Friday, 22 May 2015

ቴዎድሮስ አስፋው በድጋሜ ዋስትና ተከለከለ

ቴዎድሮስ አስፋው በድጋሜ ዋስትና ተከለከለ
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ግድያ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስሮ በ6 ሺህ ብር ዋስትና ከወጣ በኋላ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ያሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው በድጋሜ ዋስትና ተከልክሏል፡፡ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ቴዎድሮስን ካሰረው በኋላ ፍርድ ቤት አቅርቦ ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ አሰጥቶበት የነበረ ቢሆንም ቀጠሮው ከተሰጠ በኋላ ለፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ ተከሳሹ ከሀገር ሊወጣ እንደሚችል በመግለጽ ከቀጠሮው በፊት በሰበር ከታየ በኋላ በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ተጠይቋል፡፡
ይህንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ‹‹ተከሳሾቹ የዋስትና ግዴታቸውን እንደማይወጡ ግምት በመውሰድ ቀድመው ያስያዙትን ዋስትና ቀሪ በማድረግ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥ›› ሲል ጠይቋል፡፡ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ካሰረው በኋላ ቴዎድሮስ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበር ሲሆን አሁን ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲዛወር ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ – የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!

የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!! አገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::
ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?
ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።
ዛሬ በግሌ እና በአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። በዚህ ምርጫ አትሳተፉ። የምርጫ ካርዳችሁን ቀዳችሁ ጣሉት። እናምርር። ካላመረርን ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ይልቅስ ለማይቀረው የመጨረሻው ትግል ራሳችንን እናዘጋጅ::
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር የአገር አድን ኃይል በመገንባት ላይ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት አንከፋፈልም። ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ስብስብ ፈጥረን በኅብረት አገዛዙን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ትግል ነው። የትግሉም ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው። ክርስቲያን ሙስሊም፤ ወንድ ሴት፤ ወጣት አረጋዊ ሳንል፤ በብሔርም ሆና በቋንቋ ሳንከፋፈል ሁላችንም ይህን አስከፊ ሥርዓት በቃህ እንበለው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ - የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!
የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!
እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። በወገኖቻችሁ ላይ አትተኩሱ። ይልቁንስ አፈሙዛችሁን አገራችንን ለውርደት በዳረገውና በሙስና በተጨማለቀው ዘራፊው የህወሓት አገዛዝ ላይ አዙሩት። ታሪካችሁን ከምታበላሹ፤ ታሪክ ሥሩ። ለራሳችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለልጆቻችሁ እና ለሕዝብ የሚጠቅም አገርና መንግሥት እንዲኖረን የእናንተ የግልም ሆነ የጋራ ተነሳሽነት ወሳኝ ነው። ወያኔ ህዝቡን የሚዘርፈው በእናንተ ትከሻ ላይ ቆሞ እንደሆነ ላንዳፍታም አትርሱት:: እንደመላው ህብረተሰብ እናንተም በነጻነትና በኩራት የምትኖሩበት ሀገር እንደምትሹ አልጠራጠርም:: ስለዚህም ይህን የህወሓት የውሸት ምርጫ ተቃወሙ። ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ትግላችን እስከ ነፃነት ድረስ ይቀጥላል። ነፃነታችንን በእርግጠኝነት በትግላችን እንቀዳጃለን። የምትወዷት፣ የምትኮሩባት አገር - ኢትዮጵያ - ትኖረናለች። ለዚህ ግን ዛሬ ተደራጅተን፣ ፀንተን መታገል የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ዛሬ ሁላችንም በፍላጎትና በመንፈስ የተገናኘን ነንና ሁሉም በያለበት ትግሉን ያጧጡፍ። ውጤቱ ቀድሞ በታወቀው በዚህ ምርጫ አለመሳተፍ ለትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነውና ለውሸት ምርጫ ያለን የመረረ ተቃውሞ በምርጫው ባለመሳተፍ እናሳይ።
ነፃ እንወጣለን!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Thursday, 14 May 2015

የሁለት አመት የአስተማሪ ደሞዝ ለአንድ ቀን ፌሽታ

የሁለት አመት አስተማሪ ደሞዝ ለአንድ ቀን ፌሽታ በዲሲ (የሳሞራ የኑስ የሆቴል ወጪ በአንድ ቀን)
ጀነራል ሳሞራ የኑስ፣ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹም ናቸው። አንዳንዶች እንደዉም አገሪቷን የሚመሩት አቶ ኃይለማሪያም ሳይሆኑ እኝሁ ጀነራል ናቸው የሚሉም አሉ። ጀነራሉ በዋሽንግተን ዲሲ Mandarine Oriental Hotel እንዳረፉ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ጀነራሉ ለምን ወደ አሜሪካ እንደመጡ የታወቀ ነገር የለም። በዋሺንገትን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድህረ ገጽ ስለ ጀነራሉ ጉብኘት በድህረ ገጹ ላይ ምንም ነገር አላሰፈረም። ምናልባትም የጀነራሉን ጉብኘት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላያውቀዉም ይችላል። ጀነራል በግላቸው ለግል ጉዳይ መጥተዉም ይሆናል። በምርጫው ወቅት አዲስ አበባ አለመገኘታቸው ፣ ምናልባት የሕክምና ችግርም አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል የሚል ግምትም በአንዳንዶች ዘንድ አለ።
ሆኖም አንድ ትኩረታችንን ሊሰብ የሚገባ ትልቅ ነጥብ አለ። ጀነራሉ ያረፉበት ሆቴል እጅግ ዘመናዊና በጣም ዉድ ሆቴል ነው። ለምሳሌ ማንዳሪን ሱት የሚባለው በቀን 1295 ዶላር ( 28 ሺህ ብር ) ነው የሚከፈለው። አምባሳደር ሱት 1495 ዶላር ( 31 ሺህ ብር ) ሲሆን ኦሪየንታል ሱት ደግሞ 2500 ዶላር ( 53 ሺህ ብር) ነው።
እንደዉ አንድ ኢትዮጵያ ያለ አስተማሪ በደንብ ተከፍሎት የወር ደሞዙ 2000 ብር ቢሆን፣ ጀነራል ሳሞራ ለአንድ ቀን ዲስ ፌሽታ የሚያወጡት ቢያንስ ለሁለት አመታት የአንድ አስተማሪን ደሞዝ የሚከፍል ነው ማለት ነው።
የጀነራሉን ወጭ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍሎ ከሆነ፣ ኤምባሲው አወቆት፣ እንግዲህ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ እንዳለች በገሃድ በድጋሚ የሚያሳየን ነው የሚሆነው።
በግላቸው ከሆነ ደግሞ ጄነራል ሳሞራ የመጡት፣ ከሁለት አመታት በላይ የአንድ አስተማሪ ደሞዝን ሊሸፍን የሚችል ገንዘብ፣ ለአንድ ቀን ሆቴል የመክፈል አቅም እንዴት ሊኖራቸው ቻለ የሚል ጥያቄ ይነሳል። ይሄም አሁን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ለጥቂቶች ሲኦል እንደ ጀነራል ሳሞራ ላሉ በሙስና ለተጨማለቁ ዘራፊ ባለስልጣናትና መኮንኖች ግን ገነት መሆኗንም የሚያሳይ ነው።



ሜሮን አለማየሁ ተፈቅዶላት የነበረውን ዋስትና ተከለከለች

ሜሮን አለማየሁ ተፈቅዶላት የነበረውን ዋስትና ተከለከለች
መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው ሜሮን አለማየሁ በፍርድ ቤት የተፈቀደላትን የዋስትና መብት ተከልክላ በእስር ላይ እንድትቆይ ተደርጋለች፡፡ ሜሮን ትናንት ሚያዝያ 5/2007 ዓ.ም ንፋስ ስልክ ላፍቶ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርባ ክስ የተመሰረተባት ሲሆን በ4000 ብር ዋስ ከእስር ተለቃ እንድትከራከር የዋስትና መብት ተከብሮላት ነበር፡፡
ይሁንና ሜሮንን በዋስትና ለማስወጣት ገንዘቡ በሲፒኦ ተይዞ የዋስትናው ጉዳይ ካለቀ በኋላ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ የዋስትና መብቷን ከልክሎ በእስር እንድትቆይ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሜሮን ታስራበት ከነበረው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፖሊስ ጣቢያ ወደልታወቀ ቦታ ወስደዋታል፡፡
በተመሳሳይ በሰልፉ ምክንያት ተይዞ በ25 ሺህ ብር ዋስ ከወጣ በኋላ እንደገና ተይዞ በትናንትናው ዕለት 6 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጣ ከታዘዘ በኋላ እንደገና ዋስትናውን ተነጥቋል፡፡ ሜሮን አለማየሁና ዳዊት አስራደ ለተጨማሪ ምርመራ ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Wednesday, 13 May 2015

