Thursday, 25 June 2015

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

ሰበር ዜና - የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18/2007 ዓም በአቶ
አንዳርጋቸው ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግ/ወያኔን መንግስትን ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘገበ።
የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሙንድ
ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18/2007 ዓም የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢህአዴግ/ወያኔን መንግስት ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዘገባ ገልጧል።ጉዳዩን አስመልክቶ የዘገበው ሮይተርስ የሚከተሉትን ነጥቦች እና ሌሎችንም ይዟል -
የኢትዮጵያ መንግስት የእንግሊዝ ዜግነት ያለውን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የያዘበት አግባብ በምንም አይነት ተቀባይነት የሌለው እና ጉዳዩ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የመጉዳት ትልቅ አደጋ እንዳለው ዛሬ ሐሙስ ለኢትዮጵያ መገለፁን ያብራራል።
ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18/2007 ዓም የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሞንድ ለኢትዮጵያው አቻቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ በጉዳዩ ላይ አፅንኦ ሰጥተው ማስታወቃቸውን ያብራራል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ ጋር ያለን የሁለትዮሽ ግንኙነት አደጋ ላይ ነው ማለታቸውን ገልጧል።
የሮይተርን ሙሉ ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

LONDON
UK tells Ethiopia its treatment of opposition official imperils ties
The British government told Ethiopia on Thursday its treatment of an imprisoned opposition figure, who is also a British national, was unacceptable and that the case risked hurting ties between the two countries.
Andargachew Tsige was sentenced to death in 2009 in absentia over his involvement with an opposition political group and another trial handed him life behind bars three years later. He was arrested in Yemen in 2014 and extradited to Ethiopia.
British Foreign Secretary Philip Hammond said on Thursday he had discussed the matter with Tedros Adhanom Ghebreyesus, his Ethiopian counterpart, and delivered a stern message.
"I am deeply concerned that, a year after he was first detained, British national Andargachew Tsige remains in solitary confinement in Ethiopia without a legal process to challenge his detention," Hammond said in a statement after the call.
"I am also concerned for his welfare and disappointed that our repeated requests for regular consular access have not been granted, despite promises made."
Britain summoned Ethiopia's chargé d'affaires in August last year to seek assurances that Tsige would not be put to death.
Secretary-general of the Ginbot 7 political group, he was among 20 opposition figures and journalists charged with conspiring with rebels, plotting attacks and attempting to topple the government.
Hammond said Britain's ties with Ethiopia were at risk.
"Ethiopia's failure to grant our repeated and basic requests is not acceptable," he said. "The lack of progress risks undermining the UK’s much valued bilateral relationship with Ethiopia."
(Reporting by Andrew Osborn; Editing by Stephen Addison )
Source - Reuters

Tuesday, 23 June 2015

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ, ኦስሎ ተካሄደ!!!

