Tuesday, 25 August 2015

አርበኞች ግንቦት ሰባት ገንዘባችንን ዘረፈው ( ሄኖክ የሺጥላ )

አርበኞች ግንቦት ሰባት ገንዘባችንን ዘረፈው ( ሄኖክ የሺጥላ )
ትግሉ ገንዘብ ያስፈልገዋል ማለት ትግሉ በገንዘብ ነው የሚመጣው ማለት አይደለም። አርበኞች ግንቦት ሰባት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ማለት፣ ገንዘብ ስላዋጣሁ አንገረብን አልፋችሁ ካልሄዳችሁ ውርድ ከራሴ የሚያስብል አይመስለኝም ። ትግል በገንዘብ ይደገፍ ይሆናል እንጂ ፣ ገንዝብ የድል መሰረት ሆኖ ትግሉን ወደፊት አይገፋውም ። ትግሉ ብረት የተሸከሙት ሰዎች ቁርጠኝነት እና መለኮታዊ ዕድል ድምር ነው ። ገንዘብ ያንን ዕድል ማስፈጸሚያ እና አጋጣሚውን መፍጠሪያ ነው ።
ስለዚህ ትግሉ ባለ ድል የሚሆነው በናንተ ድጋፍ ነው ሲባል ፣ የቁስ ብቻ ሳይሆን የመንፈስ መሆኑን አትርሱ። በተጨማሪም ፣ ገንዘብ ስለረዳችሁ ብቻ አርበኞች ግንቦት ሰባት ህወሃትን የማሸነፍ ግዴታ አትጣሉበት ። እናንተም ትግሉ ወደ ድል እንዲቀየር በሃሳብ እርዱ ። ገንዘብ ባለ ድል ቢያደርግ ኖሮ ታላቋ አማሪካ በሄደችበት ባሸነፈች ነበር ። የልጆቹን ወኔ ፣ የአላማ ጽናት እና የሕይወት መስዋትነት ፣ ከባህር ማዶ በጨረታ መሃል በምትረጩት ገንዘብ ልክ አትዩት ። እያደረጋችሁት ያለውን እኔ በበኩሌ አደንቃለሁ ። ግን መዋጮ የቁጣ እና የየት ደረሰ ሊቸንሳ አይመስለኝም ። ሰው ህይወቱን በሚያዋጣበት ትግል ፣ የገንዘብ እርዳታ አድርጎ ያንን እንደ ትልቅ አስተዋጾ መቁጠር የሚፈልግ ካለ ፣ ልክ አይመስለኝም ። እርዱ ፣ ግን ደሞ አትታበዩ ። የምናደርገው ነገር ሁሉ ለራሳችን ነውና !

Tuesday, 21 July 2015

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል


የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል” በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል አባላት ለፕሮፌሰሩ በጋራ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የገለጸው ሻለቃ አክሊሉ፣ ከአባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በሰራዊቱ ውስጥ የታየው መነቃቃት ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲፋጠን፣ በተለይም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ተቀራርቦ የመስራት ድርድር እንዲፋጠን እንደሚያደርገው ሳለቃ አክሊሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል።የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ መድረስ ዜና ይፋ ከሆነ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ህዝብ እየጨመረ መምጣቱንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕ/ር ብርሃኑ ግንቦት7ትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተው ፣ አርበኞች ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ የውህዱ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነዋል። በውህደቱ ላይ ለመገኘት የነበራቸው ውጥን ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ፣ ለመሪነት የተመረጡት በሌሉበት ነው። ይሁን እንጅ በውህደቱ ወቅት ለጉባኤተኛው በስልክ ባስተላለፉት መልክት፣ አንዳንድ ችግሮች ተፈተው በቅርቡ በረሃ ወርደው እንደሚቀላቀሉዋቸው ቃል ገብተው ነበር።
በምርጫ 97 በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከሁለት አመት ላለነሰ ጊዜ በእስር ቤት አሳልፈዋል። ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው በክኔል ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው ከወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።