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ




 ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት ኢህአዴግ፣ ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ
ራሳቸው ሆነዋል።
በጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የተደረገው ግምገማ አንድ ሙሉ ቀን የወሰደ ሲሆን፣ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ መጠናቀቁን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም ብዙዎችን የግምገማ ነጥቦች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለግምገማው መራዘም ምክንያት ሆኗል።

ሁሉም ባለስልጣናት የሚገመገሙባቸው ነጥቦች ተመሳሳይነት አላቸው። አስተያየቶች የሚሰጡትም በእነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ነው።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅድሚያ ራሳቸውን የሄሱ ሲሆን፣ እንዲህ ብለዋል ” ጥራት ያለው እቅድ አዘጋጅቶ በማከናወን ረገድ ፣ ራስን በንባብ ለማብቃት ጥረት በማድረግ ላይ እንዲሁም የለውጥ ትግበራ ላይ ችግሮች አሉብኝ” ። ነገር ግን “ስራን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመፈጸም፣ ስራን በተሟላና ጥብቅ ስነምግባር በመፈጸም፣ ለስራ የተሰጠኝን መሳሪያዎች በእኔ ባይነት ስሜት በመጠቀምና በመጠበቅ እንዲሁም በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በኩል ችግሮች የሉብኝም” ብለዋል። ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል በኩል በከፊል ችግሮች አሉብኝ ሲሉ አክለዋል።
ከቃለ ጉባኤው ለመረዳት እንደሚቻለው የመጀመሪያውን ሂስ ያቀረቡት ነባሩ የህወሃት ታጋይና የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ናቸው። አቶ አርከበ ” የተጠራቀሙ ችግሮችን በመፍታት በኩል ችግሮች አሉብህ፣ ካቢኔህ ውስጥ ያለውን የጥራት ችግርም በደንብ አላየኸውም፤ ለሃገሪቱ አመራር ቶሎ ምላሽ አትሰጥም፤ ‘እኔ የሚመስለኝ እንዲህ ነው’ ከማለት ውጭ፣ ቆፍጣና የሆነ አመራር አትሰጥም፤ ስራዎች ሁሉ ከሌላው አካል እንዲመጣልህም ትጠብቃለህ፣ ብዙውን ጊዜ በቅጻቅጾች ላይ አትኩረህ አይሃለሁ፤ ከብሄራዊ ደህንነት እና የቴክኖሎጂ ቁርኝት ጋር ያለውን ችግር ቁጭ ብለህ አለመፍታትህ ውዝግቡ እስካሁን እንዲቆይ አድርጎታል” ሲሉ ሂስ ሰንዝረዋል።
ሌላው የህወሃት አባል አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ደግሞ ” ስልጣንን ጠቅልሎ የመያዝ ነገር አለ፤ ስዎችን እርስ በርስ የማጋጨት ነገርም አለ፣ ለአማካሪዎችህ ‘እሱ ምን ሰርቶ ነው’ ትላለህ፣ በፖሊሲና እና ስትራቴጂ ላይ አዲስ የፈጠርኸው ቋንቋም የለም፣ ፓርላማው በአንተ
ጊዜ አዲስ ቃላትን እንኳ አለመደም፣ ይህም ከንባብ የመጣ ችግር ነው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን በመደገፍ ፤ ሃሳብን በመቀበል ረገድ ችግር አለብህ፣ ገንቢ ሃሳብም በመስጠት ላይ ችግር ይታያል”” ብለዋል።
አቶ ሃይለማርያምን እጅግ ያበሳጫቸው የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል አሊሴሮ ያቀረቡት ትችት መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ።በቃለ ጉባኤው ላይ ሰፍሮ እንደሚታየው አቶ አሊሴሮ ” ተግባብቶ መስራት ላይ ችግር አለ፣ ከክልሎች ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል
የእሱ አስተዋጽኦ የለበትም፣ ያልተጻፉ ህጎች ይወጣሉ፤ ከክልሎች ጋር ሳትነጋገር ከምክትሎች ጋር የኮሚኒኬሽንን ስልጣን በመጋፋት የህዝብ አስተያየት ትሰበስባለህ፤ ሰዎች ነጻ ሆነው እንዲሰሩ አለማድረግ፤ ገፍቶ ሄዶ ችግሮችን አለመፍታት፣ በአማራና አፋር፣ በትግራይና
አፋር ድንበሮች ያለውን ውዝግብ ተጋፍቶ ችግሮችን ለመፍታት አለመቻል፣ ጥሩነትን ወይም በጎነትን አለማበረታታት፣ አንዳንድ ሚኒስትሮች ቤተመንግስት እንዳይገቡ መከልከል፤ እቅድ ከማውጣት ጀምሮ በፖለቲካ ላይ ለውጥ ለማምጣት ስትጥር አለመታየት” የሚሉ
ትችቶችን በንባብ አሰምተዋል።
አቶ ሃይለማርያም ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀውንና እንዲቀርብ ያደረገውን ሰው አውቀዋለሁ በማለታቸው ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር፣ እንደምንጮች መረጃ።
ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ባቀረቡት ሂስ ደግሞ ” በመንግስት በጀት እና ፋይናንስ እገዛ ማድረግ እና ስራ እንዲሰራ መደገፍ ሲኖርብህ አትገድፍም፤ የመከላከያ ገንዘብ አወጣጥን በተመለከተ በከፊል በኦዲተር እንዲጣራ ከተስማማህ በሁዋላ ፣ በግልህ ሽረህ በእኔ ላይ ዛቻ እንዲደርስብኝ አስደርገሃል። ቤተመንግስቱን ኦዲት ለማድረግ በኦዲተርነት ሰርቶ የማያውቅ ሰው ተመድቧልና አይሆንም ስል፣ ‘ሂጂ ስራሽን ስሪ ዛሬ ችሎ ሊሆን ይችላል’ ተብያለሁ፣ ይሄ ስራ እንዲሰራ አለመፈለግ ነው። ለለውጥም ዝግጁ አይደለህም። በረከት ሰብስቦን
ሁሉም ስህተቱን ሲቀበል አንተ አልተቀበልህም፣ ይሄ ለለውጥ አለመዘጋጀትህን ያሳያል።” ብለዋል።
ወ/ሮ ሙፍሪያት ” ከቢሮ ስነምግባር አንጻርም ችግሮች አሉ ይላሉ። ወደ ውጭ አገር በሚደረግ ጉዞ ላይ አድልዎ መኖሩን ራሳቸውን በምሳሌነት በማቅረብ ተናግረዋል። ” በግል ‘ አንቺ ተጽኖ ፈጣሪ አይደለሽም ፣ ደቡብ አንቺን ከሚወክል ቢቀር ይሻል ነበር’” ተብያለሁ
የሚሉት ወ/ሮ ሙፈሪያት፣ ወደ አውሮፓና ግብጽ ለሚደረገው የዲፕሎማሲ ጉዞ አስቀርቶኝ ወደ አዋሳ ልኮኛል ብለዋል። ዋናው ኦዲተር በአግባቡ እየሰራ አለመሆኑን ስናገርም ሙፈሪያት ስራ አትሰራም ብለኸኛል። ከካሱ ኢላላና ከሽፈራው ጋር ተጋጭቼ አንድም ቀን
ችግሩን ለመፍታት አልሞከርክም፤ የሰው ስም ታጠፋለህ፣ ትለማመናለህ”” ሲሉ የሰላ ትችት አቅርበዋል።
ወርቅነህ ገበየሁ ደግሞ ” ቆራጥ አመራር በመስጠት በኩል መሰራታዊ ክፍተቶች አሉብህ” ያሉዋቸው ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ ራሱ ተሟሙቶ ካልሰራ በስተቀር ሃይለማርያም አያግዘውም ሲሉ አክለዋል። “አፋጣኝ መልስ መስጠት ላይ ችግር አለ። የፌደራል ፖሊስ
ኮሚሽነር በነበርኩበት ዘመን፣ ህዳር 23 ሶማሊ በነብርኩበት ጊዜ በተደጋጋሚ ደውየ ‘ ስብሰባ ላይ ነኝ’ በሚል አልመለስክልኝም፤ ይዘነው የመጣነውን ፕሮግራም ጠፍቶብኝ ከደህንነቶች ጋር ስጨቃጨቅ ውዬ ፣ ተሰድቤ በበነጋታው ችግሩን ስነግርህ ልትፈታው አልቻልክም። የፌደራል ፖሊስ ከደህንነት ክፍሉ ጋር ያለው ግንኙነት የደከመ ነው። ጋምቤላ ላይ ያሉ ተዋጊዎችን እናጥፋቸው አሁንም ሶማሊና አማራ ክልል ያሉ አማጽያንን እናጥፋ ስልህ የደህንነት ክፍሉና ጸጋየ በርሄ ይዘውታል ብለኸኛል። ጅጅጋ በተፈጠረው ነገር አራት ጊዜ ደውየ
ምላሽ ሳጣ ለሳሞራ ደወልኩ፣ እናም ‘ ለእኔ ከማሳወቅ ይልቅ ከጦሩ ጋ መንጠንጠል ይወዳል’ አልከኝ። ኢንሳ፣ ኢሳያስ ክፍል ስንሄድ ‘ሁሉንም ነገር እንዳታደርጉ ተብለናል’ እንባላለን። ከሁሉም የደህንነት ክፍሎች ጋር ፊትና ሁዋላ ሆነን እያለ በግዴለሽነት ችግሩን አልፈታሃውም” ሲሉ ጠንካራ ነቀፌታ አቅርበዋል።
ነባሩ የህወሃት ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ በበኩላቸው ” ሃይለማርያም ቸልተኝነት ያበዛል፣ በጣም ችላ ይላል፤ ስራዎችን ይገፋል። የሚያውቃቸውን ክህሎት፣ ካለው ሃላፊነት አንጻር ለሌሎች ላማካፈል አይጥርም፤ ያለመጋጨት ነገር አለ። ሚኒስትሮች ‘በፍላጎት እንዳንሰራ
ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ስልጠናዎችን ስናገኝ ስለሚያሳልፍብን ነው’ እያሉ ስሞታ ያቀርባሉ። በስራ ስምሪት ወቅት በምትፈልጋቸው ስራዎች ላይ ራስህ ሰው ትመድባለህ። በረከት ላይ ትለጠፋለህ።” ብለዋል።
ሌላው ነባር ታጋይ አባይ ጸሃየ ደግሞ ” ሚኒስትሮች ሃላፊነት ተስምቷቸው የሚሰሩ አይመስለውም፤ ድጋፍ የማይሆን ክትትል ያበዛል፣ ሰራተኞችን በጣም ይንቃል። ከፍተኛ ሃላፊዎች ቢታመሙም የታመሙ አይመስልህም። ስራን ያላገናዘበ ሞራልን የሚነካ የሚያስፈራራ