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ, ኦስሎ ተካሄደ!!!
የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ታግተው ለዘረኛውና አፋኙ የወያኔ ቡድን ተላልፈው የተሰጡበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ደረጃ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በጁን 23/ 2015 በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት እልህና ቁጭት የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰልፉ ላይ ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የተገኙ በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከ13፡30 ስዓት ጀምሮ ታላቋ ብርታኒያ ለዜጋዋ አቶ አንዳርጋቸው ልዩ ትኩረት አድርጋ ከዘረኛው ወያኔ ነጻ በማውጣት ወደ ቤተሰቡ እንዲመለስ ለማሳሰብ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የነጻነት ታጋዩን አንዳርጋቸውን በተመለከተ የተለያዩ መፎክሮችን አሰምተዋል።
በዝግጅቱ ወቅት ከተሰሙት መፎክሮች መካከል “አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም” አንዳርጋቸው ነጻ ይወጣ ዘንድ እንግሊዝ ግፊት ታድርግ”፣ “በአንዳርጋቸው ላይ ለአንድ ዓመት ሙሉ እየደረሰበት ያለው የስቃይና የመከራ ዘመን ይብቃ”፣ እንግሊዝ ዜጋሽ የት ነው?”፣ “እንግሊዝ! ዜጋሽ አደጋ ውስጥ ነውና ደህንነትና ጥበቃ ያዝፈልገዋል፣ የህግ ከለላም እንዲሁ” “አዎ! እኛ ሁላችን አንዳርጋቸው ነን!” ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ያስፈልገናል” በማለት ከፍተኛ ሀገራዊ ስሜት በተንጸባረቀበት መልኩ ጩኸታቸውን አሰምተዋል።
በመቀጠልም አርበኞች ግንቦት ሰባት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተሰጠውን መግለጫ ለተሳታፊዎች በድምጽ ተነቧል። መግለጫውም የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታገት ንቅናቄው የበለጠ
እንዲጠነክርና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ውህደት በመፍጠር ትግሉን ወደፊት እንዲሄድ አድርጎታል እንጂ ወያኔ እንዳሰበው ትግሉ ወደ ኋላ እንዳልቀረ ይጠቅሳል።
በመግለጫው ማጠቃለያም በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በአፈናው የተነሳ የደረሰው መከራ ስቃይ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ለፍትህ ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት በመቆማቸው በወያኔ አረመኔዎች ቁም ስቅላቸውን የሚያዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሰቆቃ የሚያበቃው የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ በሚያደርገው ሁለ ገብ ትግል በመሆኑ ማንኛችንም በአቶ አንዳርጋቸውም ሆነ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንደራሳችን አድርገን የሚሰማን ወገኖች በሙሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከታፈኑበት አንድ አመት ወዲህ የተጀመረውን ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አጠናክረን ወደ ውጤት በማድረስ የመጪው ዘመን የህዝብ የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ተስፋ የሚለመልምበት የወያኔ አምባገነን ስርአት እድሜ የሚያጥርበት ዘመን እንዲሆን ሁላችንም የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ወገናዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በተወካዮች አማካኝነት ለኢምባሲው ከተሰጠ በኋላ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ዝግጅቱ በታቀደለት ስዓት በተሳካ 
ሁኔታ ተጠናቋል።


Wednesday, 17 June 2015

የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል!!!

የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል!!!
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ!

አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡
ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡
ሳሙኤል በአሰቃቂ ሁኔታ ከመገደሉ በፊት በተለያዩ ጊዚያት ለሚመለካታቸው አካላትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፋቸው የነበሩ መልዕክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ ግንቦት 25 2007 ዓ.ም በራሱ ገፅ በሆነው “የፌስ ቡክ” ማህበራዊ ሚዲያ ካስተላለፈው መልዕክት መረዳት እንደሚቻለው በተደራጀ ሁኔታ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነች አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሆኖም የሚሰማውና የሚጠብቀው ምንም አካል እንዳልነበረ ይልቁንም ለመገደሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላት እንደነበሩ ስጋቱን በገለፀ በቀናት ውስጥ ሕይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፏ ጉልሕ ማስረጃ ነው፡፡
በሰላማዊ ትግል ፅኑዕ እምነት የነበረው ሳሙኤል አወቀ ይደርስበት የነበረውን ለቁጥርና ለዓይነት አታካች የሆነ በደል ተቋቁሞ፣ ትግሉን እንዲያቆም ወይም የሚወዳትን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላትን ሐገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይህ ካልሆነ ግን የእሱን ሕይወት ለማጥፋት እጅግ ቀላል መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ደጋግመው ቢነግሩትም በጭቆና ስር ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ከማጠፍ ይልቅ ሕይወቱን ለመሰዋት እንደሚቀለው የገባውን ቃል በተግባር አስመስክሮ አልፏል፡፡ በማሰርና በመደብደብ አላማውን እንደማያስቀይሩት፤ ከገደሉት ግን ቀሪ ታጋዮች በተለይም የእድሜ አቻዎቹ የሆኑ የእርሱ ትውልድ የሚሰዋለትን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ “ትግሌን አደራ!! አደራ!!” በማለት ተማፅኖ አስቀምጧል፡፡
እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!!
ይህ ስርዓት በህግም በሞራልም ኢትዮጵያን የማስተዳደር ብቃት የለውም፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እያልንም አናላዝንም፤ ወንጀለኞቹ የመንግስት አካላት ናቸውና፡፡ በወንድማችንና ገና በለጋ እድሜው በተቀጨው የትግል አጋራችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ እንዳላዬ ዝም ያለ መንግስት ከዚህ የተሻለ መልካም ነገር ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልዕክት አለን፡፡ እስከ መቼ በግፍ እንገደላለን?!! ሸፍጠኞችስ እስከ መቼ ይዘባበቱብናል?!! ትግል ለውጤት የሚበቃው በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መፍጨርጨር ብቻ ባለመሆኑ የግፍ ስርዓት እንዲያበቃ ሁላችንም የሚገባንን የዜግነት ድርሻ እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ በአጠቃላይም የተለየ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ በካድሬዎች የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የሚሳደዱ፣ የሚዋረዱና የሚገደሉ ዜጎች ለከፈሉት መራራ ፅዋ ክብር ይሰጣል፡፡ መስዋዕትነታቸውም በከንቱ እንዳይሆን እሰከመጨረሻው ይታገላል፡፡
ሳሙኤል “ብታሰርም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሐገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃልህ ከመቃብር በላይ ነው!!!! ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!! ትግል ይቀጥላል . . .
ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል ለአሜሪካ አርዳታ ድርጅት ሃላፊነት የታጩትን ጌይል ስሚዝን ተቃወመ።


የዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል ለአሜሪካ አርዳታ ድርጅት ሃላፊነት የታጩትን
ጌይል ስሚዝን ተቃወመ።
የዲሲ ወጣቶች ግብረ ሃይል አባል መኮንን ጌታቸው የህወሀትደጋፊ በመሆን የሚታወቁትና ለUSAID ሃላፊነት የታጩትን ጌይል ስሚዝን በመቃወም በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይተቃውሞ አሰምቷል። ጌይል ስሚዝ በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የአሜሪካን መንግስት ጀርባ እንዲሰጥ ከሚያደርጉ ሰዎች አንዷ ናቸው። መኮንን የሟቹን ሳሙኤል አወቀን ፎቶግራፍ በመያዝ ተቃውሞውን አሰምቷል።

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አሁንም ስቃይ ላይ ናቸው

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አሁንም ስቃይ ላይ ናቸው ።_"በህይወት የመቆየት ምክንያት የለኝም። መሞት እፈልጋለሁ" አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከህወሀት የማሰቃያ ጨለማ ቤት። ዛሬ የእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ ኢንድፔንደንት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የጤንነት ሁኔታ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዘገቧል። አቶ አንዳርጋቸው ፍጹም ጤናቸው መታወኩና ከበፊቱ ምንም አይነት ለውጥ አለማሳየቱ ስቃዩም የጨመረ መሆኑን ። ለባሌቤታቸው ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሰጣቸው ሪፖርት አስደንጋጭ እንደሆነ ጋዜጣው ጠቅሷል።
ባለፈው አንድ ኣመት በማይታወቅ ምስጢራዊ እስር ቤት ታስሮ የሚገኘው የነጻነት ኣርበኛው የኣንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ኣሳሳቢ መሆኑን እና ያለበትን ሁኔታ አስመልክቶ ፍራቻዎች እየሰፉ መምጣታቸውን የተገለጸ ሲሆን የብሪጣንያ መንግስት ታጋዩን አንዲያስለቅቅ ግፊት አየተደረገበት አንደሆነና የኣንዳርጋቸው ጉዳይ ኣሳሳቢ በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት የቶርቸር ጉዳዮችን የሚመለከተው ክፍል ሃላፊ የሆኑት ጆን ማንዴዝ ጉዳዩን ማየት የጀመሩ ሲሆን ታጋይ ኣንዳርጋቸው ተለቆ ወደ አንግሊዝ አንዲመለስ ኣስፈላጊ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸው ታውቍል።

Tuesday, 16 June 2015

ሳሙኤል አወቀ ተገደለ

ሳሙኤል አወቀ ተገደለ
የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡
ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡

Tuesday, 9 June 2015

የምርጫው ሰሞን የወጣው የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዕድለኞች ከምርጫው በኋላ ዱብ ዕዳ እንደወረደባቸው እየተናገሩ ነው..

