Tuesday, 29 December 2015

ስብአዊነት ከጎስኝነት ይቅደም (ኦባንግ ሜቶ)

እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን ከጎሳ ይልቅ ሰብአዊነት ቅድሚያ መስጠት አለብን፡ ታላቅ ህዝብና የታላቅ ሃገር ባለቤት መሆን የምንችለው በዚህ ብቻ ነው።
ይህን ለማሳካት የመጀመሪያው ትልም እግዚአብሄር አንተን እንደሚወድህና እንደሚቀበልህ ሁሉ አንተም ራስን መውደድ፤ ራስን ማክበርና የራስን ማንነትን በጸጋ መቀበል ነው፤ ይህም በተሻለ መልኩ ቤተሰብህን፤ አካባቢህን፤ የየወጣህበትን ማህበረሰብ፤ ሃገርህንና ማንኛውንም ሰብአዊ ፍጡር ለመውደድና ለመንከባከብ ያስችልሃል፡
ህወሃት የተዘራውንና በሃገራችን ተንሰራፍቶ ያለውን ይህንን ሁሉ የዘር ጥላቻ፤ ኢፍትሃዊነት በአንድ መሳሪያ ብቻ ማሸነፍ እንችላለን፡፡ይህም መሳሪያ ፍቅር ነው።
የዚህን ጽነሰ ሃሳብ የማይረዱ፤ ይልቁንም የነሱ ህልውና የሚወሰነው ለግል ጥቅማቸው ሌላውን በመጫንና በመደፍጠጥ፤ ባዶ ልባቸውንና መንፈሳቸውን በቁሳቁስ ለመሙላት የሚፈልጉ እንዳሉ መረዳት ያስፈልጋል። ባዶነታቸውን ይሞላልናል ያሉት ቁሳቁስ ግን በፍጹም እርካታን አይሰጣቸው። እኛ ግን ጥሪያችን እግዚአብሄርንና ሌሎችን ራሳችንን የምንወደውን ያህል መውደድ ነው።
ወደፊትስ፤ ለራሳችን ብቻ እናለቅሳለን ወይስ የሌሎችንም ሃዝን ተካፋይ ሆነን የሰቃያቸው ምንጭ የሚደርቅበትን መንገድ ለመፈለግ ከጎናቸው እንሰለፋለን?
በኔ እምነት እያንዳንዳችንን ነጣጥሎ የሚያጠቃንንና የሚረጋግጠንን ዘረኛውን የህወሃት አፓርታይድ ስርዓት ማስቆም የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
ለዚህም ህዝቦች ወደ አንድ መምጣት አለብን፤ እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፡ ኢትዮጵያ የሚጎላት ይህ ነው፡ አፍሪቃን የሚርባት ይህ ነው። (ኦባንግ ሜቶ)

በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬#MinilikSalsawi # Oromo
በወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የታጠቁ የወያኔ ወታደሮች ግቢያችንን ለቀው ይውጡልን ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ጥያቄያቸውን ተሰሚነት ባለማግኘቱ ተጨማሪ ወታደሮች በግቢው ውስጥ ገብተው ተማሪዎችን ሲያባርሩ ሲደበድቡ እና ሲይዙ ተስተውሏል:: በርካታ ተማሪዎች ክፍኛ መጎዳታቸውን እና አንቡላንሶች ሲመላለሱ ነበር ተማሪዎች የዩንቨርስቲውን ግቢ በመልቀቅ ወደየቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ይገኛሉ:: ተቃውሞ በሚካሄድባቸው
አከባቢዎች ኦሮሚኛ ተናጋሪ ያልሆኑ እና ስለ አከባቢው ምንም አይነት እውቀቱ የሌላቸው ወታደሮች በየአከባቢው እየሰፈሩ ይገኛሉ::
እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ሂዳቡ አቦቴ ከተማ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ::በዚሁ ሰሜን ሸዋ ቱሉ ሚልኪ የወያኔ ወታደሮች የእርዳታ
ድርጅቶችን መኪና በመጠቀም ቤት ለቤት እየዞሩ ወጣቱ በማፈስ ላይ ይገኛሉ::በተጨማሪም በባሌ አጋርፋ ዳግም ተቃውሞ ተቀስቅሷል::በሰበታ
መምሕር እና ደራሲ የሆነው ለሚ ግርማ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነ ሲሆን ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል::ተቃውሞውን ወያኔ በቁጥጥር ስር አአዋልኩት ቢልም ከቀድሞውበበለጠ ሁኔታ ተፋፍሞ ቀጥሏል:: # ምንሊክሳልሳዊ