ደብዳቤ ለአራት ሚኒስትሮች ሰጥተሃል።” ሲሉ ሂሰዋቸዋል።
የብአዴኑ ሊ/መንበርና ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ በፊናቸው ” ከህዝብ ወገንተኝነት ጋር በተያያዘ፣ አሁንም ቢሆን፣ ሁሉም እምነቶች በእኩል መስተናገድ ሲገባቸው ለፕሮቴስታንት ሃይማኖት ማዳለት እንዳለ ተገንዝቤአለሁ፤ ስራን በቁጭት ትሰራለህ ብየ አላስብም፣
የመሪነቱን እንዳልታማ እንጅ ለስራው ተቆርቁሮ የሚሰራ አይመስለኝም። አስተያየት ሲሰጥ ተቀብሎ ለማሻሻል ከመጣር ይልቅ ሃሳቡ ጥሩ ነው ብሎ የመግፋት ነገር አለ፤ ከደህንነት ክፍሉና ከጠባቂዎችህ ጋር ያለህ ግንኙነትም የደከመነ ነው” ብለዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ሮማን ገብረስላሴ ደግሞ ” ፈጣን ምላሽ መስጠት ላይ፣ ስብሰባ ከገባህ በምንም መንገድ መልስ አትሰጥም፣ ስራን ከፋፍሎ ያለመስጠት ነገር አለ። በሰው ላይ እምነት የማጣት ነገር አለ። ችግርን ወደ መድረክ አምጥቶ ከመፍታት ይልቅ ወደ ዝምታ ታመራለህ። ” ብለዋቸዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ የብአዴኑ አቶ አህመድ አብተው በበኩላቸው ” ታዳላለህ፣ የአቶ አዲሱ ለገሰን ስልጠና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ፣ በአንተ አመራር ጥሩ ስራ መስራትና ጥሩ ስነምግባር ማሳየት የመብት መጣስን ያመጣል፣ በጣም ሃይለኛ ተንኮል አለብህ፤ በአንድ ስብሰባ
ላይ ‘አማራ አይቀበልህም’ ብለህ ከብሄሬ ጋር ልታጋጨኝ ሞከረሃል። በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ ሌሎች ስራዎችን ትተሃቸዋል ስልህ ‘ ስለሌሎች አያገባህም፤ እኔ ጠ/ሚኒስትር ነኝ’ አልከኝ። ለመማር እንኳ ዝግጁ አይደለህም። እኔ እየተማርኩ መሆኔን እያወቅ ከፈቃድ አሰጣት
ጋር አድልዎ ታደርጋለህ። ከጓደኞችህ ጋር በመሆን ‘አህመድ አገሪቱን በእንዱስትሪ ጭስ አፈናት ‘ ብለህ አፌዝክብኝ፤ ሰራተኛ ምንም አይመስልህም። ሞራል ትነካለህ፣ ሞራል አትጠብቅም፣ አስተካክል።” ብለዋል።
ሌላው ትችት አቅራቢ የደህዴኑ የኮምኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ናቸው። አቶ ሬድዋን ” ገንቢ አስተያየት መስጠትን በተመለከተ ፣ ብዙ ጊዜ አንድ ፕሮግራም አስቤ እጠይቅሃለሁ። ነገ ዛሬ እያልህ ሃሳብ አትሰጠኝም። አመራር ተቆራርጦ ይሰጣል። በወኔና በእልህ ሂ
ደቱን ለመለወጥ የሚደረገው ጥረት አናሳ ነው። ከእኔ ጋር በጥሩ ሁኔታ እያወራ ፣ ከሌላ ሰው ጋር ስለእኔ ሌላ ነገር ነው የሚናገረው፤ ለበረከት ‘እሱና ሽመልስ ልዩ ተልእኮ ያላቸው ሰዎች ናቸው፣ ልቆጣጠራቸው አልቻልኩም’ ብሎ ነግሮታል። ለእኔ አልነገርከኝም። የአመራር መስፈርቶችን ታሟላለህ አልልም።” የሚል ትችት አቅርበዋል።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቀረቡባቸው ሂሶች ላይ መልስ ሰጥተዋል። “መሻሻል ያለባቸውን አሻሽላለሁ” ብለዋል። “ብዙውን ስራ እራሴ እሰራለሁ በሚል ለመስራት ስለምሞክር ነው ክፍተቶች የተፈጠሩት” የሚሉት አቶ ሃይለማርያም፣ “ስራውን ጠቅልሎ ይዟል
ለሚባለው ግን የሚገባኝን ይዣለሁ ብየ ነው የማስበው” ብለዋል። ሰዎችን ማጋጨት ለተባለው “እኔ ሰዎችን በማጋጨት ምን ላገኝ? ችግር ያለበትን ሰው ችግር አለበት ፣ ጥሩውንም ጥሩ ነው” እላለሁ። ሲሉ ተከራክርዋል።
“ሶማሊና አማራ፣ ትግራይ አፋር ላይ የተነሳው ችግር ከአሰራር ጋር በተያያዘ የመጣ ችግር መሆኑን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ በሙፍሪያት ለተነሳው ቅሬታም ” ሙፈሪያትና ሽፈራውን ለማስማማት ሁለቱም ጋር ችግር አለ፤ አባይ እንዲፈታው ነግሬዋለሁ፡፡ ብለዋል””
“ስንሰራ ከፖለቲካ ጋር አስተሳስረን እንስራ ነው ያልኩት እንጅ ስራን አልከለከልኩም የሚሉት አቶ ሃይለማርያም በአቶ አህመድ በአቶ አህመድ ለቀረበባቸው አስተያየት ደግሞ ” ፊት ለፊት ለራስህን ነው የነገርኩህ፣ ለሌላ ሰው በቀልድ መሃል ላወራ እችላለሁ።” ሲሉ በመካድና ባለመካድ መሃል ሆነው መልሰዋል።
“ለውጭ ጉዞ ታዳላለህ የተባለውን በአሰራራችን መሰረት ብናየው ጥሩ ነው ” ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ “እገሌ ከገሌ የሚባል ሳይሆን የስራውን አዋጭነት አይተን ነው ሰዎችን የምንመድበው ሲሉ አክለዋል።
“ሰው ሲጋጭ ደስ ይልሃል የተባለውን አልቀበለውም” ብለዋል። “ስራ ሲሰራ በግድ መሆን ባለበት ቀን ሊሰራ አይችልም፤ ችግሮች አሉ። የደረሰንን ስልጠና አዳርሰናል፣ ማንንም የምነካ ሰው አይደለሁም፤ ማንንም አልንቅም” ሲሉ ራሳቸውን ለመከላከል ሞክረዋል።
“እምነትን በተመለከተም በእኔ እምነት ሁሉንም እኩል እያስኬዱ ነው ” አቶ ሃይለማርያም፣ የሙስሊሙንም የክርስቲያኑንም ችግሮች እኩል አያለሁ፣ ያለሁት ፖለቲካ ላይ ነው። ብለዋል።
በአቶ ስብሃት ለቀረበባቸው ሂስ ደግሞ ” ስብሃት በጣም ይጮሃል፣ እንዳሞራ ሁሉ ይዞረኛል፣ እዚህ ሳወያይ ሁሉ በጣም ይጮሃል፣ አለቃ መሆን ችግር ነው ብየ ዝም አልሁ። ንግግር ከመልክ ያምራል ይባላልና የተሳሳትኩት ነገር ካለ አርማለሁ።በአባባል ክፈተት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በማለት በአቶ ስብሃት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።
አቶ ሃይለማርያም የቀረበባቸውን ሂስ ቢቀበሉም ሌሎች አባሎቻቸው ግን በሂስ አቀባበላቸው ላይ የሰላ ትችት ከመሰንዘር አላገዳቸውም።
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ ዱሌ ” ሃይለማርያም አሁንም ለመማር አልተዘጋጀህም፣ ሰው ከሁለት ነገሮች አያመልጥም፣ ከፈጣሪና ከህሊናው። ቀኑን ሙሉ በውይይት ፈጅተን የተሰጠን ምላሽ አልተመቸኝም”ያሉ ሲሆን፣ የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ በበኩላቸው “አብዛኛውን ገፍቶታል፣ ወደውስጡ አላስጠጋውም፣ ሁሉን ከተከላከለ በሁዋላ አስተካክላለሁ ብሎአል ” ብለዋል።
ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ደግሞ ” ከፊሎችን አልነካሃቸውም ፣ መኮርኮምም አይቸብሃለሁ፤ ይሄ ከአንድ የአገር አመራር አይጠብቅም” ያሉ ሲሆን፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ደግሞ ” አቀባበሉ ላይ ዞሮ ዞሮ ላንተ ነው የሚጠቅምህ፣ እዚህ አገር ላይ የሆነ አሻራ ብታሳርፍ ያንተ ስም ነው የሚነሳው ፣ ፍቅርንና የመተባበር መንፈስን ብትዘራ ጥሩ ነው።” ብለው ምክር ለግሰዋቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ደግሞ ” ሁሉንም ጥያቄዎች ሳያቸው በወቅቱ መፈታት ይችሉ ነበር። ነገ የተሻለ አማራጭ እንዲኖረን እነዚህን ወስደህ ማረም አለብህ። የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ አመራር ማሰሩን በተመለከተ ትእዛዙ የመጣው ከላይ ነው። ባይሰራው ኖሮ ነበር የምጠይቀው” በማለት ውሳኔ የሚወስን ሌላ ሃይል እንዳለ ፍንጭ ሰጥተዋል።
አቶ ደሴ ዳልኬ ደግሞ ” በከፍተኛ አመራሩ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ምንድነው የሚለውን ለይቶ የመፍታት ነገር ቢጠናከር” የሚል ሃሳብ ሲሰነዝሩ፣ አቶ አረከበ እቁባይ የአቶ ደሴን ሃሳብ በመደገፍ ” ጠንካራ ጎኑ እንዳለ ሆኖ መስተካከል ካለበት ነገር አንዱ ነገሮችን
ጠቅልሎ መያዝ ላይ ነው። በአሰራራችን መሰረት ሚኒስትሩ የራሱን ስራ ፣ የክልል አመራሮችም ያራሳቸውን ስራ መስራት አለባቸው። ያንን ማስተካከል ያለብህ ይመስለኛል።” ብለዋል።
አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው “ቸልተኛ መሆንህና በችግሮች ልክ ቶሎ ምላሽ አለመስጠትህ በተለይ ከራሱ ጠባቂዎችና ከቤተመንግስት ደህንነቶች ጋር እንደፈለገ እንዲጨፈርብን አድርጎናል። እዚህ ላይ ብታስተካክል ጥሩ ነው። ሌሎችን ጉዳዮች በተመለከተ ራሱ ባለቤቱ
ነው መሙላትና መጨነቅ ያለበት” ሲሉ የድጋፍ አይሉት የተቃውሞ አስተያየት ሰጥተዋል።
አቶ ሃይለማርያምም በመጨረሻ የቀረበባቸውን ሂስ እንደሚያስተካክሉ ተናግረው ግምገማው አብቅቷል። አቶ ሃይለማርያም የ ቢ ደረጃ ማግኘታቸውን ከቃለጉባኤው ግምገማ ውጤት ያሳያል።

