Wednesday, 28 October 2015

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡



ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡:
እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡ በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ፍርድ ቤቱ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም አቶ አንዳርጋቸው እሱ ጋር እንደሌሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ መግለፁ ይታወሳል፡፡
ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ 
ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ከአቶ ምንዳዬ ጥላሁን በተጨማሪ 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲመሰክሩለት በመፈለጉ፤ እና ፍርድ ቤቱም አቶ አንዳርጋቸው ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲመቸው ተከሳሾቹ እንዲጠቁሙት በገለፀው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ተቋማት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
ሁለቱ ተከሳሾች ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ለፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በፃፉት ደብዳቤ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንክ ኮርፖሬት መግለጫ መስጠቱን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2007 ዓ.ም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዝ፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያ መንግስት ፍርዱን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን አስታውሰዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ዜግነታቸው እንግሊዛዊ የሆሉትን አቶ አንዳጋቸው ጉዳይ ላይ ክትትል እንደሚያደርግ በደብዳቤው አስታወስዋል፡፡
በመሆኑም ከእነዚህ ሶስት አካላት በላይ አንዳርጋቸው ፅጌ ስላሉበት ቦታ የሚያውቅ ስለሌለ ለሶስቱም አካላት አቶ አንዳርጋቸው የት እንዳሉ እንዲገልፁና አቶ አንዳርጋቸውም ምስክር እንዲሆኑላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

Tuesday, 20 October 2015

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 ሽልማት አሸናፊ ሆነ



ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 ሽልማት አሸናፊ ሆነ
18 የእስር አመታት በግፍ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 አሸናፊ ሆነ መመረጡን ድርጅቱ አስታውቋል።
ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የጽናት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ቤት አሳልፏል። የእስክንድር ስራዎቹ ድንበር እና ባህል ተሻጋሪ ናቸው በማለት ያወደሰው ድርጅቱ፣ 5 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ሽልማት በ36ኛው የአለማቀፍ ጻሃፊዎች ቀን ላይ ይበረከትለታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ቡድን የእስክንድርን መታሰር አለማቀፍ ህግን የጣሰ መሆኑን በመጥቀስ እንዲፈታ መጠየቁን መግለጫው አውስቷል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ከሶስት አመታት በፊት የፔን ባርባራ ጎልድ ስሚዝ ፍሪደም ቲ ራይት ፣ አምና ደግሞ ጎልደን ፔን አዋርድ ኦፍ ፍሪደም አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል። በምርጫ 97 ወቅት እስክንድር ከቅንጅት መሪዎች ጋር አብሮ ታስሮ የተለቀቀ ሲሆን፣ ቀድም ብሎም ከስራው ጋር በተያያዘ ከ5 ጊዜ በላይ ታስሯል። በስልጣን ላይ ያለው ገዢ ፓርቲ የጋዜጣ ፈቃድ የከለከለው እስክንድር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የስርዓት ለውጥ አይቀሬ መሆኑን ማስረጃዎችንና ምልከታውን ተንተርሶ የተለያዩ ጽሁፎችን በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ጽፏል።

የተመስገን ደሣለኝ ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ

የተመስገን ደሣለኝ ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሣለኝ ተመስገንን ረቡዕ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ዝዋይ ሄዶ መጎብኘቱንና፣ ወንድሙ የግራ ጆሮው ሙሉ በሙሉ እንደማይሰማ፣ ጀርባው ላይ ያለው እብጠት እየባሰበት መሆኑን በጀርባው መተኛትም እንደማይችል አስረድቷል፡፡ ተመስገን ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ሕክምና እንደማያገኝና ቤተሰቡም ለማሳከም ቢጠይቅም ፍቃድ መነፈጉን፣ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ይዘው ሄደው “በማረሚያ ቤቱ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም” የሚል መልስ ማግኘታቸውን ታሪኩ ለቪኦኤ ገልጿል፡፡ ተመስገን ያዘጋጃቸው ከነበሩት መፅሔቶች በአንዱ ላይ አምደኛ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምም ከጥቂት ወራት በፊት ከፕሮፌሰር መስፍንና ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው እዚያው ዝዋይ ድረስ ሄደው እንዳዩትና በወቅቱ የግራ ጆሮው ይደማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ የተመስገን ደሣለኝ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንንም የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ዝዋይ ሄደው ያዩት መሆናቸውንና በቦታው ርቀት ምክንያት ከዚያ በኋላ በአካል እንዳላገኙት ገልፀው ከቤተሰቦቹ ግን አሁን ያለበትን ሁኔታ እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት፣ መንግሥቱ ባወጣቸው ደንቦችና በዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችም መሠረት ማንም እሥረኛ ጤንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መያዝ እንደሚገባው፤ አስፈላጊ በሆነ ጊዜም ሕክምና የማግኘት መብት እንዳለው፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርም ሆነ የወህኒ ቤቱ ሃኪም ታራሚው ሕክምና ማግኘቱን የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤቱ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ ተመስገን አዲስ አበባ ድረስ ተወስዶ ሕክምና ማግኘቱን፤ በማረሚያ ቤቱ ውስጥም እየታከመ መሆኑን፣ ጤናማና እየተንቀሣቀሰ ያለ መሆኑን ገልፀው ጤንነቱ ታውኳል፤ ሕክምና ማግኘት አልቻለም የተባለው ሃሰት መሆኑን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡ ጠበቃው አቶ አምሃ ግን አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ አለመታከሙን፣ ሄዶ ቢሆን ኖሮ እርሣቸው ያውቁ እንደነበር ተናግረዋ የማረሚያ ቤቱን የሥራ ኃላፊ መግለጫ አስተባብለዋል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

