Wednesday, 26 November 2014
Tuesday, 18 November 2014
ታሪካችን የደብተራ ነው አላችሁኝ?
በፋሲል የኔያለም (የኢሳት ጋዜጠኛ)
ከዋልን ካደርን ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን። የኢትዮጵያን ታሪክ ማጠልሸት ሰሞኑን እንደ ወረርሽኝ ሆኗል። የኢትጵያን ታሪክ የደብተራ ተረት ነው ብሎ ማጣጣል፣ ደብተራን ከአማራ ጋር ብቻ ማያያዝ ያለማወቅ በሽታ ካልሆነ ምን ይባላል? አለማወቅን ማወቅ ጤና፣ አለማወቅን አለማወቅ ደግሞ በሽታ ነው።
...

ደብተራ ያየውን የሰማውን በከተበ ለምን ይንቋሸሻል? የደብተራ ጥፋቱ አስቀድሞ መሰለጠኑ ነው፤ ፊደል የስልጣኔ በር ነው፤ ደብተራ ደግሞ ፊደል የቆጠረ የመጀመሪያ ሰው ነው፤ የኢትዮጵያ ደብተሮች በጊዜያቸው ከነበሩት ሰዎች አስቀድመው የሰለጠኑ ናቸው፤ ስልጣኔውን ያገኙትም በፊደል በኩል ነው። አስቀድመው በመሰልጠናቸውም፣ ለሁላችንም የሚሆን ነገር ጽፈው አለፉ። ባይሰለጥኑ ኖሮ ታሪክን ለመጪው ትውልድ ስለማስተላለፍ አይጨነቁም ነበር። ከደብተራ ውጭ ታሪክን ለመጪው ትውልድ ጽፎ ስለማስቀረት ያሰበ ማን ነው? ተራው ገበሬ ዝናብ መጣ ሄደ፣ ተራው ነጋዴ አሞሌ ተወደደ ረከሰ፣ ተራው ወታደር ድንበር ሰፋ ጠበበ፣ ንጉስ ግብር ጨመረ ቀነሰ ከማለት ውጭ ታሪክ ጽፎ ስለማስተላለፍ ተጨንቆ ያውቃል? ስለጥበብ ስለውበት ተጨንቆ የጻፈውም ደብተራው ነው።
ደብተራ ባየው በሰማው፣ የጆግራፊ እውቀቱ፣ የእግሩ ጥንካሬ፣ የቀለም አቀባበሉና እድሜው በፈቀደለት መጠን ጻፈ። ሲጽፍ ይጨምራል፣ ይቀንሳል። የጨመረውን የቀነሰውን ማስተካከል ከደብተራ የተሻለ እውቀት ያገኘው የሁዋለኛው ትውልድ ሃላፊነት ነው። ታዲያ እንዲህ ሲባል ደብተራን በማድነቅ እንጅ በማንቋሸሽ አይጀመርም። ኒውተን ጋሊሊዮን አንቋሾ ጥናት አልጀመረም፣ አንስታይን ኒውተንን አንቋሾ አልተነሳም። የኛ ዘመንኛ ጻፊዎች ደግሞ የሁዋላውን አንቋሾ መጀመር እውቀት ይመስላቸዋል። ጽሁፋቸውም በውሃ ላይ እንደበቀለ ተክል የሚሆነው ለዚህ ነው፣ ስር አልባ ነው፤ እፍ ቢሉት እንደ ላባ በኖ ይጠፋል።
አሁን ደብተራ ባይጽፍ ኖሮ ታሪካችን የሰሃራ በታች ካሉት አገራት ይለይ ነበር?። ከሰራሃ በታች ካሉ አገራት በራሱ ቋንቋ ታሪኩን ጽፎ ያስቀረ ከእኛዋ ኢትዮጵያ ውጭ ሌላ አለ? አብዛኛው የጥቁሩ የአፍሪካ ታሪክ የተጻፈው በቅኝ ግዛት ጊዜ አይደለምን? ፈረንጆቹ ለእነሱ በሚጥማቸው መንገድ አይደለም የከተቡት? ምንጫቸውስ ምንድነው? ህንጻዎች እና ቁሳቁሶች አይደሉም? ታዲያ ደብተራ ታሪክ ጽፎ ባስቀረ፣ ድንጋይና ቁሳቁስ ከመፈለግ ባዳነ ለምን ይሰደብ?