በጋራ ከማልቀስ፣ በጋራ መታገል

በጋራ ከማልቀስ፣ በጋራ መታገል
በአበበ ገላው
ከ66ቱ አብዮት ወሳኝ ትምህርት መቅሰም አለብን። የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች መሬት ላራሹ እና ዳቦ ለተራበው ነበሩ። የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት አልባ አድርጎ ሲያስገብር የነበረው ፊውዳላዊ ስርአት የተንኮታኮተው እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመነሳታቸው ብቻ አልነበረም። ኢትዮጵያውያን ሁሉ በገዥዎችና በተገዢው ጭቁን ህዝብ ያለውን የመደብ ትግል ተረድተው ከዳር እስከዳር በአንድነት መነቃነቅ በመቻላቸው ነበር።
በርግጥ ያለመታደል ሆኖ ያ ህዝባዊ አብዮት በወታደራዊ ሃይል ተቀልብሶ ሌላ አስከፊ አንባገነናዊ ስርአት ተተካ።ከዛ ዘመን በከፋ መልኩ ዛሬ የኢዮጵያን ህዝብ ከመሬቱና ከቀዬው እያፈናቀለ በረሃብ የቀፈደደውን የህዝብ ደም እየመጠጠ በዘር ከፋፍሎ እየቀጠቀጠና እየገደለ የሚገዛ ዘረኛ የውስጥ... ቅኝ ገዢ አስተሳሰብ ያለው የጥቂቶች ዘውጋዊ ስርአት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል እየፈጸመ ህዝብን በመግዛት ላይ ይገኛል።
ስለዚህም ነው የስርአቱ ሰለባ ሁሉ ልዩነቱን አቻችሎ በዘር ቆጠራ ላይ የተመሰረተውን የህወሃቶች ስርወ መንግስት ከስር መሰረቱ ለመጣል በጋራ መነሳትና መታገል የሚገባው። ሰሞኑን በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ አመጽም በድጋሚ ሊያስተምረን የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ ህወሃቶች የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም የማይፈጽሙት ወንጀል የለም። የህዝብ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ህዝብ በአሸባሪነት ፈረጆ ጦርነት ማወጅ የስርአቱን ቀቢጽ ተስፋነት በግልጽ አጉልቶ ያሳየ እውነታ ነው።
የህወሃቶች ስርወ መንግስት በስልጣን ላይ እስካለ ድርስ የየትኛው ህዝብ የመብትና የፍትህ፣ የእኩልነትና የነጻነት፣ የመሬትና የዳቦ ጥያቄ ፈጽሞ ሊመለስ እንደማይችል ግልጽ ነው። በመሆኑም በየአቅጣጫውና በየክልሉ የሚደረገውን ትግል ከፍ አድርጎ ብሄራዊ ንቅናቄ መጀመር የግዜው አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ከውጭም ከውስጥም በህብረት ለመታገል ሁላችንም ልዩነቶቻችንን አቻችለን በቅን ልቦና እንነሳ።
በተለይ ደግሞ አክቲቪስቶችና የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎች ለሚቀርቡላችሁ የጋራ የትግል ጥሪ ፈጣንና አወንታዊ መልስ እድትሰጡ በጭቁ ህዝባችን ስም እማጸናለሁ።
አንድነት ሃይል ነው!


