Wednesday, 2 April 2014

ዜና በትንሽ ጨዋታ፤ ፍቅር ይልቃል ከኢቲቪ ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ!


ዜና በትንሽ ጨዋታ፤ ፍቅር ይልቃል ከኢቲቪ ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ!
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስፖርት ፕሮግራም አዝጋጅ እና ስፖርት ዜና አንባቢነት የሚታወቀው ወዳጃችን ፍቅር ይልቃል ላለፉት ሶስት አመታት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ምክትል ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የመዝናኛ ክፈሉ ደግሞ ዋና ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ ቆይቶ ነበር።
ፍቅር ዛሬ ከታድያስ አዲስ ጋር ባደረገው ቆይታ እንዳረጋገጠው በራሱ ጠያቂነት ከሁለቱም ስልጣኖቼ አንሱኝ ብሎ ጠይቆ ኢቲቪም “ካልክ እሺ” ብሎ ከሃላፊነቱ ሊያነሳው ተስማምቷል።
(እዝችጋ ትንሽ ፉገራ ትምጣ፤ ፍቅር ስልጣኑ ይቅርብኝ ያስባለው ምን እንደሆነ ሲያብራራ የስራ መደራረቡ ያመጣበት ህመም መሆኑን ገልጿል ባለፈው ጊዜ ጠቅላያችን በታመሙበት ወቅት አቶ በረከት የህመማቸው መንስኤ ምንድነው ሲባሉ፤ የስራ መደራረብ መሆኑን ነግረውን ነበር። ያው ሀመም በርተቶ ለሞት ዳርጓቸው፤ (ዳንኤል ብርሃኔ እንደነገረን ያለ ሃይማኖታቸው ስላሴ ጓሮ እንዲጠቃለሉ አድርጓቸዋል።) ታድያ እኔ የምለው እንዴት ነው መንግስታችን የሚሾማቸው ሁሉ ለህምም የሚዳርጉ ከሆነ እየተዳደርን ያለነው ፍቃድ መውሰድ በተሳናቸው ህመምተኞች ነው ለማለት ያስደፍር ይሆን…)
ለማንኛወም ወድ ዜናችን ስንመለስ፤ ሰይፉ ፋንታሁን ፍቅር ስልጣኑን የሚለቀው ሰው ለሰው ድራማ እና ኢቲቪ በገጠሙት ውዝግብ ይሆንን ብሎ ጠይቆት ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል በፍጹም ብሎ መልሷል። በተጨማሪም ጋዜጠኛው ክዚህ በኋላ በኢቲቪ ስፖርት ዜናዎች ላይ እናየው ይሆን የሚለውን የተጠየቀው ፍቅር በስፖት ዜናዎች ላይ ለመታየት ፍላጎቱ መሆኑን ሲናገር ሰምቻለሁ።
ወዳጃችን ፍቅር ከህመሙ እንዲበረታ ዱዓ የማደርግ መሆኔን እገልጻለሁ!

No comments:

Post a Comment