Tuesday, 29 September 2015

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ !


ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ !

የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ቁጥጥር ስራ መዋሉን ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ችያለሁ ። ጋዜጠኛ ግሩም ላለፉት ሶስት ቀናት ሲታደን መቆየቱን የጠቁሙኝ ምንጮች ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠውልኛል !
የጋዘጠኛ ግሩም መታሰር እንደሰማሁ ወደ የመን ስልክ በመደዎል ያነጋገርኳት ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ በየነንየጋዜጠኛ ግሩምን መታሰር አረጋግጣልኛለች ። ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ ከዚሁ ጋር አያይዛ ጋዜጠኛ ግሩምን ያሳሰረው ኢትዮጵያዊ መሆኑንና የታሰረበትም ምክንያት " ከተለያዩ ሃገራት በተረጅዎች ስም ገንዘብ ትሰበስባለህ ፣ ወደ ከየመን ውጭ መረጃ ታሰራጫለህ " የሚል ክስ እንደሆነ ጠቁማኛለች ።
በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃን ከማቅረብ ባለፈ ፣ ረግተው በማያውቁት የየመን ከተሞችና በርሃ ላይ በአደጋ ተከበው ለሚሰቃዩ ስደተኛ ወገኖች በነፍስ ደራሽ የነበረው ብርቱ ጋዜጠኛ ግሩም የየመኑን የኢትዮጵያን የስደት መከራና ሰቆቃ የሚዳሰወስ "የሞት ጉዞ " የሚል መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘመጋም !
በጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት እስራት ዙሪያ ስላሉት አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልኩ መረጃ የማቀርብ መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 18 ቀን 2008 ዓም

Thursday, 24 September 2015

«ሀገር እንወዳለን»

