ቴዎድሮስ አስፋው በድጋሜ ዋስትና ተከለከለ
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ግድያ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስሮ በ6 ሺህ ብር ዋስትና ከወጣ በኋላ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ያሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው በድጋሜ ዋስትና ተከልክሏል፡፡ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ቴዎድሮስን ካሰረው በኋላ ፍርድ ቤት አቅርቦ ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ አሰጥቶበት የነበረ ቢሆንም ቀጠሮው ከተሰጠ በኋላ ለፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ ተከሳሹ ከሀገር ሊወጣ እንደሚችል በመግለጽ ከቀጠሮው በፊት በሰበር ከታየ በኋላ በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ተጠይቋል፡፡
ይህንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ‹‹ተከሳሾቹ የዋስትና ግዴታቸውን እንደማይወጡ ግምት በመውሰድ ቀድመው ያስያዙትን ዋስትና ቀሪ በማድረግ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥ›› ሲል ጠይቋል፡፡ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ካሰረው በኋላ ቴዎድሮስ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበር ሲሆን አሁን ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲዛወር ተደርጓል፡፡
No comments:
Post a Comment