ኢንጅነር ይልቃል ዛሬ ለቪኦኤ ልዩ ቃለ ምልልስ አደረጉ

''ሰማያዊ ፓርቲ ከትግራይ እስከ ሞያሌ ቦረና እጩዎችን አቅርቧል''
ኢንጅነር ይልቃል ዛሬ ለቪኦኤ ልዩ ቃለ ምልልስ አደረጉ
====================================
የሰማያዊ ፓርቲ ኢቲቪ ከ11 ጊዜ በላይ የመወዳደርያ አማራጭ ሀሳቦቹን ቢመልስበትም፣ካቀረባቸው ከ400 በላይ እጩዎች ውስጥ ከ200 በላይ የሚሆኑትኢህአዴግ ከፍርሃት የተነሳ በሰበብ አስባቡ ቢያስራቸውም፣በደበድባቸውም፣ ፓርቲው አሁንም ኢህአዴግ/ወያኔን ሙሉ በሙሉ የማሸነፍ ብቃት እንዳለው ከዋይት ሃውስ እስከ አዲስ አበባ እይተመሰከረለት ነው።እዚህ ላይ የምርጫውን ውጤት ማስጠበቅ እና እንደ 1997 ዓም እንዳይነጠቅ መጠበቅ የህዝቡ መሆኑ ሳይዘነጋ።
...
ኢንጅነር ይልቃል ሰሞኑን በአውሮፓ እና አሜሪካ ባደረጉት ጉብኝት ከተለያዩ
የዜና ማሰራጫዎች ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ለሕዝብ እየደረሰ ነው።የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለስልጣናትን ያስደመሙት ኢንጅነር ይልቃል ባለሥልጣናቱን ከአፍሪካ ቀንድ የደህንነት ዋስትና አንፃር የኢትዮጵያን ጉዳይ ችላ ያሉበትን አግባብ ክፉኛ ሞግተዋል።
ዛሬ ግንቦት 5/2007 ዓም ከአሜሪካ ድምፅ ራድዮ አማርኛው አገልግሎት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ (ከሁለተኛ አጋማሽ በኃላ ባለው ሰዓት ላይ ያዳምጡ) -
VOA Amharic http://av.voanews.com/…/20150512-180000-VAM068-program_orig…

ደርግን በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚከሰው ወያኔ የዘር ማጥፋት አየፈፀመ ይገኛል፡