«ልብ ብለው ያንብቡት»
«ሀገር እንወዳለን»
ፋስት መረጃ ዶት ኮም / በዳንኤል ክብረት

ሰውዬው የውጭ ሀገር ዜጋ ቢሆኑም ዐሥር ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አስተምረዋል፡፡ ሚስተር ዣክ ይባላሉ፡፡ ሻሂ እየጠጡ ኢትዮጵያዊውን ጓደኛቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ ሁለት ጊዜ ፉት እንዳሉት ጓደኛቸው ከች አለ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የተጠለፈበት ቆብ አድርጓል፡፡ በለመዱት የኢትዮጵያውያን ባህል መሠረት ከመቀመጫቸው ተነሥተው ተቀበሉት፡፡ ወንበር ስቦ እንደ ተቀመጠ ያጠለቀውን ቆብ ጠረጲዛው ላይ አኖረው፡፡ ሚስተር ዣክ የተቀመጠውን በኢትዮጵያ
ባንዴራ የተጠለፈ ቆብ አየት አደረጉና «እናንተ ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው በባንዴራችሁ
ማጌጥ የምትወዱት?» አሉና ኢትዮጵያዊውን እንግዳቸውን ጠየቁት፡፡ «እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገራችንን እንወዳለን፡፡ በሀገራችን ለመጣ ርኅራኄ የለንም፡ ይህ የሀገር ፍቅር በደማችን ውስጥ አራተኛ ሴል ሆኖ
ተቀምጧል፡፡ ለዚህ ነው» አላቸው፡፡ «ቆይ ግን ሀገራችንን እንወዳለን ስትሉ ምን ማለት ነው? ወንዙ እና ተራራው ነው? ሜዳው እና ጫካው ነው? ምኑ ነው ሀገር?» ኢትዮጵያዊው ትኩር ብሎ እያያቸው «ሁለመናው ነው፡፡ ሰው፣ እንስሳው፣ ሜዳው፣ተራራው፣ ጫካው፣ ወንዙ፣ ሁሉም» አለና መለሰላቸው፡፡ «እኔ ግን አይመስለኝም» አሉት ሚስተር
ዣክ፡፡ «እንዴት?» ተገርሞ ጠየቃቸው፡፡ «እናንተ ለሀገራችሁ የድመት ፍቅር ይመስለኛል
ያላችሁ» «የድመት ፍቅር ምን ዓይነት ነው» እንግዳው ተገርሞ እንደገና ጠየቀ፡፡ «ቤት ያከራዩኝ ሰውዬ ምን እንዳሉኝ
ታውቃለህ፡፡ ድመት ልጆቿን የምትበላው ስለምትወዳቸው ነው፡፡ ፍቅሯን የምትገልጠው
ልጆቿን በመብላት እና ለዘላለም ሆዷ ውስጥ በማድረግ ነው አሉኝ» «እና»
«እናማ እናንተም ለሀገራችሁ ያላችሁን ፍቅር የምትገልጡት ሀገራችሁን በመብላት
ይመስለኛል» «ያንን ያህል እንደርሳለን ብለው ነው» አንገቱን ወዘወዘ እንግዳው፡፡
«ኧረ እንዲያውም ሳይብስ አይቀርም፡፡ አሁን ለምሳሌ እናንተ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዥዎች
ባለመገዛታችሁ ስትኮሩበት አያለሁ፡፡ ልክ ነው ለጀግኖች አባቶቻችሁ ምስጋና ይግባቸውና ለዚህ
የታሪክ ዕድል አብቅተዋችኋል፡፡ የሦስት ሺ ዘመን የነጻነት ታሪክ አለን እያላችሁ በኛ በአፍሪካውያን ላይ ትኮሩብናላችሁ እንጂ በሦስት ሺ ዘመን ምን ሊሠራበት እንደሚችል አላሳያችሁንም፡፡ ነጻነትን እንዴት ማግኘት
እንደሚቻል አሳያችሁን እንጂ በነጻነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል አርአያ ልትሆኑን አልቻ ላችሁም፡፡ እርስ በርስ ስትዋጉ፣ አንዳችሁ የሠራችሁትን ሌላችሁ ስታጠፉ፣ መቶ ዓመት የለፋቸሁበትን በአንድ ቀን ደምስሳችሁ እንደገና
