ ጋር ስለመቀላቀል የተደረገውን ታላላቅ የዲፕሎማሲ ጥረቶች አብጠርጥረው እና አንጠርጥረው አሳይተዉናል::ተፈሪ መኮንን ረዥሙ የስልጣን ጉዞ በተሰኘው መጽሃፋቸውም አጼ ሃይለስላሴ የስልጣኑን እርካብ እንዴት አድርገው እንደተቆናጠጡ ምን አይነት ግለ ስብእና እንደነበራቸው ጨምሮ ሌሎች አበይት ታሪኮችን ከትበዉልን እንደ ሌሎች የታሪክ አዋቂዎች የጋን ዉስጥ መብራት ሳይሆኑ ለሌላው ጮራን የፈነጠቁ ታሪክን በግዙፍ መጽሃፍ እየጻፉ ያስረከቡን ሰው ነበሩ::
አብዛኛዎቹ ስለ ኤርትራ የሚጻፉ መጽሃፎች አንድም በጥላቻና በግልብ የሃገር ፍቅር የተጻፉ ሚዛናዊነት የጎደላቸው ሲሆኑ አንድም የመረጃ እጥረት የሚታይባቸው የተለበለቡ እንጂ ያልበሰሉ ጽሁፎች ነበሩ::
የአምባሳደር ዘዉዴ ረታ “የኤርትራ ጉዳይ”የተሰኘው በሻማ ቡክስ አታሚዎች የቀረበው መጽሃፍ ግን እጅግ የተለየ ድንቅ መጽሃፍ ነበር:: ሌላው ደግሞ ስለ አጼ ሃይለ ስላሴ ከዉልደት እስከ አገዛዝ ዘመናቸው የጻፉት ሁለት ትልልቅ መጽሃፋቸው ነው::የመጀመሪያው “ተፈሪ መኮንን ረዥሙ የስልጣን ጉዞ” የሚለውና “የቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ መንግስት” የሚለው እጹብ ድንቅ መጽሃፋቸው ነው::
በቅርብ ጊዜ በሰጡት ቃለ ምልልሳቸው ላይ “እድሜ እና ጤና ይስጠኝ እንጂ ከህመም ጋር እየታገልኩም ቢሆን የቀረዉን መጽሃፌን እጨርሰዋለሁ” ብለው ቃል ገብተዉልን ነበር::አይ ሞት ክፉው ሳይጨርሱት ነጠቀን::ይብላኝ ለኛ ላላወቅነው እንጂ እርሳቸውማ ኖረዉበት ያወቁት ታሪክ ነው::
ለኛ እዉቀታቸውን ሊያካፍሉ ከእንግሊዝ ላይብረሪ እስከ ጣልያን ላይብረሪ ድረስ ከኪሳቸው በሚያወጡት ገንዘብ እየተንከራተቱ ባገኙት መረጃ የጻፏቸውና ያሳተሟቸው በደፈናው መጽሃፍ የሚባሉ ታላላቅ ጥራዞች ዛሬም ይሄ ትዉልድ በሚገባ አንብቦ እና መርምሮ በሚገባ የተረዳው አይመስለኝም::
እንግዲህ ታላቁን ቤተ መዛግብታችንን አጣን ዘዉዴ ረታም አረፉ::በሟች ማዘን የለም ባለ መጽናናት ነው ይሉ የለ::በቃ ቀሪ ቅርሳችን የእርሳቸው መጻህፍቶች ናቸው በእነርሱ እንጽናና እንጂ::
ክቡር አምባሳደር ዘዉዴ ረታ ነብስዎትን ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን:

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አሚሶል ስር ያለውን ንብረነታቸው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የሆኑትን ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በደቡባዊ ምዕራብ ሶማሊያ በጌዶ ግዛት በደፈጣ ውጊያ ማውደሙን አልሸባብ አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በአሊላን መንደር ውስጥ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ሰራዊት መሃከል ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነው። በአርፒጂ የጦር መሳሪያ ተሽከርካሪዎቹ መመታታቸውን የአካባቢው የዐይን እማኞች ተናግረዋል። በአልሸባብ ጥቃት ብዛት ያለቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን ራዲዮ ሸበሌ ቢዘግብም፣ ከገለልተኛ ምንጮች አለማረጋገጡን አስታውቋል። ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ የአፍሪካ ሕብረት ጦር አሚሶም በምድር እና በአየር ላይ ጥቃት በመፈጸም ስትራቴጂክ ከተማ የሆነችውን ዋርዴርን ከአልሸባብ እጅ አስለቅቆ የያዘ ሲሆን ፣ በወቅቱ ብዙ ሰላማዊ ሰዎችና የሰራዊት አባላት መገደላቸው ማእረግ ድረገጽ በሰበር ዜናው ዘግቧል። በሶማሊያ ከተሰማራው የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ አገራት ውስጥ አብዛኞቹ የደረሰባቸውን የሰራዊት ሞትና ቁስለኛ ለ ሕዝባቸው በየወቅቱ የሚገልፁ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት በሰራዊቱ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ለአንድም ቀን ለፓርላማ አባላት እንኳ ገልጾ አያውቅም። የሟችና የጉዳተኛ ቤተሰቦችም ስለ ልጆቻቸው ምንም ዓይነት በቂ መረጃ አግኝተው አያውቁም ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን ገልጿል።