Tuesday, 29 April 2014

በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የእስር እርምጃ እንዳሣሰበው ሲ.ፒ.ጄ ገለጸ።
ኢሳት ዜና :-ዓለማቀፉ የጋሴጠኞች ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ) ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን በ9 ጸሀፍያን ላይ የወሰደው የእስር እርምጃ፤ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ከተቃጡ የከፉ እርምጃዎች አንዱ ነው ብሏል።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን መግለጽን እንደወንጀል እየቆጠሩት ነው” በማለት ነው -የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪቃ ወኪል-ቶም ሩድስ-እርምጃውን የኮነኑት።





እሁድ ዕለት የመንግስት አቃቤ ህግ በ አዲስ ጉዳይ ዋና አዘጋጅ በ አስማማው ሀይለጊዮርጊስ፣ በፍሪላንስ ጋዜጠኞቹ በተስፋለም ወልደየስ እና በ ኤዶም ካሣዬ፣ እንዲሁም በጦማርያኑ በ አቤል ዋቤላ፣በ አጥናፍ ብርሀኔ፣በማህሌት ፋንታሁን፣ በዘላለም ክብረት እና ...በበፈቃዱ ሀይሉ ላይ ከውጪ ድርጅቶች ጋር ይሠራሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀምም በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ይንቀሳቀሳሉ.. የሚል ክስ እንደመሰረተባቸው ሲፒጄ አውስቷል።
ተስፋለም፣አስማማውና ዘላለም ለፊታችን ሚያዚያ 28 ቀሪዎቹ ደግሞ ለሚያዚያ 29 እንደተቀጠሩ ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የደረሰውን መረጃ ዋቢ አድርጎ የጠቀሰው ሲፒጄ፤ በታሳሪዎቹ ላይ እስካሁን መደበኛ ክስ እንዳልተመሰረተ ጠቁሟል።
ሲፒጄ በመግለጫው-ፀሀፊዎቹ ዞን ዘጠኝ ተብሎ የሚጠራ የገለልተኛ አክቲቪስቶች ስብስብ አባል ሆነው የተለያዩ ዜናዎችንና ጽሑፎችን ይጽፉ እንደነበር አመልክቷል።
“ዞን ሰጠኝ የተሰኘው ስያሜ ከቃሊቲ የተገኘ መሆኑና የጸሐፊዎቹ መሪ ቃል፦”ስለሚያገባን እንጦምራለን” የሚል መሆኑ በሲፒጄ መግለጫ ተመልክቷል።
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከደህንነቶች በሚደርስባቸው ወከባ ምክንያት ላለፉት ሰባት ወራት ዘግተውት የቆዩትን የፌስቡክ ገፃቸውን ዳግም በከፈቱ ማግስት መሆኑን እንደተረዳም የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ተቋሙ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ፦”የታሰሩት ጋዜጠኞች አይደሉም፤ እስሩ ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር የተገናኘ አይደለም። ከከባድ ወንጀል ጋር የተገናኘ ነው” ማለታቸውን ሲ.ፒ.ጄ ጠቁሟል።
“በጋዜጠኝነት ወይም ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ የቃጣነው በትር የለም። ሆኖም ማንም ቢሆን ሙያውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ለመፈፀም ሲሞክር በህግ ይጠየቃል” ሲሉም አክለዋል-አቶ ጌታቸው ረዳ።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደለየለት ፈላጪ ቆራጭ አገዛዝ ማዘንበላቸውን እንዲገቱና በሀገሪቱ ነፃ ሀሳቦች ይንሸራሸሩ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል-ሚስተር ቶም ሩድስ።
የታሰሩት 9ኙም ጸሀፊዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ድርጅቶችም የ ኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጦማርያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የወሰዱትን እርምጃ በማውገዝ ፤ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡት የ አሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ እስረኞቹን እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
የተለያዩ ዓለማቀፍ የሚዲያ ተቋማትም ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በ9ኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደውን የማሰር እርምጃ ሽፋን ሰጥተውታል።
ከሚዲያ ተቋማቱ መካከል ኤ.ቢ.ሲ ኒውስ፣ ሲ ኤን.ኤን፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ሬውተርስ፣ እና አልጀዚራ ይገኙበታል።
እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በጉብኝታቸው ስለታሰሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አጠንክረው እንደተናገሩ የኒውዮርክ ታይምሱ ታዋቂ አምደኛ ኒኮላስ ክሪስቶች ለሰጣቸው አስተያዬት፤ “ በጣም ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ዩናይትድስቴትስ በመላው ዓለም ላይ የፕሬስ ነፃነትን በመደገፍና ከጥቃት በመከላከል ባላት ጠንካራ አቋም ትቆያለች” በማለት ምላሽ ሰጥተውታል።

Monday, 28 April 2014



በአዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ዮናስ ከድር የዩኒቨርስቲ ፈተናውን እንዳይፈተን በፖሊስ ተከለከለ::
ዮናስ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከሌሎች የፓርቲው አባላት ጋር በቅስቀሳ ላይ እያለ ባሳለፍነው ሳምንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ፈተና እንዳለበትና በፖሊስ ታጅቦ ሄዶ መፈተን ህጋዊ መብቱ መሆኑን ለፖሊስ ቢገልፅም እንዳይፈተን ተወስኖበታል::
በአንድ ወቅት ፕ/ር መስፍንን ሳዋራቸው ስለ ትምህርት እንዲህ ብለውኝ ነበር
"በመማሬ ካገኘሁት ጥቅም መካከል ዋነኛው የኢህአዴግ አባል ከመሆን መዳን ሲሆን ያጋጠመኝ ደግሞ እስር ነው"
ልክ ብለዋል ፕ/ር የምሁር ቤቱ በመሀይማን በሚመራው እስር ቤት ነው