ስትጀምሩ ነው የኖራችሁት፡፡ እስቲ ተመልከቱት የሦስት ሺ ዘመን ታሪክ አለን ነውኮ
የምትሉት፡፡ ታድያ ሦስት ሺ ዘመን ተጉዛችሁ እዚህ መድረስ ብቻ ነው የቻላችሁት? አቆጣጠራችሁ ግን በምንድን ነው? አንድ ዓመትስ በእናንተ ዘንድ ስንት ቀን ነው? «ለመሆኑ ሀገራችሁን ስለምትወዱ ነው እርስ በርስ ስትዋጉ የኖራችሁት? ሀገራችሁን ስለምትወዱ ነው የቀደመውን እያፈረሳችሁ እንደ አዲስ የምትጀምሩት? ወንዙን ሰው ሲነካባችሁ ዘራፍ ብላችሁ ትነሣላችሁ፤ እናንተ ግን ወንዙን አትጠቀሙበትም፡፡ መሬቱን ሰው ሊቆርስ ሲመጣ አራስ ነብር ሆናችሁ
ትነሣላችሁ፤ እናንተ ግን መሬቱን አታለሙትም፡፡ ቅርሳችሁን ሰው ሊዘርፍ ሲመጣ የቻለ ይዘምታል ያልቻለ ያቅራራል፤ እናን ተም ግን ቅርሱን አትጠብቁትም፡፡ አሁን ይሄ ምቀኝነት ነው ወይስ ሀገር መውደድ ነው?» ኢትዮጵያዊው እንግዳ ያልጠበቀው ነገር ስለመጣበት ትክዝ እንደማለት አለና «በርግጥ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ዋልጌዎች የሚሠሩት ሥራ ግን መላውን ሕዝብ መወከል የለበትም» አላቸው፡፡ «ልክ ነህ» አሉ ሚስተር ዣክ «ልክ ነህ ጥቂቶች ሁሉንም አይወክሉም፡፡ የማየው ነገር ግን ይህንን አባባልህን እንዳልቀበለው ያስገድደኛል፡፡ ተመልከት ቅቤው ውስጥ ሙዝ እየጨመረ የሚሸጠውኮ የራሳችሁ ሰው ነው፡፡ ለውጭ ሀገር አይደለም የሚሸጠው ለገዛ ጎረቤቱ ነው፡፡ ሂድ እስኪ በየሱቁ ስንት ጊዜው
ያለፈበት የታሸገ ምግብ ይሸጣልኮ፡፡ ገዥው የሌላ ሀገር ሰው አይደለም፡፡ የራሳችሁ ወገን ነው፡፡ ያደረ ኬክ፣ ያደረ ምግብ፣ የተበላሸ ሥጋ የምትሸጡትኮ ለጠላት ሀገር አይደለም ለራሳችሁ ሰው ነው፡፡ አሁን እነዚህ ሰዎች
ሀገራችንን እንወድዳለን ብለው ግሥላ ሲሆኑ ባይ ይገርመኛል፡፡ ወገናቸውን እየገደሉ ምኑን
ነው የሚወድዱት እላለሁ፡፡ አሥር ብር የገዛችሁትን ዕቃ አንዳች እሴት ሳትጨምሩበት በገዛ ወገናችሁ ላይ መቶ ብር አትርፋችሁ ያለ ርኅራኄ እየሸጣችሁ ሀገራችሁን ትወድዳላችሁ ማለት ነው?» «መሬቱን ብቻ ነው እንዴ ሀገር የሚሉት?
በአንድ መንደር ውስጥ የሚገኝ መሸታ ቤት መንደርተኛውን እየበጠበጠ ስላስቸገረ የቀበሌ ጥበቃዎች መጡና ድምጽ ቀንሱ አሏቸው፡፡
እነርሱም እሺ አሉና የሚገርም ዘፈን ከፈቱ አሉ፡፡»
«ምን የሚል?»
«እኛም አንተኛ ሰውም አናስተኛ የሚል»
«ሆሆይ! ይህቺን አገር አገላብጠው ነውኮ የሚያውቋት» አለ እንግዳው ተደንቆ፡፡
«ሂድና ሠራተኛውን እየው፡፡ ሌላ ትርፍ ሀገር ያለው፣ በቅኝ ገዥዎች ተገድዶ የሚሠራ ነውኮ የሚመስለው፡፡ አንዳንዱ ዘግይቶ ይገባል፣ አንዲት ነገር ሳይሠራ ለሻሂ ይወጣል፤ እጁን ወደ