ደብተራ ታሪክ የሚጽፈውስ በእኛ አገር ብቻ ነው? የአውሮፓ የጥንት ታሪክ በማን ተጻፈና ነው? የአውሮፓ የታሪክ ወመዘክር ካቶሊክ ቤ/ክ አይደለችም? ስኮላስቲስዝም የሚባለው ታላላቅ ምሁራን የወጡበት የትምህርት ስርዓት የሚመራው በደብተሮች አልነበረምን? የአውሮፓን ታሪክ ከደብተራ ታሪክ መነጠል ይቻላል? የፈረንጅን ደብተራ አቆለጳጵሰን የሃበሻን ደብተራ የምናዋርድበት ምክንያቱ ምን ይሆን? አውሮፓ ውስጥ በኢራስመስ ስም ስኮላርሽፕ የምትመጣው ኢራስመስ ማን ሆነና ነው? የፈረንጅ ደብተራ አይደለም?
ከአገራችን ደብተራ ብንማር ኖሮ ዛሬ እንደ አውሮፓውያን 6 ቢሊዮን ኪሜትር የሚጓዝ መንኮራኩር እናመጥቅ ነበር። ኮፐርኪነከስና ጋሊሊዮ ማን ናቸው? ደብተሮች አይደሉም? የሰማይን ምስጢር ለማወቅ ሰማይ ሲያንጋጥጡ በመኖራቸው የኸው ለዛሬው አስደማሚ የህዋ ምርምር በር ከፈቱ። የእኛዎቹ ደብተሮች ስለአስትሮሎጂ ምርጥ የሆነ እውቀት ቢያከማቹም አጣጥለነው በዘመናዊ መንገድ ሳንማረው ቀረን፤ የማጣጣላችን ውጤትም ፈረንጅ ወደ ላይ ሲመጥቅ እኛ መሬት መሬት እያየን ተቀብረን ቀረን። ዛሬ በየጋዜጣው ጀርባ የምታነበው ሆሮስኮፕ፣ የእኛ ደብተሮች ከዘመናት በፊት ኮከብ ቆጠራ እያሉ ሲያሰሉት የነበረ ነው። ፈርንጅ የተለየ ስም ስለሰጠው እንጅ ስራውና ይዘቱ ያው ነው። ልጅ እያለሁ አንድ ደብተራ ስለ ኮከብ ቆጠራ እና ስለጨረቃ አወጣጥ ቀመር አስተምረውኝ ነበር፤ የደብተራ ትምህርት ዳቦ አያበላም ብየ ሳልገፋበት ቀረሁ። የአገራችን ደብተሮች እምቅ እውቀት ቢኖራቸውም እያጣጣልነው ሳንጠቀምበት ቀረን።
ደብተራ ማለት ፊደል የገደለ ከሆነ ታሪኩን ጽፎ ያስቀረ ስንት የእስላም ደብተራስ አለ? በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ወደ አማርኛ የተተረጎሙ የሃይማኖት መጽሃፍት በአረብ ደብተራ የተጻፉ ናቸው። ደብተራንስ ማነው አማራ ብቻ ያደረገው? የትግሬ ደብተራም ሞልቷል።
ለታሪካችን የምንሰጠው ዝቅተኛ ቦታ ገና ዋጋ ያስከፍለናል፤ ታሪክ አልባነት የሚፈጥረውን ስሜት ለማወቅ ወደ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ሂዱና እዩት። በ20ኛ ክፍለዘመን መግቢያ ፈረንሳይ ውስጥ እነ ሴዳር ሴንጎር ያቋቋሙት ኔግሪቲውድ የሚባል እንቅስቃሴ ነበር። ኔግሪቲውድ የተመሰረተው ፈረንሳይ ጥቁር አፍሪካውያንን ፓሪዛውያን አደርጋለሁ ብላ ወደ ፈረንሳይ ሰብስባ ካመጣቻቸው በሁዋላ ነው። ጥቁር አፍሪካዊያኑ ፈረንሳይ ከመጡ በሁዋላ ሲያዩት ባዶነት ተሰማቸው፣ የሚወራው ታሪክ ታሪካቸው አልመስል አላቸው፤ ታሪካቸውንና ባህላቸውን ፈልጎ ለማግኘት ተነሳሱ፤ ኔግሪቲውድን ፈጠሩ። ያን ጊዜ የነበሩ ጻሃፎች ሁኔታውን ታቡላ ራሳ (tabular rasa) ብለው ይገልጹት ነበር። በግርድፍ ትርጉሙ፣ ባዶ ሰሌዳ ማለት ነው፤ አዎ የመጡበትን ታሪክ አለማወቅ ጭንቅላትን ጥቁር ሰሌዳ ያደርጋል፤ ጭንቅላትህ ጥቁር ሰሌዳ ከሆነ ደግሞ ነጭ ጠመኔ ( ቾክ) እንደፈለገ ይጽፍብሃል። ያን ጊዜ የምታነበንበው ነጩ ቾክ የጻፈልህን ይሆናል። ራስን ለባርነት አሳልፎ መስጠት ይሉሃል ( ይሉሻል) ይህ ነው።

Thursday, 30 October 2014
ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !
ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። “ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ...ከሆነ ትወጣለህ። አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተው” በማለት አማራጭ ቢያቀርቡለትም፣ ሃብታሙ መሞትን እመርጣለሁ የሚል መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣ እየደረሰበት ባለው ስቃይ በጣም እየታመመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ህዝባዊ ሃይሉ ለኢሳት በላከው መግለጫ የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ ‘’ህዝባዊ ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኛና አፋኝ የወያኔ ስርዓት ከህዝብ እና ከሃገራችን ጫንቃ ላይ አስወግዶ በምትኩ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት ጊዚያት በርካታ ስራዎችን በመስራት አስተማማኝ ድርጅታዊ አቋም ላይ ይገኛል’’ ማለታቸውን ጠቅሷል።
የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው ባንድ ድርጅት ጥላ ስር ትግላቸውን አስተባብረው ለመታገል የሚያደርጉትን የውህደት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ባደረሱበት ወቅት ላይ መርቃቱ መደረጉን ያወደሱት ኮማንደሩ፣ የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው እንደሚሆንም ተናግረዋል።
ኮማንደሩ ‘’ስልጠና ለአንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ‘’ በማለት ለስልጠናው መሳካት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ከዚህ ቀደም 4 ተከታታይ ምርቃቶችን ማካሄዱ ይታወሳል።

“እስኪ ትግሉን እናስቀጥላለን የሚሉ ሰዎች ያድኑህ ? “ ሲሉ አሳሪዎቹ በስቃዩ የሚደሰቱ ሲሆን፣ ከባለቤቱ በስትቀር ጠበቃዉም ሁሉ ሳይቀር እንዳያየው ተደርጓል። በተመሳሳይ ሁኔታ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ ፣ በታፈነና አየር በማያስወጣ ክፍል ዉስጥ እንዲታሰር በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተቅማጥና ተያያዥ በሽታ መጋለጡን፣ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ለማወቅ ችለናል።
“የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሃብታሙ አያሌው ፣ በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽ “የግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበት” ሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እን...ግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል።“የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሃብታሙ አያሌው ፣ በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽ “የግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበት” ሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል
ህዝባዊ ሃይሉ ለኢሳት በላከው መግለጫ የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ ‘’ህዝባዊ ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኛና አፋኝ የወያኔ ስርዓት ከህዝብ እና ከሃገራችን ጫንቃ ላይ አስወግዶ በምትኩ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት ጊዚያት በርካታ ስራዎችን በመስራት አስተማማኝ ድርጅታዊ አቋም ላይ ይገኛል’’ ማለታቸውን ጠቅሷል።
የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው ባንድ ድርጅት ጥላ ስር ትግላቸውን አስተባብረው ለመታገል የሚያደርጉትን የውህደት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ባደረሱበት ወቅት ላይ መርቃቱ መደረጉን ያወደሱት ኮማንደሩ፣ የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው እንደሚሆንም ተናግረዋል።
ኮማንደሩ ‘’ስልጠና ለአንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ‘’ በማለት ለስልጠናው መሳካት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ከዚህ ቀደም 4 ተከታታይ ምርቃቶችን ማካሄዱ ይታወሳል።
Monday, 27 October 2014
===========
ከአንዶም ገብረስላሴ
...