ይህ የምትመለከቱት ወጣት መሰረት ሙሌ ይሰኛል፡፡ የወያኔ 24ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሬጅመንት ወታደሮች ከመተማ ሸዲ አቶ ፈለቀ ከተባለ የ50 ዓመት ጎልማሳ ጋር አፍነው ወደ ሁመራ በመውሰድ ምሽት ላይ ጉድጓድ ካስቆፈሯቸው በኋላ አቶ ፈለቀን ከጉድጓዱ ውስጥ እንዲጋደም  አድርገው በሁለት ጥይት ደብድበው ሲረሽኑት መሰረት በደመነብስ ወዳገኘው አቅጣጫ እግሬ አውጭኝ ይላል፡፡ ከዚያም ወታደሮች የእሩምታ ተኩስ ከፍተው የጥይት በረዶ አዘነቡበት፤ እንደዚህ ከሽንጡ፣ ከቀኝ እግሩ ከጭኑና ከባቱ ላይ ባጠቃላይ ከ3 ቦታ በጥይት ተበሳስቶ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ደርሶ ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል፡፡ ግፉ አሁንም እንደቀጠለ ነው፤ ህወሓት ሌሎችንም የመተማ አካባቢ ነዋሪዎች እያፈነ ወደ ሁመራ በመውሰድ እየረሸናቸው ይገኛል፤ ደርጉ አስሬ፣ አያናው አለምዬ፣ ስዩም ዘርይሁን፣ ታደሰ ማትያስና ጎሸ ገበዬ የተባሉት የመሰረት ሙሌ የቅርብ ሰዎች በህወሓት 24ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሬጅመንት ታፍነው ተወስደው የደረሱበት አልታወቀም፡፡ የጎልማሳው አቶ ፈለቀ አጣ እንደደረሰባቸው ይታመናል፡፡ ደርግን በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚከሰው ወያኔ የዘር ማጥፋት አየፈፀመ ይገኛል፡

Tuesday, 12 May 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ከትናንት በፊት እሁድ ግንቦት 2 2007 ዓ.ም ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ከትናንት በፊት እሁድ ግንቦት 2 2007 ዓ.ም ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና እንዲሁም የመረጃና ደህንነት ስፋትና ጥልቀት ያላቸውን ትምህርቶች በመውሰድ በብቃት የተወጡና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኘ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡
...
አርበኛ ታጋዮች በተመረቁበት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሌሎች ደርጅቶች አመራሮችና ልዩ ልዩ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ማዕዛው ጌጡ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ታጋዮች ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመመረቃቸው ታሪካዊና ልዩ እንደሆኑና ነባሩን ሰራዊት ሲቀላቀሉ ተረክበው በረሃ የወረዱበትን ታላቅ የህዝብ አደራ በማናቸውም የነፃነት ትግል ሜዳ ላይ ሙሉ በሙሉ መወጣት ስለመቻላቸው ታላቅ ዕምነት እንዳላቸውና እንዲሁም የህወሓት አገዛዝ ግብአተ መሬት መቃረቡንም ጭምር ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወታደራዊ መምሪያ ዋና ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ኮማንደር አሰፋ ማሩም በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ የህወሓት አገዛዝ ህዝባዊነትና ወታደራዊ አቅም እየተሸመደመደ በእጅጉ እየተዳከመ ባለበት ሁኔታ በተቃራኒው አርበኞች ግንቦት 7 ሰፊ የህዝብ ድጋፍ እያገኘ ወታደራዊ ጡንቻውም እየፈረጠመ የመጣ መሆኑን፤ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ አንገቱን የደፋው ህዝብ አለንላችሁ ተብሎ ቀና እንዲል የሚደረግበት ጊዜ መድረሱን እና ከእንግዲህ ወዲህ ማናቸውም ምድራዊ ኃይል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ፋጽሞ ሊያቆመው እንደማይችል ተናግረዋል፡፡


Monday, 11 May 2015

ከሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ !

ከሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ !
የስም ማጥፋት ዘመቻው ከጀመርነው ትግል ፍፁም አያንበረክከንም!
ሰሞኑን በህውሓት/ኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ባሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘመተ ያለውን የስም ማጥፋት ፕሮፓጋንዳ በአትኩሮት ሲከታተለው ቆይቷል፡፡ በዚህም የህዝብ ንብረት የሆኑ ሚዲያዎች፤ ለህዝብ አገልግሎትና በህዝብ ግብር በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚተዳደሩ የማህበረሰቡ የአገልግሎት ተቋማት ጭልጥ ብለው የሰማያዊ ፓርቲ ስም በማጉደፍ እና በማብጠልጠል ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውን በትዝብት ተመልክተናል፡፡
ሰማያዊ ከተቋቋመ ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ በደሎችን በሀገርም ሆኖ በውጪ ሲፈፀም ዝም ብሎ የመመልከት ትዕግስት ኖሮት አያውቅም፡፡ ይህ በዋነኝነት ፓርቲው የተቋቋመለት መርህ ነው፡፡ በግራዚያኒ ስም ለሚሰራ ሃውልት ተቃውሞ ለማሰማት አስፈላጊውን የህግ መስፈርት አሟልተን ባለበት ሁኔታ በገዢው ፓርቲ ትእዛዝ አባላቶቻችን ተደበደቡ፡፡ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው ኢሰብአዊ በደል ሰቆቃቸውን ለማሰማት በጠራነው ሰልፍ እንደገና በመንግስት ትእዛዝ አባላቶቻችን ላይ ድብደባና እስር ተፈጸመባቸው፡፡ በቅርብ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ ሰቅጣጭ እና በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ብሔራዊ ውርደት ሰማያዊ ፓርቲ አስቆጭቶታል፡፡ በዚህም የተነሣ እነዚህ በደሎች መድረሳቸው ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በንቃት እየተከታተለ መረጃው ለህዝብ እንዲደርስ እያደረገ ጎን ለጎን መንግስት ለወገኖቻችን የድረሱልኝ ጥሪ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ፓርቲያችን ሲያሳስብ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡
ሆኖም ይኸንን ዘግናኝ እና አረመኔያዊ ድርጊት ማውገዛችን እና መቃወማችን ከዛም አልፎ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመ ተግባር መከታተላችን ፓርቲው ሊያስመሰግነው ሲገባ ይልቁንም ገዥው ፓርቲ በተለያዩ የመንግሰት ሚዲያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ስም ለማጠልሸት ሲሯሯጡ ማየት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ብቻ ሳይሆን በህግም የሚያስጠይቅ ጭምር ነው፡፡
መንግስት ሃላፊነቱን እና ተግባሩን በመመርመር በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ብሔራዊ ውርደት ዳግመኛ እንዳይፈጸም ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ገዢው ፓርቲ ከሃገር ብሄራዊ ጥቅም ይልቅ የድርጅቱ ኢኮኖሚያዊ ትርፍ በልጦበት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ከዛም አልፎ ተርፎ ዜጎች በሀገራቸው በሚደርስባቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ ተነጋግሮ ለመፍታት ጥረት ማድረግ እየተሳናቸው በየበረሃው ሲሰደዱ የሚደርስባቸው ስቃይ አልበቃ ብሎ አይኤስ አይኤስ በሚባል አሸባሪ ቡድን የደረሰባቸውን ዘግናኝ በደል ሃዘኑ ገና ከልባችን ሳይጠፋ በሃገር ውስጥ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ የሚንቀሳቀስ ሰማያዊ ፓርቲን ከእንደዚህ አይነት ነውረኛ እና ሰይጣናዊ ተግባር ከሚፈጽመው ድርጅት ጋር ህብረት እንዳለን ለማሣየት መሞከሩ እጅግ ጸያፍና ለዜጎቹ ያለውን ንቀት ማሳያ ጭምር ነው፡፡
ሰማያዊ በዜጎቻችን ላይ ከ1ዓመት ከ6 ወር በፊት በሳውዲ አረቢያ እንዲሁም በተለያዩ አገራት አገራቸውን በመንግስት የአስተዳዳር ደካማነት በተፈጠረው ችግር ምክንያት ጥለው በመሰደዳቸው፤ ለተለያየ ችግር እና ብሔራዊ ውርደት የሚዳረጉ ወገኖቻችንን ችግር ለመፍታት ጥሪ ለመንግስት አድርገን የአንድ ሠሞን ጫጫታ ከመሆን አልፎ ለዘለቄታው ችግሩን ለመፍታት ባለመቻሉ ለዳግመኛ ዘግናኝና አረመኔያዊ ስቃይ ዜጎቻችንን መዳረጉ በገሀድ የሚታይ እውነታ ሆኗል፡፡
ስለዚህ መንግስት ሰማያዊን በመውቀስ ፋንታ ለድርጊቱ ቀጥተኛ ተጠያቂ የሆነውን የድርጊቱ ፈፃሚ አይኤስ አይኤስ ተጨባጭ አፀፋዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል አቅም እንደሌለው ጭምር አስመስክሯል፡፡ ዜጎች በሀገራቸው የሚደርስባቸው የተለያዩ ችግሮች ምክንያት እንዲሰደዱ የዳረጋቸው የተሣሣተ አመራር የያዘው ህወሓት/ኢህአዴግ መሆኑን ተረድቶ ነገ ከታሪክ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል ሰማያዊ ፓርቲ ያስገነዝባል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በአዋጅ የተሰጠውና ስልጣን ወደጎን በመተው ሰማያዊ ፓርቲ የስራ እንቅስቃሴውን ለመተለም የሚያደርገውን ተግባር በህወሓት/ኢህአዴግ እና በሌሎች የሚደረግበት ጣልቃ ገብነትን በዝምታ ማለፉ ፓርቲያችንን እጅግ ያስቆጣ ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕጋዊነት እውቅና የሰጠውን ተቋም ህወሓት/ኢህአዴግ እና ደጋፊዎች በአሸባሪነት ሲፈርጁ ምንም ለማለት አለመፈለጉ ሰማያዊ ፓርቲ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነቱ ላይ ለሚያነሳው ጥያቄ ዋንኛ ማሳያ ነው፡፡
ሰማያዊ በአገራችን ጠንካራ አማራጭ ፓርቲ እንደሆነ አምነው ከጎኑ የቁሙትን በሙሉ እያመሰገነ፤ ፓርቲው የህዝብ አማራጭነቱን ለማጥፋት በከፍተኛ ጥረት የተሰማራው ህወሓት/ኢህአዴግ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እያስጠነቀቀ፣ ህወሓት/ኢህአዴግ እየፈፀመበት ያለው የስም ማጥፋት ውንጀላ ሰማያዊ ፓርቲ ከጀመረው ትግል ፈፅሞ እንደማይገታው በፅኑ ያሳውቃል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Saturday, 9 May 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ አዲስ ድህረ ገጽ መልቀቁን ከድርጅቱ ጽ/ቤት ለማወቅ ተችሎል