Thursday, 16 July 2015

ስዊድን፥ ጠቅላይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ መልስ ሆስፒታል ገቡ

ስዊድን፥ ጠቅላይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ መልስ ሆስፒታል ገቡ
የስዊድኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ሽቴፋን ሎፍቨን ከኢትዮጵያ ወደ ስዊድን በመብረር ላይ ሳሉ ስለታመሙ ሀገራቸው ሲደርሱ ሐኪም ቤት መግባታቸውን የሚንሥትሩ ቃል አቀባይ አኔ ኤክበርግ ገለጡ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ አውሮፕላናቸው የስቶክሆልም አየር ማረፊያን እንደነካ በአምቡላንስ በፍጥነት ወደ ሐኪም ቤት መወሰዳቸው ተዘግቧል። አዲስ አበባ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የልማት ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የስዊድኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ወደ ስዊድን ሲበሩ «ብርቱ ማቅለሽለሽ» እንደገጠማቸውም ተጠቅሷል። የጠቅላይ ሚንሥትሩ ቃል አቀባያዋ አኔ ኤክበርግ፣ ሚንስትሩ «የተወሰኑ ምርመራዎች ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ» ሲሉ ለፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ስለጠቅላይ ሚንሥትሩ ኅመም ግን ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የ57 ዓመቱ የሶሻል ዴሞክራት ፖለቲከኛ ከዘጠኝ ወራት በፊት አንስቶ የስዊድን ጠቅላይ ሚንሥትር ናቸው።

Wednesday, 15 July 2015

አቶ አበበ ቸኮል ታሰረ

አቶ አበበ ቸኮል ታሰረ
የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ አበበ ቸኮል ታሰረ፡፡ አቶ አበበ አርብ ሀምሌ 3/2007 ዓ.ም የታሰረ ሲሆን ሀምሌ 4/2007 ዓ.ም ቄራ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ ሰሞኑን የታሰሩት የመርከቡ ሀይሌና የደብሬ አሸናፊ ቤት መበርበሩም ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ሀምሌ 8/2007 ዓ.ም ለይግባኝ ጉዳይ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት እነ ወይንሸት ሞላ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን አላየሁትም በማለቱ ለሀምሌ 14/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
በሌላ በኩል በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ በፍቃዱ አበበ የመከላከያ ምስክሮቹ እየታሰሩበት እንደሆነ ገልጾአል፡፡ አቶ በፍቃዱ በመከላከያ ምስክርነት ሊያቀርበው የነበረው ወንድሙ ባንተወሰን አበበ እንደታሰረና ሌሎች የመከላከያ ምስክሮቹም በፖሊስ እየታደኑ እንደሆነ ገልጾአል፡

Saturday, 11 July 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ እስሩ ቀጥሏል

በአዲስ አበባና በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ እስሩ ቀጥሏል፡፡ ትናንትናው ዕለት በሸዋ ሮቢት የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች የሆኑት አቶ ዘነበ ደሳለኝ፣ አቶ መንግስቱ ተበጀ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሀብቴ እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ አቶ ደብሬ አሸናፊ ታድነው የታሰሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት አቶ መርከቡ ሀይሌና አናኒያ ኢሳያስ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
መርከቡ ሀይሌና አናኒያ ኢሳያስ ዛሬ ሀምሌ 4/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ አራት ኪሎ አካባቢ በፖሊስና ደህንነቶች ተይዘው ታስረዋል፡፡ እነ መርከቡ በተያዙበት ወቅት ፖሊስና ደህንነቶች ‹‹ብጥብጥ ልታስነሱ እየጣራችሁ መሆኑን ደርሰንበታል›› እንዳሉዋቸው ተገልጾአል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ስለሽ ደቻሳ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ከቤቱ በደህንነትና በፖሊስ ታፍኖ ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመበት በኋላ ታስሯል፡፡ ስለሽ ደቻሳ በተፈፀመበት ድብደባም እጅና እግሩ ላይ ስብራት እንደደረሰበት ታውቋል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ የነበረው አስፋው ጀማል በትናንትናው ዕለት በፖሊስ ተይዞ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ መርከቡ ኃይሌና አናኒያ ኢሳያስ በአራዳ ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም ስለሽ ደቻሳ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ እስሩ በየ ክፍለ ሀገሩን የቀጠለ ሲሆን በከፋ ዞን ጨላ ወረዳ 8 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ‹‹ማዳበሪያ አልወስድም ብለዋል›› በሚል ለእስር እንደተዳረጉ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በማዳበሪያ ሰበብ ድብደባ እየደረሰባቸው እንደሆነ የገለጹት የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ነሲብ አደነ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የዞን 9 ጦማርያንን እና ጋዜጠኞችን አስመልክቶ የተሰጠ አጭር መግለጫ