የምርጫው ሰሞን የወጣው የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዕድለኞች ከምርጫው በኋላ ዱብ ዕዳ እንደወረደባቸው እየተናገሩ ነው...
የኮንደሚኒየም ዕድለኞች ለቅሶ
የምርጫው ሰሞን የወጣው የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዕድለኞች ከምርጫው በኋላ ዱብ ዕዳ እንደወረደባቸው እየተናገሩ ነው፡፡ዕጣው እንደደረሳቸው ካረጋገጡ በኋላ እስከዛሬ ከቀበሌ ወደ ክፍለ ከተማና ቤቶቹ ይገኙባቸዋል ወደተባሉ ሳይቶች ሲመላለሱ የቆዩት ዕድለኞች በዛሬው ዕለት ጆሮን ጭው የሚያደርግ መርዶ ተነግሯቸዋል፡፡
ቤቱን ከመረከባቸው በፊት የተወሰነ ክፍያ እንደሚከፍሉ ተነግሯቸው የነበሩት ዕድለኞች በድንገት ‹‹እስከ ፊታችን አርብ ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርጉ ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ዕድሉ እንደሚያልፋቸው ተነግሯቸዋል፡፡ባለ 2 መኝታ ቤት ደርሷቸው የነበሩ አንድ አባወራ ‹‹91.000ብር እስከ አርብ ከየት እንደማመጣም አላውቅም እናም ብቸኛው አማራጪ ዕድሉን በተወሰነ ብር የሚገዛኝን ባለ ሀብት መፈለግ ብቻ ነው፡፡እሱም ቢሆን ከአርብ በፊት እንዴት እንደሚገኝ አላውቅም››ብለዋል፡፡

Wednesday, 3 June 2015

ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት

ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት!
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በመንግስት ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በምርጫ ማግስት ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ለእስር የተዳረገችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት፡፡...
ዛሬ ግንቦት 26/2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረበችው ወ/ሮ ንግስት፣ በፌደራል አቃቤ ህግ ከሳሽነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 490/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት አሸባሪ፣ ታርዷል ወገኔ፣ ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ፣ ወያኔ አሳረደን፣ ናና መንግስቱ ናና፣ ወያኔ አሸባሪ...በማለት እጅን አጣምሮ ወደላይ በማድረግ ታስረናል›› በማለት ሰላማዊ ሰልፉ እንዲታወክ አድርጋለች በሚል ተከሳለች፡፡ በተጨማሪም በሚያዝያ 13/2007 ዓ.ም ቂርቆስ አካባቢ ‹‹ስብሰባን ወይም ጉባኤን›› በማወክ እንደተከሰሰች የክስ ቻርጁ ያሳያል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበችበት ወቅት ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ‹‹በምስክሮች ላይ ማስፈራራት እየተፈጸመ ስለሆነና ምርመራየንም ስለጨረስኩ›› በሚል ፖሊስ ዛሬ ቤተሰቦቿ እንኳ ሳይሰሙ ወ/ሮ ንግስትን ፍርድ ቤት አቅርቦ ክስ መስርቶባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው በቀጣይ አርብ ግንቦት 28/2007 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡


Tuesday, 2 June 2015

ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት

ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት @semayawiparty
የኢትዮጵያ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን የጭካኔ እርምጃ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የታሰረው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት፡፡ ዛሬ 25/2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩን ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት...›› የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንጋይ በመወርወር ሰልፉን አውካችኋል›› የተባሉ ሌሎች አምስት ወጣቶች ለሰኔ 4 የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ተቀጥረዋል፡፡ በሰልፉ ሰበብ ተይዘው የታሰሩት ወጣቶች በቤተሰብ እንዳይጠየቁ መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