ኋላ አጣምሮ እየተዝናና ቢሮ ይመለሳል፣ አንዲት ነገር ሳይሠራ ለምሳ ይወጣል፡፡ አንድ ነገር ከጠየቅከው «ነገ፣ ነገ» ነው የሚለው፡: ነገ መቼ እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ግንባታዎቻችሁ ለጠላት ሀገር የሚሠሩ እንጂ እንወድዳታለን ለምትሏት ሀገር የሚሠሩ አይመስሉም፡፡ የሚጀመሩበትን እንጂ ግንባታው የሚያልቅበትን ጊዜ ማንም አያውቅም፡፡ ተሠርቶ ሳይመረቅ ይፈራርሳል፡፡ ከሚሠራበት ገንዘብ የሚበላው ይበልጣል፡፡ ሠራተኛው ምድጃ ከብቦም ተረት ያወራል፣ አካፋ ተደግፎም ሥራ ላይ ተረት ያወራል፡፡ «ለመሆኑ እነዚያ የዚህ ሁሉ ግንባታ ሠሪዎቹ፣ አሠሪዎቹ፣ ተቆጣጣሪዎቹ አሁን አንተ እንደምትለኝ ሀገራቸውን ይወዳሉ ማለት ነው? የትኛዋን ሀገር ነው የሚወድዱት? ወይስ እኛ የማናውቃት ሌላ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለቻችሁ? ቻይናዎቹ ያሉትን ሰምተሃል?»
«ምን አሉ?» «መንገድ ሲሠሩ፣ እነርሱ ቀን ቀን የሠሩትን እና የሰበሰቡትን የአካባቢው ሰው ሌሊት ሌሊት አፍርሶ እና አግዞ እየወሰደ አስቸገራቸው፡፡ በኋላ እንደ እኔው ሀገራችሁን ትወዳላችሁ ሲባል ሰምተው ስለነበር «ቆይ እነዚህ ኢትዮጵያውያን
ሌላ ሀገር አላቸው እንዴ? ከሀገራቸው ሰርቀው የት ነው የሚወስዱት?» አሉ ይባላል» «አሁን አሁንኮ ትውልዱ ጉዳዩን እያስተዋለ እየተለወጠ ነው፡፡ ምናልባት ቀድሞ እንዲህ ያለ ነገር ሊኖር ይችላል» አለ ኢትዮጵያዊው እንግዳ፡፡
«የለም የለም እንዲያውም ብሷል፡፡ አዲሱ ትውልድ የምትለው የሚገኘውኮ እኔ በማስተምርበት ኮሌጅ ነው፡፡ አየሁትኮ፡፡ ቤተ መጻሕፍት ገብቶ በድኻ ሀገር በጀት የታተመ መጽሐፍ የሚሰርቅ፣ የሚቀዳድድ፣ እላዩ ላይ ትርኪ ምርኪ ነገር የሚጽፍ ይህ ነው ሀገር ወዳዱ ትውልድ? ከእርሱ ቀጥሎ እዚህ ትምህርት ቤት የሚማረው የራሱ ወንድም እና እኅት መሆኑን እንኳን የሚረሳው ነው ሀገር ወዳዱ? ከዕውቀት ክርክር ይልቅ በጎጠኛነት ተቧድኖ መደባደብ የሚቀናው ነው ሀገር ወዳዱ ትውልድ? ነገሩ ምን ያድርግ የሚያስተምሩትም ቢሆኑኮ የሀገራቸውን ሰው የሚያስተምሩ፣ እንወዳታለን ለሚሏት ሀገር ትውልድ ሊያፈሩ የሚያስተምሩ አይመስሉም፡፡ የዛሬ ሃያ ዓመት ባዘጋጁት ማስታወሻ እያስተማሩት፣ ከቤተ መጻሕፍት አውጥተው ቢሮአቸው የደበቁትን መጽሐፍ ማጣቀሻ እየሰጡ ጥናት እያዘዙት ምን ያድርግ፡፡ በገጠሩ ሴት ልጅ በልጅነቷ ተጫውታ ሳትጨርስ ትዳርና በልጅነቷ ትወልዳለች፡፡ እርሷም ልጅ፣ የወለደችውም ልጅ ይሆንባትና አብረው እየተጫወቱ ያድጋሉ፡፡ አሁንም ኮሌጃችሁን እንደዚያው አደረጋችሁትኮ፡፡ «አሁን በየሕክምና ቦታው የሚሠራው የድሮው ትውልድ ነው ልትለኝ ነው? ለመሆኑ እርሱ ሀገር ወዳድ ነው? ጊዜ ባለፈበት መድኃኒት ወገኑን የሚያክመው፣ በመንግሥት በጀት የተገዛ መድኃኒት አውጥቶ የሚሸጠው፣ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሌለ ምርመራ እያዘዘ ድኻው ተማርሮ ከሕክምና ይልቅ ወደ ዳማ ከሴ እንዲጓዝ ያደረገው ሀገሩን ስለሚወድድ ነው? «እስቲ የመኪና ምርመራ እንዴት