የምርጫው ሰሞን የወጣው የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዕድለኞች ከምርጫው በኋላ ዱብ ዕዳ እንደወረደባቸው እየተናገሩ ነው...
የኮንደሚኒየም ዕድለኞች ለቅሶ
የምርጫው ሰሞን የወጣው የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዕድለኞች ከምርጫው በኋላ ዱብ ዕዳ እንደወረደባቸው እየተናገሩ ነው፡፡ዕጣው እንደደረሳቸው ካረጋገጡ በኋላ እስከዛሬ ከቀበሌ ወደ ክፍለ ከተማና ቤቶቹ ይገኙባቸዋል ወደተባሉ ሳይቶች ሲመላለሱ የቆዩት ዕድለኞች በዛሬው ዕለት ጆሮን ጭው የሚያደርግ መርዶ ተነግሯቸዋል፡፡
ቤቱን ከመረከባቸው በፊት የተወሰነ ክፍያ እንደሚከፍሉ ተነግሯቸው የነበሩት ዕድለኞች በድንገት ‹‹እስከ ፊታችን አርብ ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርጉ ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ዕድሉ እንደሚያልፋቸው ተነግሯቸዋል፡፡ባለ 2 መኝታ ቤት ደርሷቸው የነበሩ አንድ አባወራ ‹‹91.000ብር እስከ አርብ ከየት እንደማመጣም አላውቅም እናም ብቸኛው አማራጪ ዕድሉን በተወሰነ ብር የሚገዛኝን ባለ ሀብት መፈለግ ብቻ ነው፡፡እሱም ቢሆን ከአርብ በፊት እንዴት እንደሚገኝ አላውቅም››ብለዋል፡፡

No comments:
Post a Comment