Monday, 28 December 2015

ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ

ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ
አንዳንድ አካባቢዎች ተቀጣጥሎ ይገኛል
========================
ከኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም ትናንትና ዛሬ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል :: ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት አሳፍሪ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሴት ተማሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:፡

ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣

Hiber radio: ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃት በመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ፣ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ፣ ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩን ጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ ፣አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ፣የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ፣ ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙት የኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ እና ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉንhttp://www.hiberradio.com/archives/1556

የካራቶሪው ባለቤት መሬቴን ትነኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናትን አስጠነቀቁ


 በጋምቤላ 300 ሺ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ለማልማት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው የካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ
 መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ከሪፖርትር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የጋምቤላ ክልል መንግስት በግድ ሳይፈልጉ በፈለጉት ዋጋ ከፍለው 300 ሺ 
ሄክታር መሬት እንደሰጧቸው ተናግረዋል። እኔ የጠየቁት 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ያሉት ባለሃብቱ፣ እነሱ ግን 300 ሺ ሄክታር ካልወሰድ ብለው ሰጡኝ ብለዋል። 
መሬታቸውን ማንም እንደማይነጥቃቸው የተናገሩት ባለሀብቱ "መሬቴን ንኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ። ይሄ ማስጠንቀቂያ ነው። የእስካሁኑ የሚበቃ መሰለኝ። ራሴን 
መከላከል አያስፈልግኝም። ባለስልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት ውጤቱን ያገኙታል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ 
ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት 
እንደሚሰጡኝ ይልቁንም እኔ በማምንበት ዋጋ እንድከፍል፣ ከዚያ ያነሰ መሬት ግን እንደማይሰጡኝ አስታወቁ፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፡፡" ተቀበልኩ የሚሉት ባለሃብቱ፣ 
በመካከለኛ ደረጃ ያሉ ባለስልጣናት ፖለቲካውን ተገን አድርገው ሊያሰሩኝ አልቻሉም ብለዋል። ሼክ ሙሃመድ አላሙዲንንም በኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን የቻሉ መንግስት
 ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

Saturday, 26 December 2015

እነ ጌታቸው ሺፈራው 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

እነ ጌታቸው ሺፈራው 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው
በሽብር ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪያቸው ተናግሯል
‹‹ካሁን በፊት ይዝቱብኝ ነበር፤ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የታሰርኩት›› ጌታቸው ሺፈራ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ትናንት ታህሳስ 15/2008 ዓ.ም በያሉበት ታድነው የታሰሩት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ዳንኤል ተስፋየ እና ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ዛሬ ታህሳስ 16/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡...
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በሽብር ተጠርጥረው መታሰራቸውን በመግለጽ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ፖሊስ ታሳሪዎቹ የተጠረጠሩበትን ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪዎች ‹‹የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን፣ በመመልመል፣ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ወንጀል ሊፈጽሙ ሲሉ ተይዘዋል›› ብሏል፡፡
ተጠርጣሪዎች ስለተጠረጠሩበት ወንጀል እና ስለተጠየቀባቸው የጊዜ ቀጠሮ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ይዝቱብኝ ነበር፤ እኔ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የተያዝኩት፡፡ ቤቴ ሲፈተሽ የተገኘውም የህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ሰማያዊና መድረክ) መግለጫዎችና ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ ከተባለው ወንጀል ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ በነጻ ልሰናበት ይገባል›› ሲል ተናግሯል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባሉ አቶ ዳንኤል ተስፋየ በበኩሉ ‹‹በፍተሻ የተያዙብኝ ባንዲራ፣ ሲዲ እና ስልክ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለምርመራ የተጠየቀውን ያህል ጊዜ መፈቀድ የለበትም፤ አጭር ቀጠሮ ይሰጠን›› ሲል ጠይቋል፡፡
ሦስተኛው ተጠርጣሪ አቶ ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ደግሞ ‹‹እኔ በቂርቆስ ክ/ከተማ በኢህአዴግ ተደራጅቼ የምሰራ ሰው ነኝ፡፡ ፖሊስ ከገለጸው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ ድርጅቱን ጭራሽ አላውቀውም፤ የልጅ አባት ስለሆንኩ አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ›› በማለት አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ፖሊስ የጠየቀውን 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለጥር 14/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ከሁለት ወራት በፊት ከአርባምንጭ ተይዘው ወደማዕከላዊ የመጡት በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እነ ሉሉ መሰለ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ለእስር ከተዳረጉት መካከል የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አቶ ኤርሚያስ ጸጋየ፣ አቶ ፍሬው ተክሌ እና አቶ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