እንደሚደረግ ተመልከት፡፡ መኪናው ሳይታይ በስልክ እኮ ነው የሚመረመረው፡፡ ለመሆኑ መርማሪው ሰውዬ ይሄ መኪና እርሱን፣ ቤተሰቡን፣ ዘመዶቹን እንደማይገጭ ርግጠኛ ነው? ሀገሩን ስለሚወድ ነው ሕዝብ እንዲያልቅ ፈቅዶ የተበላሸ መኪና ጤነኛ ነው ብሎ የሚፈርመው? «በአንድ ወቅት አዲስ አበባ መንገዶቿን ሰየመች ተብሎ በየቦታው ተለጠፈ፡፡ ሦስት ወር አልሞላውም ሲወድቅ እና ሲጠፋ፡፡ ማን ዘረፈው? ሀገር ወዳዱ፡፡ ተካዮቹስ ቢሆኑ ለምን ዘወር ብለው አላዩትም? ሀገር ወዳድ ስለሆኑ፡፡
«እኔ ሀገር የመውደድን ጉዳይ አሁን እርስዎ ባሰቡበት መንገድ አስቤው አላውቅም፡፡ ብቻ እኛ የሀገራችን ጉዳይ ሲነሣ ደመ ቁጡዎች፣ አትንኩን ባዮች እና ኮስታሮች መሆናችንን አውቃለሁ፡፡» አለ ኢትዮጵያዊው እንግዳ፡፡
«ልክ ነህ ይህንንማ ዓለም በሙሉ ይመሰክርላችኋልኮ፡፡ ይህች ሀገርኮ ዝም ብላ እንዲሁ በነጻነት አልኖረችም፡፡ አንዳች ልዩ ነገርማ አላችሁኮ፡፡ ሀገራቸውን ባይወድዱ ኖሮ አባቶቻችሁ ደማቸውን ባልገበሩ ነበር፡፡ አጥንታቸውን ከስክሰው ድንበር ባላጠሩ ነበር፡፡ ዘመናዊ መሣርያ የታጠቁትን በባህላዊ መሣርያ ባላሸነፉ ነበር፡፡ ግን ሀገር መውደድ ይሄ ብቻ ነወይ) ሌላ አይንካን እኛ ግን እንደፈለግን እንጫረስ፣ ሌላ አይዝረፈን እኛ ግን እንዘራረፍ፣ ሌላ አይጨቁነን እኛ ግን
እንጨቋቆን፣ ቅኝ ገዥ መጥቶ ቀንበር የሆነ ሕግ አያውጣብን እኛ ግን እርስ በርሳችን ቀንበር እንጫጫን፣ ጠላት ወርሮ
መብታችንን አይንካ፣ እኛ ግን መብታችንን እርስ በርስ እንገፋፈፍ ነው የምትሉት) ይሄኮ ነው ያልገባኝ ነገር፡፡ ሀገር ማለትኮ መልክዐ ምድሩ ብቻ አይደለም፤ ይሄ ባለጉዳይ ሆኖ ቢሮህ የመጣው፣ታምሞ ሊታከም አንተጋ የመጣው፣ሊማር አንተ ጋ የመጣው፣ሊገዛ ሱቅህ ጋ የቆመው፣ በሞያህ እያገለገልከው ያለኸው፣በመኪናህ ላይ የተሳፈረው፣ እርሱኮ ነው ሀገር» አሉ ሚስተር ዣክ፡፡
«እንዴ ሚስተር ዣክ በዐሥረኛው ዓመት ሀገራችን መረረዎት መሰለኝ፡፡ እርስዎም እንደኛው ደመ ቁጡ ሊሆኑ ነው ማለት ነው፤ባለፈው ታምመው ተኝተው እያለ የኢትዮጵያዊ ደም ነበር እንዴ የተደረገልዎ» አለ ኢትዮጵያዊው ነገሩን ወደ ቀልድ ወስዶ ሀሳብ ለማስቀየር፡፡
«አየህ ይህች ሀገር ይበልጥ ስታውቃት ይበልጥ የምታሳዝን፣ ይበልጥ የምታስቆጭ፣ ይበልጥ የምታንገበግብ ናት፡፡ ቆይ ግን ህንን ሁሉ የምታደርጉት ሀገራችሁን ስለምትወዱ ከሆነ ሀገራችሁን ባትወድዱ ኖሮስ ከዚህ የከፋ ምንታደርጉ ነበር? አንድ እዚህ ሀገር የሰማሁት ቀልድ ነገር አለ፡፡ አንድ ባል ሚስቱን ይደበድባታል፡፡ እርሷም ቤቷን ትታ ትወጣለች፡፡
በኋላ ሽማግሌ ገብቶ ታረቁ ይላቸዋል፡፡ ባልም እኔኮ ስለምወዳት ነው የመታኋት፣ የፍቅር ነው ይላል፡፡ ሚስቲቱም ስትወደኝ ከሆነ እንዲህ የምትመታኝ ስትጠላኝ ምን ልታደርግ ነው? አለችው አሉ፡፡ አሁንም እናንተ በሀገራችሁ ላይ ራሳችሁ ይህንን ሁሉ ግፍ የምትፈጽሙት ሀገር ወዳድ ስለሆናችሁ ከሆነ ብትጠሏት ኖሮ ምን ልታደርጉ ነበር?