ከአንዶም ገብረስላሴ
...
ዓረና ትግራይ ባለፈው ዓመት በዓዲግራት ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበርና የህወሓት ፋሺሽታዊ ተግባር በጠራራ ፀሃይ የተጋለጠበት ኣጋጣሚ መፍጠሩ ያሚታወስ ነው።
በህዝባዊ ስብሰባው እኔ #Amdom,#abraha ፣ato asgede ና ሌሎች ኣባሎቻችን በፖሊሶች ፊት ተደብድበን ህዝቡ በህወሓት መሪዎች የነበረችው ትንሽ ተስፋ ጨርሶ ያጣበት ኣጋጣሚ ነበር።
ዓረና ከዛ ፋሽሽታዊ የህወሓት ተግባር በሗላ በዓዲግራት ከተማ ትልቅ የሚባል ህዝባዊ ማነሳሳት ኣላካሄደም ነበር።
ዛሬ ሰኞ 17 / 02 / 2007 ዓ/ ም የዓረና ኣባላት የፓርቲው ኣማራጭ ፖሊሲዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች የያዘ በራሪ ፅሁፍ ሲያድል ወለዋል።
በዛሬው ቀን የዓጋመና የዓዲግራት ህዝብ በከተማው የተፈፀመው የህወሓት ፋሽሽታዊ ተግባር ክፉኛ እንዳሳፈረውና እንዳናደደው በራሪው ፅሁፍ ስንሰጠው ይሰጠን የነበረ ኣስተያየት ኣመላካች ነበር።
ኣንድ ምሳሌ ልጥቀስላቹ ኣቶ ፀሃዬ የተባለ የድሮ ታጋይና የሰለሞን ሆቴል ባለበት የዓረና ኣባላት በሆቴሉ ኣልጋ ይዘው ኣደሩ።
ጥዋት በራሪ ፅሁፋችን ለማደል ኣዲሱ የዓረና ብርቱኳናማ ቲሸርት ለብሰን ስንንቀሳቀስ ዝምብሎ ያየን ነበር። ትንሽ ረፈድ ሲል ከህወሓት ካድሬዎች ስልክ ተደዉሎ የተለያዩ ዛቻዎች ወረዱበት።
በካድሬዎቹ ዛቻ ክፉኛ የደነገጠው ፀሃየ በሆቴሉ ሻይ ኣዝዞ ለነበረው የዓረና ኣባል በማዋከብና የስድብ ውርድብኝ በማዝነብ ከሆቴሉ ኣስወጣው። ከዚህ ኣልፎም "..ንዓረና ቦታ ኣይንህቦን(ለዓረና ቦታ ኣንሰጠውም)፣ ቃልስና ነዊሕን መሪርን እዩ ዓወትና ናይ ግድን እዩ ( ትግላችን ረዥምና መራራ ነው፣ ድላችን የግድ ነው።.." የሚል በሆቴሉ ደጃፍ ለጠፈ።
ይህ ሁሉ ይከታተሉ የነበሩ ወጣቶች ፀሃየን ክፉኛ በመውቀስ "...እኛ ኣማራጭ እንፈልጋለን፣ እነዚህ ሰዎች የራሳችን ወገኖች ናቸው፣ ከየትም ኣልመጡም የት እንዲሄዱ ነው የምትፈልገው? ባለፈው ዓመት የሰራቹት ኣፀያፊ ተግባር ኣሁንም ለመድገም መሞከራቹ ነው?.." ወዘተ የሚሉ ምክሮች በመለገስና ኣቋሙ እንዲያስተካክል ጥረት ኣድርገዋል።
የህዝቡ ጥያቄ "...ዓረና በዓዲግራት ህዝባዊ ስብሰባ እንዲያካሂድ..." የሚል ነበር። ዓረናም ኣማራጭ ሃሳቡ ለዓጋመና ዓዲግራት ህዝብ በማቅረብ ጠቃሚ የውይይት መድረክ እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብተንላቸው ተመልሰናል።
በዓዲግራት ከተማ በራሪው ፅሁፍ እያደሉ ከነበሩ 3 ቡድኖች የኣንዱ ክንፍ በምስሉ የሚታዩት ናቸው።
በዓዲሱ ዓመት የዓረና በራሪ ፅሁፍ በኣላማጣና ሌሎች 4 የራያ ዓዘቦ ቀበሌዎች፣ ውቕሮ፣ ዓብይ ዓዲ፣ መቐለ፣ ኲሓ፣ ኣይናለም ዛሬም በዓዲግራት ከተሞች ለህዝቡ ኣዳርሷል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው...!