የዞን 9 ጦማርያንን እና ጋዜጠኞችን አስመልክቶ የተሰጠ አጭር መግለጫ
የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ሁለት አባላት እና ሶስት ጓደኞቻችንን መፈታት በመልካም ጎኑ የምንቀበለው ነው፤ ኢፍትሃዊ የሆነውን መታሰራቸውን፣ የስማቸውን መጥፋት ለአካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት መዳረጋቸው ፣ ከትምህርት እና ከሥራቸው መስተጓጎላቸው በቤተሰብ እና በወዳጆቻቸው ላይ የደረሰው እንግልት፣ በቸልታ የሚታለፍ ጉዳይ ባይሆንም ከ10 ተከሳሾች መካከል የአምስቱን ክስ መቋረጥ አዎንታዊ እርምጃ ጅምር ነውና ይበልጥ ሊበረታታ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ክስ የቀረበባቸው ቀሪ የዞን ዘጠኝ አባላት ማለትም ሶልያና ሽመልስ ( በሌለችበት) ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ እና አጥናፍ ብርሃኔ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ተነጥለው እስካሁን መታሰራቸው እና ክሳቸውም አንደሚቀጥል መስማታችን ጉዳዬ አሁንም እጅግ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ ያሳያል፡፡
የአምስቱ ክሳቸው የተቋረጠው ጓደኞቻችን ክስ በእርስ ከሚገኙት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ቀሪ አራት ታሳሪ ጦማርያንን በእስር ለማቆየት የሚሰጥ ማንኛውም ምክንያት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ እኛም በአምስቱ ወዳጆቻችን መፈታት ደስታችንን እየገለጽን አራቱ ቀሪ ጦማርያን እስኪፈቱ ድረስ የዞን9 ጦማርያን ይፈቱ የሚለው ጥያቄያቸን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ይህ መልካም ጅምር አገራችን ጠባብ የፓለቲካ ምህዳር እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መታፈናቸውን እንዲቀይር ተጨማሪ የፓለቲካ እና የህሊና እስረኞችን በመፍታት አንዲጠናከር እየጠየቅን ከዚህ የአገሪቱን መልካም ስም ከሚያጠፉ ድርጊቶች መንግስት ራሱን ቆጥቦ ሁሉም ዜጋ የየራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በሩ ክፍት ይሆን ዘንድ አሁንም ማንኳኳታችንን ይቀጥላል፡፡ ለዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኛ ቤተሰቦች ጓደኞች እና አጋርነታችን ስታሳዩን ለከረማችሁ ብዙዎች በዚህ አጋጣሚ ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን ፡፡
የሽብር ክስ የቀረበባቸው እና የተፈቱትም ሆነ አሁንም ክሳቸው ይቀጥላል ተብሎ በእስር የሚገኙ ጓደኞቻችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
አሁንም ስለሚያገባን እንጦምራለን፡፡
ዞን9

በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ተከፈተው የእስር ዘመቻ ዛሬም ቀጥሏል


በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ተከፈተው የእስር ዘመቻ ዛሬም ቀጥሏል
ዛሬ ሐምሌ 4 2007ዓ.ም ረፋዱ ላይ አቶ መርከቡ ሃይሌ ሰሞኑን ሲከታተሉት በነበሩ ደህንነቶች እና ፖሊስ ታፍኖ ለጊዜው ወደአልታወቀ ቦታ ተወስዷል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ትናንት በኢህአዴግ የታሰረው አቶ ደብሬ አሸናፊ ዛሬ ረፋዱ ላይ ቤቱ በከፍተኛ የታጠቁ ሃይሎች ተከቦ ፍተሻ የተካሄደበት ሲሆን አሁን በጉለሌ አካባባቢ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ተረጋጧል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ታፍነው የታሰሩት በሰሜን ሸዋ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ የነበሩትን አቶ ዘነበ ደሳለኝ፣ የፓርቲው ንብረት ያዥ የሆኑትን አቶ መንግስቱ ተበጀና የቀድሞው አንድነት የቀጠና አመራርና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ቴዎድሮስ ሀብቴ ውጬ አቶ ምንተስኖት ወንዳፈራሁ እና አቶ ብሩ አይደፈር የተባሉ የሰማያዊ አባላት ታፍነው መታሰራቸውን ታውቋል፡፡