Sunday, 18 October 2015

የአብዱ ኪያር “አልተለያየንም” ዘፈን በመንግስት ሚድያዎች እንዳይተላለፍ ታገደ

Sunday, October 18th, 2015 | ዘ-ሐበሻ
የአብዱ ኪያር “አልተለያየንም” ዘፈን በመንግስት ሚድያዎች እንዳይተላለፍ ታገደ
(ዘ-ሐበሻ) ድምፃዊ አብዱ ኪያር “አልተለያየንም” በሚል በአዲሱ የ”ጥቁር አንበሳ” ሲዲው ላይ ያቀረበው ዘፈን በመንግስታዊ ሚዲያዎች ላይ እንዳይተላለፍ ዕግድ መተላለፉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስታወቁ::
“በካርታ ብንለያየም – ኢትዮጵያም ኤርትራም አንድ ናቸው”… “አዲሱ ማንነቴን መቀበል አቃተኝ”… “በወላይታ ሙዚቃ ይጨፈራል በአስመራ”… የሚሉ መል ዕክቶች ያሉት በአንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይኸው የአብዱ ኪያር ዘፈን በኢትዮጵያ ሁሉም ከተሞች ባሉ ሙዚቃ ቤቶች; በምሽት ክለቦችና መዝናኛ ቦታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::...
መንግስታዊ ሚድያዎች እንዳያሰሙት የተከለከለው ይኸው “አልተለያየንም” የሚለውን ዘፈኑን ዘ-ሐበሻ እዚህ ጋብዛችኋለች:: ያድምጡት:: ለወዳጅ ዘመድዎም ያካፍሉት::





ድል ለአርበኞች ግቦት7! ሞት ለዘረኞች!

በ17/10/15 በሚኖሶታ ከተማ ለአርበኞች ግቦት7 የተደረገው የገዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማረና በደመቀ፣ኢትዮጲያዊ ጨዋነትና ቁርጠኝነት የታየበት ነው በድጋሚ ሚነሶታዎች ኮርተንባችኃል በርቱ፣ ለወገን ኩራት ፣ለጠላት ራስምታት ሆናችኃል ኢትዮጲያዊነት በተግባር ታይቷል። የፑስት ሮድ ታክሲ ሹፊሮች ከነፃነት ታጋዮች ከታጋይ ትግስት፣ከታጋይ ዘመነ ካሴና ከሊሎችም ታጋዮች ጉን መሰለፋችሁን በተግባር አሳይታችኃል በርቱ በርቱ።ሴቶች እህቶቼ የወገን ግፍና ሰቆቃ እረፍት እደነሳችሁና ግፍና ግፈኞችን ለመታገል ያደረጋችሁት ቁርጠኝነትና ያስመዘገባችሁት ስኬት የጣይቱ ልጆች ያስብላችኃል በርቱ በርቱ፣ አባቶችና እናቶችም በሳያችሁት አኩሪ ተግባር የብዙ ወጣቶችን ልብ አንፃችኃል በርቱ በርቱ።ዲያቆናት፣ቄሱች፣ሼህሁች በዝግጁቱ ላይ ተገኝታችሁ ለሐይማኖታችሁናለአገራችሁ በፅናት ...መቆማችሁን አስመስክራችኃል በርቱ በርቱ።አበሳው ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየው/ዘሀበሻ/ለወገንህ መረጃን ማድረስ ብቻ ሳይሁን ግዜህን ፣ጉልበትህን፣ገንዘብህ ለኢትዩጲያ ነፃነት ሁሉንም ነገርህን ከነቤተሰብህ መስጠትህን በቃል ብቻ ሳይሁን በተግባር ማሳየትህ ጋዜጠኛ ብቻ ሳትሆን አርበኛም ጭምር መሆንህን በማየቴ እስርቤት ያሉት የሙያ ጓደኞችህ በመንፈስ ሀሴትንና ደስታን እደሚያደርጉ ምንም ጥርጥር የለኝም በርታ አባሳዩ የኢትዩጲያ አምላክ ብድራቱን ይክፈልህ !በአጠቃላይ በሚኖሶታ አኩሪ ታሪክ ተመዝግቧል። ኢትዩጲያ በቆራጥ ልጆቹ ሀይማኖትና ባህሏ፣ተሪክና ክብሯ ነፃነቷ ተጠብቆ ለዘላለም ይኖራል።ድል ለአርበኞች ግቦት7! ሞት ለዘረኞች!