IT IS SO...!

====================
አብርሃ ደስታ ጥላቻን በፍቅር የሚታገል፤ ከስሜት ይልቅ ምክንያት የሚያስቀድም፤ ከብሄርተኝነት ይልቅ ለሰው እና ለሰብአዊነት ልዩ ክብር ያለው፤ የብሄር አጥር በጣጥሶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሁ...ለንተናዊ ለውጥ በጋራ እንዲሰለፍ ብዙ መስዋእት የከፈለ የዘመኑ ዘመናዊ ማንዴላ ነው፡፡
የኔ ትውልድ ካፈራቸው ምርጥና ምጡቅ ፖለቲኮኞ አንዱና ምናልባትም ግምባር ቀደሙ አብርሃ ደስታ ነው፡፡ አብርሽ ኢሰብኣዊነትን በእውቀቱና በብእሩ በሰላማዊ መንገድ ብቻ የሚታገል ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ልክ የ60ዎቹ ትውልድ ተብለው የሚጠሩት እነ ሀይለ ፊዳ፣ ብርሃነ መስቀል ረዳ ፣ ጌታቸው ማሩ ፣ ጥላሁን ግዛው….ምርጥ ወጣቶች ተብለው እንደሚጠሩ ሁሉ አብርሃ ደስታ፣በቀለ ገርባ፣ ሃብታሙ አያለው፣ ….የአሁኑ ትውልድ ምርጥ ወጣቶችና የትውልዱ ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ጀግኖች ሰው አይደለም አይጥም ሳይገድሉ ነው ወደ ወሀኒ የተወረዎሩት፡፡ አንዳች ንብረትም አላወደሙም፡፡ ሀጥያታቸው ፍቅርን መስበካቸውና አምባገነንነትን በማርያም መንገድ መታገላቸው ብቻ ነው፡፡
የስርዓቱ ሰላማዊ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ለማጥመድ ሆንተብሎ የፀደቀው የፀረሽበር ህግ አብርሃ ደስታ ያለ አንዳች መረጃ አጥምዷል፡፡ ፖሊስ እስከ አሁን ያቀረበው ጠብ የሚል መረጃ የለም፡፡ ሁሌ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ እያለ ሰውን እያሸ ነው፡፡ ወጣቱ ፖለቲከኛ በሃሰት ለማስወንጀል በመቀሌ የተደረጉ አሳፋሪ ደራማዎችም አይተናል፡፡ ዓረና ትግራይ ህወሓት ያደረጋቸው እያንዳንዷ እርምጃ እግር በግር እየተከታተለ ነው፡፡ ጊዜው ሲደርስ ከነጭብጦቹ ይፋ ይደረጋል የሚል ግምት አለኝ፡፡
ከወደ ሰሞኑን ደግሞ ለአበርሀ ምግብ እያመላለሰች ስትጠይቀውና ስትከታተለው የነበረች የአክስቱ ልጅ እንዳትጠይቀው ተከልክላለች፡፡ እቺ እህታችን ከዚህ በፊት በሳምንት አንድ ጊዜ እንድታገኘው ተፈቅዶላት ትጠይቀው ነበር፤ አሁን ግን ከእናቱ፣አባቱ፣ወንድሙ፣እህቱ ውጪ ሌላ ማንም ሊጠይቀው አይችልም አንቺም አትችይም ተብላለች፡፡ የአብርሀ ቤተሰቦች ደግሞ ውክልና ለሷ ነው የሰጧት፡፡ ቤተሰቦቹ በሀውዜን ስለሚኖሩ ሊከታተሉትም ሊጠይቁትም አይችሉም፡፡ ልትጠይቀውም ልትከታተለውም የምትችለው በአደስ አበባ የምትኖረው የአክስቱ ልጅ ብቻ ናት፡፡ ከዚህ የተነሳ መላ ቤተሰቡ ተጨንቀዋል፡፡ ይህ ወጣት ፖለቲከኛ ከሌሎች የህሊና እስረኛች በተለየ መልኩ ጫና እየተደረገበት ነው፡፡ ሌሎች በየ ቀኑ እንዲጠየቁ ተፈቅዶላቸው አብርሃ ግን ያቺ በሳምንት አንዴም ተከልክሏል፡፡ እናም ወንድማችን እኛም ቤተሰቦቹም በምን ሁኔታ እንዳለ ማወቅ አልቻልንም፡፡ ብርታቱ እና ፅናቱ ይስጠው፡፡

እስራት የጀግኖቻችን ማጎሪያ በሆነበት ስርዓት እንደ ተሜ አይነት ሀገር ወዳድ የሆኑ ቆራጦች በይስሙላ የፍትሕ ስርዓት በግፍ ወደ ማጎሪያ ማዕከል መግባታቸዉ የስርዓቱን አይን ያወጣ አምባገነንነትና ሗላ ቀርነት ፍንተዉ አድርጎ የሚያሳይ ነዉ።ታድያ ሁሉም ኢትዮዽያዊ በታሰረበት አገር ነጻዉ ማን ነዉ???በኔ ምልከታ ያልታሰረዉ የህብረተሰብ ክፍል ስለ ሀገሩና ህዝቡ ግድ የሌለዉ ብቻ ነዉ።ልብ ይበሉ! ተመስገን የታሰረዉ የመናገር፤የመጻፍ፤ሀሳብን የመግለጽ ዼምክራሲያዊናህገ መንግስታዊ መብት የሚለዉን እንተወዉና ተፈጥሯዊ ወይም ሰብ አዊ መብቱን ተገፎ ነዉ።ሞት ላሳዳጁና ለግፈኛዉ የወያኔ ስርዓት ነጻነት ሳይተነፍስ በቁሙ ለሞተዉ ሰፊዉ ህዝብ