May 9,2015
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ባለፉት ወራቶች ውህደት ከፈጸመ በሆላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበት ሲሆን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በአካባቢው መፈጠሩና ውጥረት መከሰቱ የሚታወቅ ሲሆን ብዙዎቹ የድል ሽታ መፍጠሩን ይስማሙበታል። ወያኔ በምንም ታምር በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን እንደማይወርድ እና በስልጣኑ የመጡበትን ሁሉ መግደል ወይም ማሰር እና ማሰደድ ላይ ያተኮረው የህወሃት ድርጅትን ብቸኛው መንገድ በሁለገብ ትግል ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አሁን ያለው ሁኔታ የሚመሰክር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይስማሙበታል።
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ይህን ትግል ከግብ ለማድረስ የጀመረውን እንቅስቃሴ በማጠነከር ረገድ ስራውን እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በርካታ ወጣቶችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ድርጅቱን መቀላቀላቸው ይታወቃል።
አዲሱ ድህረ ገጽ www.patriotg7.org ነው። እለታዊ ዜናዎችንና መረጃዎችን ዌብሳይቱን በመጎብኘት ሊያገኙ ይችላሉ።
EPPF-G7-header

www.patriotg7.org

Saturday, 2 May 2015

“ቀነኒሳ ሽሻ ቤት?” – ድህነትን በሩጫ አመለጥነው ይሄንንስ ?

 (አሌክስ አብርሃም)
ታዋቂው አትሌት ሃይለ ገብረ ስላሴ በአንድ ወቅት ባደረገው ቃለመጠይቅ እንዲህ ብሎ ነበር‹‹ ድህነትን በሩጫ አመለጥኩት!!›› ይህ ንግግሩ ሃይሌ በአንድ ጠጠር ሽ ከሚሊየን የስንፍና ወፎችን ያረገፈበት ነበር ! ሃይሌ በድህነት የሚጠራ ስማችንን በአለም ፊት የተንኮታኮተ ስማችንን በሩጫ በሰባበራቸው ሪከርዶች እንዲያገግሙ አድርጓል ! መሮጥ በወጣትነት ፈተና ከሆኑት መጥፎ ሱሶች ትውልዱን ከመታደጉም በላይ ከነሙሉ ክብሩና ስልጣኑ በድህነት መቃብር ላይ ሃይሌ የሚባል ህያው የስኬት ሃውልት እንዲቆም ሌሎችም እግር በእግር ተከትለው ከድህነትም ከታሪካዊ ጥቁር ድህነትና የርሃብ ታሪካችንም በሩጫ እንዲያመልጡ አርያ ሁኗል !!