Friday, 25 April 2014

ስድስት የዞን 9 ጦማርያን በመንግሥት ተያዙ




ዛሬ አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ ይህንኑ ዜና ይፋ ያደረገው የጦማሪያኑ የፌስቡክ ገጽ ሲሆን፤ ታሳሪዎቹን ለመያዝ የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን መስማታቸውን በዚሁ አጭር መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።
ከሰአታት በፊት በወጣው መግለጫ፣ ““ዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 15፣2006 በዋጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እነዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ፡፡” በማለት ያትታል።
በተያያዘ ዜና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስም ዛሬ በፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መግባቱም ተዘግቧል።
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በመንግስት በኩል የተሰጠ ምንም አይነት ማብራሪያ የለም።

Sunday, 6 April 2014

ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም! (ግንቦት7) April 5, 2014
Ginbot 7 weekly editorialየወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።
ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።
ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።
እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።
ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።
ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።
ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
አንድነት ፓርቲ በደሴ የተሳካ ሰላማዊ ሰልፍ አደረገ።


"እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን !!! ” የደሴ ነዋሪዎች...
የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ ታውቋል።
ከቅስቀሳ ጀምሮ በደህንነቶች እና በፖሊስ ሃይሎች ወከባ እና መንግስታዊ ውንብድና የተደረገበት የደሴው ሰልፍ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ለመብቱ እና ለነጻነት ያለውን ቀናኢነት በማሳየት ትልቅ ትብብር አድርግዋል። በደሴ ከተማ በዛሬው እለት የተደረገው ሰልፍ ከጠዋት ጀምሮ ህዝቡ ፍርሃቱን በመስበር ወደ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ያሰማ ሲሆን ፖሊሶች መንገድ በመዝጋት ሽብር ለመፍጠር ቢሞክሩም ህዝቡ እያሳበረ በሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞውን አሰምቷል።

ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ መፈክሮች ደምቆ ነበር።ህዝቡ አንግቦት ክንበሩት መፈክሮች ውስጥ ፦
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ - አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ - መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን - ድል የህዝብ ነው - በግፍ የታሰሩ ይፈቱ ......... የሚሉ ይገኙበታል።
የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ቀበና ሼል አከባቢ የሚገኘውን የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በመክበብ ወከባ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።
በደሴው ሰላማው ሰላፍ ላይ የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንቱ አቶ ተክሌ በቀለ እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ሃላፊው ዘለቅ ረዲ የደሴ የአንድነት ሰብሳቢ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ


UDJ party demonstration in Dese

Friday, 4 April 2014

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫ          

ETH J
ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።
በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራው ይህ ቡድን ከ March 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።  ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።
ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል።  የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣  በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።
በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱ መብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች እዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ለመረዳት ችለናል።
ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።
አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።  ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።
በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽ ግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆች እንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Wednesday, 2 April 2014

ዜና በትንሽ ጨዋታ፤ ፍቅር ይልቃል ከኢቲቪ ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ!


ዜና በትንሽ ጨዋታ፤ ፍቅር ይልቃል ከኢቲቪ ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ!
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስፖርት ፕሮግራም አዝጋጅ እና ስፖርት ዜና አንባቢነት የሚታወቀው ወዳጃችን ፍቅር ይልቃል ላለፉት ሶስት አመታት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ምክትል ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የመዝናኛ ክፈሉ ደግሞ ዋና ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ ቆይቶ ነበር።
ፍቅር ዛሬ ከታድያስ አዲስ ጋር ባደረገው ቆይታ እንዳረጋገጠው በራሱ ጠያቂነት ከሁለቱም ስልጣኖቼ አንሱኝ ብሎ ጠይቆ ኢቲቪም “ካልክ እሺ” ብሎ ከሃላፊነቱ ሊያነሳው ተስማምቷል።
(እዝችጋ ትንሽ ፉገራ ትምጣ፤ ፍቅር ስልጣኑ ይቅርብኝ ያስባለው ምን እንደሆነ ሲያብራራ የስራ መደራረቡ ያመጣበት ህመም መሆኑን ገልጿል ባለፈው ጊዜ ጠቅላያችን በታመሙበት ወቅት አቶ በረከት የህመማቸው መንስኤ ምንድነው ሲባሉ፤ የስራ መደራረብ መሆኑን ነግረውን ነበር። ያው ሀመም በርተቶ ለሞት ዳርጓቸው፤ (ዳንኤል ብርሃኔ እንደነገረን ያለ ሃይማኖታቸው ስላሴ ጓሮ እንዲጠቃለሉ አድርጓቸዋል።) ታድያ እኔ የምለው እንዴት ነው መንግስታችን የሚሾማቸው ሁሉ ለህምም የሚዳርጉ ከሆነ እየተዳደርን ያለነው ፍቃድ መውሰድ በተሳናቸው ህመምተኞች ነው ለማለት ያስደፍር ይሆን…)
ለማንኛወም ወድ ዜናችን ስንመለስ፤ ሰይፉ ፋንታሁን ፍቅር ስልጣኑን የሚለቀው ሰው ለሰው ድራማ እና ኢቲቪ በገጠሙት ውዝግብ ይሆንን ብሎ ጠይቆት ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል በፍጹም ብሎ መልሷል። በተጨማሪም ጋዜጠኛው ክዚህ በኋላ በኢቲቪ ስፖርት ዜናዎች ላይ እናየው ይሆን የሚለውን የተጠየቀው ፍቅር በስፖት ዜናዎች ላይ ለመታየት ፍላጎቱ መሆኑን ሲናገር ሰምቻለሁ።
ወዳጃችን ፍቅር ከህመሙ እንዲበረታ ዱዓ የማደርግ መሆኔን እገልጻለሁ!