Sunday, 26 October 2014
የኢትዮጵያን የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሰው የገቡ አምስት የሱዳን ሔሊኮፕተሮችና 26 አብራሪዎቻቸው ታስረው መለቀቃቸውን የታጋይ አማረ አረጋዊ ንብረት የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ
ሩሲያ ሠራሽ የሆኑት አምስት የትራንስፖርት ሔሊኮፕተሮች ንብረትነታቸው ተቀማጭነቱ ሱዳን ካርቱም የሆነ ሔሊኮፕተር አከራይ ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው በሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የተመዘገበ ሆኖ፣ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የበረራ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አብራሪዎቹ ግን ምሥራቅ አውሮፓውያን ናቸው ተብሏል፡፡
ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከሦስት ሳምንት በፊት አምስቱ ሔሊኮፕተሮች የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንን ሳያስፈቅዱ ከካርቱም ወደ ባህር ዳር ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ ሔሊኮፕተሮቹን የተከራየው የታንዛኒያ መንግሥት ሲሆን፣ አብራሪዎቹ ዓላማቸው ከካርቱም በኢትዮጵያን አ...ድርገው፣ ኬንያ በመቀጠል ወደ ታንዛኒያ ማቅናት ነበር፡፡ ባህር ዳር አርፈው ነዳጅ ቀድተው ጉዟቸውን ለመቀጠል አቅደውም ነበር፡፡

ይህን ሁሉ ሲያቅዱ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የበረራ ፈቃድ (የኢትዮጵያን የአየር ክልል ለማቋረጥ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ለማረፍ) የሚሰጠውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽንን አላነጋገሩም፡፡ ጉዳያችሁን አስጨርሳለሁ ያላቸውን አንድ የባህር ዳር ነዋሪ በሰጣቸው የመተማመኛ ቃል ብቻ ይዘው፣ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በአማራ ክልል በኩል ጥሰው ገብተዋል፡፡
ጉዳዩን በከፍተኛ ንቃት ሲከታተል የነበረው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሰሜን ዕዝ የአየር መቃወሚያ ክፍል፣ ሔሊኮፕተሮቹን ዒላማ ውስጥ አስገብቶ ሲቃኛቸው እንደነበር ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ባለሙያዎችም በአገር አቀፍ ራዳር ሲከታተሏቸው እንደነበር ታውቋል፡፡
አምስቱም ሔሊኮፕተሮች በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ባህር ዳር ግንቦት 20 ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም አርፈዋል፡፡ ‹‹ሔሊኮፕተሮቹ የሲቪል እንደሆኑ በመታወቁ በተዋጊ ጄቶች ማጀብ አላስፈለገም፤›› ብለዋል ምንጮች፡፡