ከእነዚህ በህይዎት እያሉ ህያው የኩራት ሃውልቶቻችን መካከል አንዱ ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ነው ! ቀነኒሳ ለእኔ በአትሌቲክሱ ዓለም ክስተት ነው ! እድል ገጥሞኝ አንዴ ሲሮጥ በአካል አይቸዋለሁ …አጃኢብ አስብሎኛል ! አሯሯጡ ከሩጫ በላይ የሆነ አርት አለው ! የአካልም የስነልቦናም ብርታቱ ለመላው አለም ወጣቶች አርዓያ የሚሆን ወጣት ጀግናችን ነበር ዛሬም ነው !! ቀነኒሳ በቀለ … ከባንዲራችን ስር የሚውለበለብ ሌላው የመልካም ታሪካችን ባንዲራ !
ከሰሞኑ ታዲያ አንድ ወሬ ሰማሁና ‹‹ ሳይቃጠል በቅጠል ›› እንዲሉ …ቀነኒሳን በአደባባይ ልወቅስ ወጣሁ ….ከዛ በፊት ግን ማጣራት ይቅደም …ጀግና ጠላቱ ብዙ ነውና የጥላት ወሬ እንዳይሆን ብየ እስካሁን ጉዳዩን አዘገየሁት …አሁን ግን ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ በሚለው ብሂላችን መሰረት ያየሁትን ልናገር ይህን ፅሁፍ እነሆ ብያለሁ !
ሲጀመር … አንድ የማይገባበት ስርቻ የሌለው ጓደኛየ የማላምነውን ወሬ ነገረኝ። “አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሺሻ ቤት ከፈተ” የሚል። እንዴት ላምነው እችላልሁ? ቀነኒሳ እኮ ነው ያለኝ ! ጭራሽ ወዳጀ ጨመረበት ‹‹ ቦሌ በሚገኘውና በስሙ በከፈተው አዲሱ ሆቴሉ ውስጥ ነው ሽሻ ቤቱ የተከፈተው›› ሲል አረዳኝ (ሳላረጋግጥ አረዳኝ አልኩኝ? አማልኝ ማለቴ ነው)። መሀላው ከወትሮው በተለየ ስለበዛብኝ ለማረጋገጥ ወሰንኩ።
በቀነኒሳ ጉዳይ ማንንም አላምንም እራሴ በዓይኔ በብረቱ ካላየሁ ትንፍሽ አልልም በቃ!! መሸት ሲል ጠብቄ ጉዱን ለማየት ቦሌ ወደሚገኘው ቀነኒሳ ሆቴል አመራሁ። ይሄ ሆቴል ሆቴል ብቻ አይደለም …የሃይሌ ቃል ግንብና መስተዋት ለብሶ በአካል የተከሰተበት ሃውልት እንጅ …‹‹ድህነትን በሩጫ ለማምለጣችን ምስክር ሊሆን በግርማ ሞገስ የቆመ ሃውልት ! አትሌቶቻችን፣ በሃይሌ ገ/ስላሴ አርአያነት፤ ዝነኛ ካደረጋቸው ሩጫ ተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቬስት በማድረግ በርካታ የስራ እድሎችን (ለህዝባቸው) እየፈጠሩ ይገኛል። ጀግናው ቀነኒሳ በቀለም በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠው፤ ስሙም በዚህ መሰል መልካም ስራዎች የሚነሳ ዝነኛ አትሌት ነው። ይሄ ሆቴል ደግሞ ላብን ጠብ አድርጎ ከሰራ ማንም የት እንደሚደርስ የሚያሳይ ማማ ነው !!
የሰማሁትን ላለማመን ስለ መልካምነቱ አብዝቼ አሰብኩ። ቀነኒሳ ሆቴል ከዚህ ቀደም ተስተናግጄ ባውቅም፤ በእንዲህ አይነቱ ሁሉን በሚታዘብ አይን አልነበረም። መግቢያው በር ላይ እንደደረስኩ “ታዛቢው” አይኔ ነገረኛ አደረገኝ። ሆቴሉ የዚህ ታላቅ ሰው ስለመሆኑ ከእንግሊዝኛና ቻይንኛ በቀር በአማርኛ የተጻፈ ምንም ነገር የለም። ቀነኒሳ ሆቴል ይላል ጽሁፉ በሁለቱም የባዕድ አገራት አፍ። ይሁን ከስራ የበለጠ ቋንቋ የለም ! ቀነኒሳ ብቻውን ብርታት የሚባል ቋንቋ ነው !! በደንቡ መሰረት ተዳብሼ (ተፈትሼ) ገባሁ። የእንግዳ መቀበያው ጠረጴዛ ጀርባ የዚህን ታላቅ ሰው ስዕል ተሰቅሎ አየሁት። መልኩ እና ግርማ ሞገሱ እንዳለ ነው። ምንአልባት ቻይንኛ ወይንም አንግሊዝኛ የማያነብ ሰው፤ ትልቁን ምስል ሲያይ ሆቴሉ የሱ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሊገምት ይችላል። እኔ ግን ከዛም በላይ አሰብኩ- ሆቴሉ የቀነኒሳ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ማንኛውም በዚህ ቤት ውስጥ ያሉትን ስራዎች ሀላፊነት ወሳጁ ራሱ መሆኑን።
እንግዲህ የሽሻዋ ነገር ሆድ ሆዴን እየቆረጠችኝ …እዚሁ የእንግዳ መቀበያ ጠረንጴዛ ላይ ((ማጨስ ክልክል መሆኑ)) በእንግሊዝኛ ተፅፎ ስመለከት ትንሽም ቢሆን የሰማሁትን ‘ሀሜት’ ላለማመን ፈለግኩኝ። አንደውም ኩራት ተሰማኝ ! ቀነኒሳ ሆቴል፤ ባለ ሰባት ፎቅ ህንጻ ሊፍቱ ላይ በተደረደሩት ቁጥሮች አወቅኩ። “ወዳጀ” ሲነግረኝ ፎቅ ላይ መሆኑን እንጂ ስንተኛ መሆኑን አጥርቼ አልጠየኩትም ነበር። ሶስተኛ ፎቅ ላይ ወርጄ አሰሳ ጀመርኩ። ሺሻ በአይን ብቻ ሳይሆን በአፍንጫም መፈለግ ስለሚቻል፤ የተዘጉ ክፍሎች ሳይቀሩ እየተጠጋው እንደ ሰላይ ስልጡን ውሻ ማሽተቴን ተያያዝኩት።
ሶስተኛውን ፎቅ በንጹህነቱ አድንቄ፤ ደረጃውን ተወጣጥቼ 4ኛ ፎቅ ደረስኩ። እስከ ስድስተኛ ፎቅ ድረስ አፍንጫዬን በርግጄ፤ ከንፈሬን አሞጥሙጬ፤ እያሸተትኩ እና ከግራ ቀኝ፣ ጫፍ እስከ ጫፍ ከንቱ “ስለላዬን” ባካሂድም ይብስ ብሎ የክፍሎቹ መልካም ጠረን አስደሰተኝ። “እገሌ”ን ለመውቀስ የቀረኝ አንድ ፎቅ ብቻ ነው። ሰባተኛው ፎቅ ላይ ደረስኩ። በጭራሽ ውሸት እንደሰማው ተረዳሁ። ምንም ነገር የለም። ስለምን በቀነኒሳ ላይ እንዲህ አይነት ወሬ በሀሰት አወራልኝ ብዬ ምክንያቱን መመራመር ያዝኩ። ይሄ የወሬ ባህላችን መቸ ይሆን የሚለቀን እያልኩ !! ቀነኒሳን በክፉ በመጠርጠሬ ‹‹አፉ በለኝ›› ልል በልቤ እየከጀልኩ !
ወደ መጣሁበት ለመመለስ ሊፍቱ ጋር ስጠጋ፤ አንድ ወጣት ፊት ለፊት ወንበር ዘርግቶ ተቀምጦ አስተዋልኩ። ምን ሊሰራ ይሆን ወጭ ወራጁን ተቀምጦ የሚያየው ስል ለራሴ ጠየኩና፤ ልቅ፣ ደፋር ሆንኩኝ። “ነፍሴ… ሺሻ ቤቱ የቱ ጋር ነው? ሰው ቀጥሮኝ ነበር” አልኩት። ከተቀመጠበት ተነስቶ በትህትና እየተሸቆጠቆጠ ሸሸግ ያለችውን የሰባተኛ ቅጥያ ፎቅ መግቢያ ጠቆመኝ። ለማመላከት የተቀመጠ ነው መሰለኝ “ስራ የተፈጠረለት” ይህ ወጣት። ከተቀመጠበት አጠገብ ያለው ግርግዳ በስፖንጅ የተለበጠ ድምጽ ማፈኛ ከለላ ተሰርቶለታል። ከቅጥያ ሰቀላዋ ከሚመጣው የሙዚቃ ድምጽ ለክፍል እንግዶች ጸጥታ ጥንቃቄ መሆኑ ነው። ጨለማ የወረሰውን ደረጃ ወጥቼ ሙዚቃ ታፍኖ የሚሰማኝ ክፍል ጋር ስደርስ በሩ የትኛው መሆኑ ግራ ገባኝ። አገኘሁት። ወደ ውስጥ ገባሁ።
በዘመናዊና ባህላዊ መካከል የሚገኝ ጥቁር አጭር ጉርድ ቀሚስ መሀሉን ጥንታዊው የጥበብ መስቀል የተጋደመበትን ልብስ የለበሱ የሚያማምሩ ሴት አስተናጋጆች ውር ውር ሲሉ ሳይ የት ነው እንዴ ያለሁት?… አልኩኝ። ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ ሆቴል። የተነገረኝን “ሀሜት” እውነትነት ለማረጋገጥ አሁን ካለሁበት ሰወር ወዳለው ክፍል መዝለቅ ነበረብኝ። በደመ ነድሴ እና ልምድ ባካበተው አፍንጫዬ ተመርቼ ገባሁ። እውነትም ሺሻ ቤት ውስጥ ገብቻለሁ። እያንዳንዱ የቡድን መስተናገጃ ክፍልፋይ በብራማ ክር መሳይ የጌጥ ገመዶች በስሱ ተጋርዶ፤ በውስጡ በርካታ ተስተናጋጆች በሙዚቃ ታጅበው ሺሻውን ያንዶቆዱቁታል። የሰማሁት ነገር እውነት መሆኑን ባይኔ በብረቱ፤ ባፍንጫዬ ባነፍናፊው፤ በጆሮዬ በቅስሩ፤ አረጋገጥኩ። “ስራ የተፈጠረላቸው ወጣቶች” ከሰል ሲያቀጣጥሉ፤ ባለ አጭር ቀሚሶቹ ደግሞ በፈገግታ ያስተናግዳሉ።
በመጠኑም ቢሆን ለትዝብት ያህል ተቀምጬ፤ እዚህም እዚያም የሚብሎቀለቀው ሺሻ ጠረኑ ስላልተስማማኝ በፍጥነት “ቀነኒሳ ሺሻ ቤት”ን ለቅቄ ወጣው። ቀነኒሳ ግን በሀገራችን ከሱ ውጪ ሳንባ ያለው ሰው እንዲኖር አይፈልግም እንዴ?…እንደው ድህነቱ ቢቀር ሽሻውን በሩጫ ለማምለጥ ወደሊፈቱ መሮጥ አማረኝ !! ወደኋላየ ገልመጥ እያልኩና ‹‹አልሆንልህ አለኝ ማመን ›› እያለኩ… መቸስ ይህን ስራ ባለቤቱ ሳያውቀው ይከናወናል ማለት ይከብዳል ቢሆንም ግን … በየጉዳንጉዱ በሰሌንና ችፕውድ ተከልለው ሽሻ ከሚጨስባቸው ቤቶች የተሰበሰበ እቃ ፖሊስ ‹‹አቃጠልኩ›› እያለ እኛም ‹‹አበጀህ ›› እያልን የኖርን ህዝቦች …ይሄ ትውልድን ገዳይ ቆሻሻ ሱስ የሰው አናት ላይ መውጣቱ ሲገርመን እንዲህ ህንፃው አናት ላይ ያውም ከነፍሳችን የምናደንቀው ብርቅየ አትሌታችን የከፈተው ሆቴል ህንፃ ላይ መውጣቱ አሳዝኖናል !!
ለአትሌታችን ያለን አክብሮት እንዳለ ሁኖ ይህን ድርጊት ግን ‹‹አይጠበቅም›› እንላለን !!
እንዲህ በስራቸው በአለም ፊት ያስጠሩን ታላላቅ ሰዎቻችን ለትውልዱ አርአያ ካልሆኑ …እሽ ማነው ለዚህ ህዝብ ከልቡ የሚያዝነው የሚቆረቆረው ?? እንኳን ጓዳቸው ውስጥ ሲፈፀም በዝምታ ማለፍ በምድራችን ላይም ይህ ነገር ድራሹ እንዲጠፋ በገንዘብ በዝናቸውና በሃሳብ ሊፋለሙት ይገባ ነበርኮ ! በድርጊቱ አዝኛለሁ እንደሚስተካከልም አምናለሁ !
ፀያፍ ነገርን የሚፈፀምበት ቦታ ታላቅነት ንፁህ ሊያደርገው አይችልም !! ጨረስኩ !