Sunday, 6 September 2015

በጠራራ ፀሐይ ዘረፉ!

ገቢዎችና ጉምሩክ ነን ባዮች ከፓሊስ ጋር በመጣመር መርካቶ አካባቢ ላይ፤ ሸማቹን ህብረተሰብ መንገድ ላይ እያስቆሙ የያስከውን እቃ የገዛህበት የቫት ደረሰኝ አምጣ ወይም አሳየን እያሉ በጠራራ ፀሐይ እየዘረፉት ነው!!
መረን የለቀቀው የወያኔ አስተዳደር በህጋው መንገድ የንግድ ፍቃድ አውጥተው ህጋው ሱቅ ያላቸው ግለሰቦችን ጭምር በአሳቻ ሰዓት በመምጥ እራሳቸው ሸማች በመምሰል ከገዙ በሃላ እራቸው ምስክር በመሆን ነጋዴው ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለሃል በማለት ንብረቱን እንካን ሳይሰበስብ ወደማጎሪያቸው ይወስዳል ይህ ቅጥ ያጣ አስተዳደር ሁላችን በአንድነት በቃ ልንለው ይገባል !!!

Tuesday, 25 August 2015

አርበኞች ግንቦት ሰባት ገንዘባችንን ዘረፈው ( ሄኖክ የሺጥላ )

አርበኞች ግንቦት ሰባት ገንዘባችንን ዘረፈው ( ሄኖክ የሺጥላ )
ትግሉ ገንዘብ ያስፈልገዋል ማለት ትግሉ በገንዘብ ነው የሚመጣው ማለት አይደለም። አርበኞች ግንቦት ሰባት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ማለት፣ ገንዘብ ስላዋጣሁ አንገረብን አልፋችሁ ካልሄዳችሁ ውርድ ከራሴ የሚያስብል አይመስለኝም ። ትግል በገንዘብ ይደገፍ ይሆናል እንጂ ፣ ገንዝብ የድል መሰረት ሆኖ ትግሉን ወደፊት አይገፋውም ። ትግሉ ብረት የተሸከሙት ሰዎች ቁርጠኝነት እና መለኮታዊ ዕድል ድምር ነው ። ገንዘብ ያንን ዕድል ማስፈጸሚያ እና አጋጣሚውን መፍጠሪያ ነው ።
ስለዚህ ትግሉ ባለ ድል የሚሆነው በናንተ ድጋፍ ነው ሲባል ፣ የቁስ ብቻ ሳይሆን የመንፈስ መሆኑን አትርሱ። በተጨማሪም ፣ ገንዘብ ስለረዳችሁ ብቻ አርበኞች ግንቦት ሰባት ህወሃትን የማሸነፍ ግዴታ አትጣሉበት ። እናንተም ትግሉ ወደ ድል እንዲቀየር በሃሳብ እርዱ ። ገንዘብ ባለ ድል ቢያደርግ ኖሮ ታላቋ አማሪካ በሄደችበት ባሸነፈች ነበር ። የልጆቹን ወኔ ፣ የአላማ ጽናት እና የሕይወት መስዋትነት ፣ ከባህር ማዶ በጨረታ መሃል በምትረጩት ገንዘብ ልክ አትዩት ። እያደረጋችሁት ያለውን እኔ በበኩሌ አደንቃለሁ ። ግን መዋጮ የቁጣ እና የየት ደረሰ ሊቸንሳ አይመስለኝም ። ሰው ህይወቱን በሚያዋጣበት ትግል ፣ የገንዘብ እርዳታ አድርጎ ያንን እንደ ትልቅ አስተዋጾ መቁጠር የሚፈልግ ካለ ፣ ልክ አይመስለኝም ። እርዱ ፣ ግን ደሞ አትታበዩ ። የምናደርገው ነገር ሁሉ ለራሳችን ነውና !