ባህር ዳር እንዳረፉ ከሔሊኮፕተሮቻቸው በቀጥታ ወደ መኪና ገብተው በኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች ታጅበው ወደ ማረፊያ ቤት መወሰዳቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ባለሙያዎች በአብራሪዎቹ ላይ ምርመራ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አብራሪዎቹ ያለፈቃድ የአንድ ሉዓላዊ አገር የአየር ክልል አልፈው በመግባታቸው የአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር በሚገኘው የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
በተካሄደው ምርመራ አብራሪዎቹ ሌላ ተልዕኮ ኖሯቸው ሳይሆን በተሳሳተ አካሄድ ባህር ዳር አርፈው ነዳጅ ሞልተው ጉዟቸውን ወደ ታንዛኒያ ለመቀጠል በማቀድ ነው የሚል መተማመኛ ላይ በመደረሱ፣ ባለፈው ሳምንት አምስቱ ሔሊኮፕተሮችና 26 አብራሪዎች ተለቀው ከአገር መውጣታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
አብራሪዎቹ የተለቀቁት በዋስትና ሲሆን በቀጠሮአቸው ቀን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አዲስ አበባ የሚገኙ የሱዳን ዲፕሎማቶች አብራሪዎቹን ለማስለቀቅ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ ቢሆንም፣ በዲፕሎማሲያዊ ውይይት መፍትሔ ሊያገኝ እንደሚችል ምንጮች ያላቸውን ግምት ገልጸዋል፡፡
ባህር ዳር አርፋችሁ ነዳጅ እንድትቀዱ ተፈቅዶላችኋል ብሎ ያሳሳታቸው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሔሊኮፕተሮች ነዳጅ የመያዝ አቅማቸው ውስን በመሆኑ ረዥም በረራ በሚያደርጉበት ወቅት በየቦታው በማረፍ ነዳጅ ይቀዳሉ፡፡ አንድ ሔሊኮፕተር በአማካይ በሰዓት 800 ሊትር ነዳጅ እንደሚጠቀም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ኃላፊዎች ስለጉዳዩ የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡ የሱዳን ኤምባሲን በስልክ ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
በ1992 ዓ.ም. ያለፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ የአየር ክልል የገባ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አየር መከላከያ ምድብ በተተኮሰ ቮልጋ ሚሳይል ተመትቶ መጋየቱን ያስታወሱት ምንጮች፤ ‹‹የኢትዮጵያ አየር ክልል እንዲያው ዝም ብሎ ዘው ተብሎ የሚገባበት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡
በዚያን ወቅት አውሮፕላኑን ያበሩ የነበሩ ሁለት የስዊድን ዜግነት ያላቸው ፓይለቶች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ አውሮፕላኑ ከአሜሪካ በኪራይ የመጣ ሲሆን ወደ ሞዛምቢክ እየተጓዘ ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከማቅናቱ በፊት አስመራ አርፎ ነዳጅ ቀድቶ ነበር፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)