አውነቱ ይውጣ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ሴቶችን በወንዶች ፊት፣ ወንዶችን በሴቶች ፊት ልብስ እያስወለቁ የአካላቸውን ክፍሎች ሁሉ ለማየት የሚያስችል አንቅስቃሴ አንዲሠሩ ማስገደድ በሽተኞችን ያስደስታል፤ የምርመራ ዘዴ ግን አይደለም፤ ውርደት እንዲሰማቸው ከሆነ በወራዶች ሰዎች ፊት የምን መዋረድ አለ? ወራዶች እነሱ ደረጃ ላይ ከእነሱ ጋር ያስተካክላሉ አንጂ አያዋርዱም፤ በሌላ አነጋገር ወራዶች አያዋርዱም፤ ወራዶቹ ደንቆሮዎችም ሆነው ነው እንጂ ልብስ የሚያስወልቁ እነሱ ብቻ አይደሉም፤ ሀኪሞችም ልብስ አስወልቀው፣ አጋድመው በጣታቸውም ሆነ በመሣሪያ የፈለጉትን የአካል ክፍል አንደፈለጉ ያደርጉታል፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ከሚያደርጉት የሀኪሞቹ የሚለየው ሀኪሞቹ ሰዎችን ለማዳን ሲሉ ነው፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ግን የራሳቸውን ሱስ ለማርካት፣ የራሳቸውን ህመም ለማስታገስ ነው፤ 
ወራዶቹንና ደንቆሮዎቹን ከመለዮአቸው አራቁቻቸዋለሁ! ከነውር በቃላት ወደነውር በተግባር፣ ያውም በመሥሪያ ቤት! ዱሮ ዱሮ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር ፊት ለፊት የአንድ ኢጣልያዊ ቡና ቤት ነበር፤ እዚያ ውጭ ተቀምጠን ቡና ስንጠጣ አንዲት ውብ ሴት ወደጸጉር መሥሪያው ቤት ስትመጣ የሁላችንም ዓይኖች እየዘለሉ እስዋ ላይ ዐረፉ፤ ከሦስታችን አንዱ ስለሴትዮዋ የወሲብ ችሎታ በዝርዝር መናገር ሲጀምር ሁለታችን ተያየንና አፈርን፤ ጨዋታው የጣመለት መስሎት ሲቀጥል የሕግ ባለሙያ የሆነ ጓደኛዬ አቋረጠውና ‹‹ስማ! ይህን ጊዜ እናትህ በአንድ ቦታ ስታልፍ አንዱ እንዳንተ ያለ ስለስዋ ችሎታ ያወራ ይሆናል!›› አለው፤ ሊጠጣ ወደአፉ ያስጠጋውን ስኒ ቁጭ አደረገና ተነሥቶ ሄደ፡፡
ሥልጣን ተሰጥቷቸው ሴቶችን ልብስ እያስወለቁ ምርመራ ነው የሚሉ በእናቶቻቸውና በእኅቶቻቸው ላይ ሊደርስ እንደሚችል አይገነዘቡም ይሆናል፤ ደንቆሮ የሚያደርጋቸውም ይኸው ነው፤ የአንዱ እናት አንድ ቦታ ላይ ራቁትዋን ቆማ በሽተኞች ተሰብስበው ሲስቁባት፣ በሌላ ቦታ ደግሞ ጓደኛው የእሱን እናት ወይም እኅት ያንኑ እያደረገ ያስቅባት ይሆናል፤ አንተ በእኔ እናትና በእኔ አኅት አስቅባቸው፤ እኔ ደግሞ በአንተ እናትና በአንተ እኅት አስቅባቸዋለሁ፤ ይህንን እየሠራን ኑሮአችንን እናቃናለን፤ እቤታቸው ሲገቡና ከእናቶቻቸውና ከእኅቶቻቸው ጋር ሲቀመጡና ሲበሉ (?!) ሰው ይመስላሉ፤ እነዚያም ግፉ የተፈጸመባቸው እናቶችና እኅቶች ‹ነውራቸውን› ምሥጢር አድርገው ለሰው ስለማይናገሩ ግፈኞችና የግፍ ሰለባዎች አብረው ይበላሉ!
አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳንድ ሴቶች የደረሰባቸውን ተናገሩ፤ አሁን ያፍራሉ የተባሉት እውነቱን ራቁቱን አወጡትና ከእፍረት ነጻ ወጡ! እውነቱ ሲወጣ የሚያፍረው ማን ነው? ደካማዎቹና የግፍ ሰለባ የነበሩት በጭራሽ አያፍሩም፤ የሚያፍሩት ግፈኞቹ ናቸው፤ የሚያፍሩት የሕዝብን አደራ በማቆሸሻቸው፣ በሥልጣን በመባለጋቸው፣ የሕዝብንና የአገርን ክብር በማዋረዳቸው ያፍራሉ፤ ኅሊናቸው በየቀኑ ነፍሳቸውን አርባ ሲገርፋት እየሳሳች እንቅልፍ ትነሳቸዋለች፡፡
ለመሆኑ በአገሩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት — ሼሆች፣ ሽማግሌዎች በአገሩ የለንም?
መስፍን ወልደ ማርያም

ደህንነቶች የወይንሸትን ቤት ሲፈትሹ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ባንዲራ በማግኘታቸው የብሄር/ብሄረሰቦችን መብት አትቀበይም ብለው ከሰሷት

ደህንነቶች የወይንሸትን ቤት ሲፈትሹ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ባንዲራ በማግኘታቸው የብሄር/ብሄረሰቦችን መብት አትቀበይም ብለው ከሰሷት

ኢትዮጲያ ባንዲራ ቀለሙ ምን አይነት ነው›› ለሚለው ጥያቂያቸው ‹‹አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ከዚህ ውጪ ሌላ አላውቅም›› ብላ በማለቷ ፈርሚ ብለው አስፈርመዋታል........ እነርሱ ሀፍረተቢስ ናቸው በሚቀጥለው ችሎት ደግሞ ከሁከት እና አመፅ ማነሳሳት ጎን ለጎን ‹‹የኢትዮጵያን ባንዲራ ባለመቀበል›› ብለውም ይከሷት ይሆናል፡፡ ወይ ዘመን፡፡
አሳሳቢው ጉዳይ የጤንነቷ ነገር ነው..... ከጥቂት ቀናት በፊት ጤና ጣቢያ ወስደዋት ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ሪፈር የፃፈላት ቢሆንም ፖሊስ ተብዬዎቹ ሊወስዷት ግን ፍቃደኞች አይደሉም፡፡ እንኳን ወደ ሆስፒታል እንድትሄድ ሊያደርጉ ቀርቶ የጤና ጣቢያው ሀኪም ያዘዘላትን መድሀኒት ራሳቸው ጋር በማስቀመጥ ጠፋብን ብለው ይኸው መድሀኒቱን ከወሰደች ሁለት ቀን አለፋት፡፡ ከውጪም መድሀኒቱን ማስገባት ከልክለዋል፡፡ ወይ ነዶ፡፡
የፌስቡክ ፓስወርዳችሁን ካልሰጣችሁ እያሉ የሚደበድቡት አንሷቸው ህክምና መከልከል አሁን ምን ይባላል?