Saturday, 14 June 2014

በግንደ በረት ፍጥጫው ቀጥሏል
በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በምትገኘው የግንደ በረት ከተማ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ እስካሁኑ ሰአት ድረስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በ7 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሧል::

Monday, 9 June 2014


የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ጁን 8, 2014 በኦስሎ ከተማ የሻማ ማብራት ስነስርአት ተደረገ ።


በምርጫ 97 በወያኔ አጋዚ ጦር በግፍ ለተገደሉ ዜጎቻችንን ለማስታወስ በዛሪዉ እለት ጁን 8, 2014 በኦስሎ ከተማ የሻማ ማብራት ስነስርአት ተደረገ ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ይህንን የሻማ ማብራት ያዘጋጀበት ዋናው አላማ በምርጫ 97 የዲሞክራሲ ጥያቄ ባነሱና ንጹሀን ዜጎቻችን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነው። ዝግጅቱ በግፍ በወያኔ ታጣቂዎች ደረትና ግንባራቸውን ተብለው ለተገደሉ ንፁሃን ወገኖቻችን በማስብ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ኀላፊ የህሊና ፀሎት በማሰድረግ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ 97ትን አስመልክቶ ሰፋ ያለ የመግቢያ ንግግር አድርገዋል እደዚሁም የኢትዮጵያ ማህበር በኖርዌ ሊቀመንበርም አጠር ያለ መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶችም በምርጫ 97 ወቅት የነበረውን የግፍ ግድያ አስመልክቶ በየተራ መልክቶቻቸውን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም በምርጫ 97 በግፍ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን አስመልክቶ አጭር በፊልም የተደገፈ ምስል ቀርቧል። በዝግጅቱ ላይ በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ዝግጅቱ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 19፡00 ተጀምሮ 20፡30 ተጠናቋል።
የዲሞክራሲያዊ ለውጥበኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
1904209_10152452016217710_6989375044162907904_n10336607_10152452015862710_5814485053426944776_n10297590_10152452016097710_7575685381704132048_n10390432_10152452016762710_8537654287919576772_n
ኢህአዴግ በአባላቶቹ የውህደቱ ሥነ-ስርዓት እንዳይፈረም ያደረገው ሴራ ከሸፈ
************************************
አንድነትና መኢአድ የሚያደርጉትን የቅድመ ውህደት ስምምነት ከአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ክፍል ኃላፊ የዕውቅና ደብዳቤ ፓርቲዎቹ ቢጠይቁም ስብሰባ ናቸው በሚል ሰበብ በሆቴል ዝግጅቱን ማከናወን ስላልተቻለ ሆቴሎች ለፓርቲዎቹ አዳራሽ ለማከራየት በመቸገራቸው የቅድመ ውህደት ስምምነታቸውን በመኢአድ አዳራሽ ሊያደርጉ ተገደዋል፡፡ ትብብር፣ቅንጅትና ግምባር በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ተፈትኖ እንደማይሰራ ተደጋግሞ በሚነገርበት ወቅት ሁለቱ ፓርቲዎች በአንድነት ለመስራት የሚያስችላቸውን የቅድመ ውህደት ስምምነት በመፈራረም መተባበር መተባበር ብቻ እንደሚገባ የፓርቲዎቹ አመራሮች ገልጸዋል፡፡
በተናጠል በሚደረግ ትግል ሁልግዜም ተጠቃሚ የሚሆነው የገዢው ፓርቲ እንደሆነ ከዚህ ቀደም የነበሩ ክስተቶችን መለስ ብሎ መመለከት ተገቢ ነው፡፡ በአንድ የምርጫ ጣቢያ በተለያዩ ስሞች ተቃዋሚዎች እየተወዳደሩ አስተኛ ድምጽ የሚያገኘው ኢህአዴግ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት እንቆቅልሽ እንዲፈታና የሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት ሌሎችም ሊከተሉት እደሚገባቸው በፊርማው ሥነ- ስርዓት በሁለቱ ፓርቲ መሪዎች ተገልጧል፡፡