Tuesday, 21 July 2015

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል


የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል” በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል አባላት ለፕሮፌሰሩ በጋራ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የገለጸው ሻለቃ አክሊሉ፣ ከአባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በሰራዊቱ ውስጥ የታየው መነቃቃት ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲፋጠን፣ በተለይም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ተቀራርቦ የመስራት ድርድር እንዲፋጠን እንደሚያደርገው ሳለቃ አክሊሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል።የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ መድረስ ዜና ይፋ ከሆነ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ህዝብ እየጨመረ መምጣቱንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕ/ር ብርሃኑ ግንቦት7ትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተው ፣ አርበኞች ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ የውህዱ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነዋል። በውህደቱ ላይ ለመገኘት የነበራቸው ውጥን ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ፣ ለመሪነት የተመረጡት በሌሉበት ነው። ይሁን እንጅ በውህደቱ ወቅት ለጉባኤተኛው በስልክ ባስተላለፉት መልክት፣ አንዳንድ ችግሮች ተፈተው በቅርቡ በረሃ ወርደው እንደሚቀላቀሉዋቸው ቃል ገብተው ነበር።
በምርጫ 97 በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከሁለት አመት ላለነሰ ጊዜ በእስር ቤት አሳልፈዋል። ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው በክኔል ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው ከወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።

Thursday, 16 July 2015

ስዊድን፥ ጠቅላይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ መልስ ሆስፒታል ገቡ

ስዊድን፥ ጠቅላይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ መልስ ሆስፒታል ገቡ
የስዊድኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ሽቴፋን ሎፍቨን ከኢትዮጵያ ወደ ስዊድን በመብረር ላይ ሳሉ ስለታመሙ ሀገራቸው ሲደርሱ ሐኪም ቤት መግባታቸውን የሚንሥትሩ ቃል አቀባይ አኔ ኤክበርግ ገለጡ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ አውሮፕላናቸው የስቶክሆልም አየር ማረፊያን እንደነካ በአምቡላንስ በፍጥነት ወደ ሐኪም ቤት መወሰዳቸው ተዘግቧል። አዲስ አበባ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የልማት ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የስዊድኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ወደ ስዊድን ሲበሩ «ብርቱ ማቅለሽለሽ» እንደገጠማቸውም ተጠቅሷል። የጠቅላይ ሚንሥትሩ ቃል አቀባያዋ አኔ ኤክበርግ፣ ሚንስትሩ «የተወሰኑ ምርመራዎች ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ» ሲሉ ለፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ስለጠቅላይ ሚንሥትሩ ኅመም ግን ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የ57 ዓመቱ የሶሻል ዴሞክራት ፖለቲከኛ ከዘጠኝ ወራት በፊት አንስቶ የስዊድን ጠቅላይ ሚንሥትር ናቸው።

Wednesday, 15 July 2015

አቶ አበበ ቸኮል ታሰረ

አቶ አበበ ቸኮል ታሰረ
የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ አበበ ቸኮል ታሰረ፡፡ አቶ አበበ አርብ ሀምሌ 3/2007 ዓ.ም የታሰረ ሲሆን ሀምሌ 4/2007 ዓ.ም ቄራ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ ሰሞኑን የታሰሩት የመርከቡ ሀይሌና የደብሬ አሸናፊ ቤት መበርበሩም ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ሀምሌ 8/2007 ዓ.ም ለይግባኝ ጉዳይ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት እነ ወይንሸት ሞላ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን አላየሁትም በማለቱ ለሀምሌ 14/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
በሌላ በኩል በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ በፍቃዱ አበበ የመከላከያ ምስክሮቹ እየታሰሩበት እንደሆነ ገልጾአል፡፡ አቶ በፍቃዱ በመከላከያ ምስክርነት ሊያቀርበው የነበረው ወንድሙ ባንተወሰን አበበ እንደታሰረና ሌሎች የመከላከያ ምስክሮቹም በፖሊስ እየታደኑ እንደሆነ ገልጾአል፡