Monday, 10 March 2014

የአዉሮፓ ሕብረት የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄን በተመለከተ አንድነትን አነጋገረ
march10/2014

በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እንዲሁም ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣ በነርሱ አነሳሽነት፣ ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አደረጉ።


ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር እንደተነጋገሩ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ባለስልጣናት፣ የአንድነት ፓርቲ በጠራዉ የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ እንዳሳሰባቸው በመገለጽ፣ አንድነት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ፣ ፓርቲው ፍቃደኛ ከሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው፣ ጠይቀዋል።

የአንድነት ፓርቲ ወክለው ከአዉሮፓ ሕብረት ጋር የተነጋገሩት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ሃብታሙ አያሌው በበኩላቸው ያሉትን ሁኔታዎች ለማስረዳት ሞክረዋል።

አንድነት አሁን የሚያደርገው የሚሊዮነሞች ንቅናቄ ከዚህ በፊት ከተደረገው የቀጠለ እንደሆነ ያስረዱት የአንድነት አመራር ፣ ፓርቲዉ አዲስ አበባ ጨምሮ በ17 ከተሞች ፣ በፍትህ እና በላንድ ሪፎርም ዙሪያ ፣ ከሕዝብ ጋር ዉይይቶችን እንዲሁም ሰላማዊ ስለፎች እንደሚያደርግ ገልጸዋል። አንድነት ከዚህ በፊት ባደረጋቸዉ በርካታ ሰልፎች አንዳች አይነት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጹት የአንድነት አመራር አባላት ፣ ወደፊት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ እንደሚሆኑ በማስረዳት ፣ አንድነት አገር አቀፍ መዋቅሩን እያሰፋ እንደሆነም ለማሳየት ሞክረዋል።

የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች፣ አንድነት ይዞት የተነሳዉ የመሬት ጥያቄ ተገቢና ወቃታዊ፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚያመጣ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ በመጪው የ2010 ምርጫ ዙሪያ አንድነት ያለውን አቋም እንዲያስረዳቸው ጠይቀዋል። «ለምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገን ነው። በሁሉም ክልሎች ለፌዴራልም ሆነ ለክልል ተወዳዳሪዎች ከወዲሁ እያዘጋጀን ነው» ሲሉ የመለሱት የአንድነት አመራሮች ፣ በምርጫ መሳተፉና አለመሳተፉ ግን ወደፊት የሚወሰን እንደሆነ ገልጸዋል። «ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር ከዘጋዉና የፖለቲካ ምህዳሩን ካጠበበው. የምርጫ ቦርድ የመሳሰሉ ተቋማት ገለልተኝነት ከሌላቸው፣ ምርጫ መሳተፉ ዋጋ እንደማይኖረዉ የገለጹት የአንድነት አመራራ፣ በምርጫዉ ጉዳይ፣ ኳሷ ኢሕአዴግ ሜዳ ላይ እንዳለች አስረድተዋል።

የፖለቲካ እስረኞችን ሁኔታ የጠየቁት የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች «እስረኞችን ለመጠየቅ ይፈቅድላቹሃል ወይ ? » ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ፣ አንዱዋለም አራጌን አንድ ጊዜ ለመጠየቅ እንደቻሉ ነገር ግን ርዮት አለሙን፣ እስክንደር ነጋ እና ናትናኤል ሞኮንን እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን የአንድነት አመራሮች አስረድተዋል።

በፊታችን ኤፕሪል በብራሰልስ፣ በአዉሮፓ ሕብረት እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል ስብስባ እንደሚደረግ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች፣ የአንድነት ፓርቲ በስብሰባው እንዲገኝ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ በገዠዉ ፓርቲ ዘንድ የፊታችን ምርጫ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል።

የአንድነት አመራሮች ግን ገዢዉ ፓርቲ የሚናገራቸውና ተግባራቶቹ አንድ እንዳልሆኑ፣ ይሄ ነው የሚባል፣ የዲሞክራሲ ግንባታዉን የሚያግዝ የተጨበጠ እርማጃ እንዳልወሰደ መረጃ ላይ በመደገፍ ገለጻ አድርገዉላቸዋል። «ጋዜጦቻችንን ማተም አልቻልም። ደጋፊዎቻችን ይታሰራሉ። ከሥራ ይባረራሉ። ሰልፍና ስብሰባዎች ስንጠራ ብዙ ጊዜ እንግልት ይደርስብናል» ሲሉም በአገዛዙ እየተፈጸሙ ያሉ ከፍተኛ የሰባአዊ መብት ጥሰቶችን ዘርዝረዋል።

በዉጭ አገር ስላሉ ኢትዮጵያዉያንም የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። «በዉጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ወደ 2 ሚሊዮን ይጠጋል። በርካታ ደጋፊዎች አሉን። በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በአሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች አሉን» ያሉት የአመራሩ አባላቱ፣ የድጋፍ ድርጅት ዉስጥ የሌሉ፡ ነገር ግን የምናደርጋቸውን ከፓርቲ በላይ የሆነውን የሚሊየኖች ንቅናቄን የሚደገፉ በርካታ ኢትዮጵያዊ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳሉም አስረድተዋል። የትግሉ አካል ከሆኑና በዉጭ ካሉ ኢትዮጵያዉያን ጋር ለመነጋገር፣ አንድነት የልኩካን ቡድኖች በቅርቡ ወደ ዉጭ እንደሚያስማራም ለአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች ገልጸዋል።

በአገሪቷ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል የተሻለዉና የሰለጠነው አማራጭ፣ መነጋገር እንደሆነ ያስረዱት የአንድነት አመራር አባላት፣ አንድነት ከኢሕአዴግ ጋር ሆነ ሽብርተኞች ተብለው ካልተሰየሙ ደርጅቶች ጋር ሁሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ፍቃደኛ እንደሆነ፣ ለዚያም ጥሪ እንዳቀረቡ ገልጸው፣ አገዛዙ ግን ቅድመ ሁኔታዎች እያስቀጠ በተደጋጋሚ ለመነጋገር ፍቃድኛ እንዳለሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱ ተረጋገጠ
======================

የአፄ ዮሃንስ IV በመተማ የተሰውበት 125ኛ ዓመት ትናንት እሁድ የካቲት 30 ተዘክሮ ዉሏል። አፄ ዮሃንስ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ሲሉ መስዋእት የሆኑበት መተማ አሁን በህወሓቶች ለሱዳኖች (ለድርቡሽ) በሚስጢር ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱ በማስረጃ አረጋግጠናል። በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አከባቢ የነበሩ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች መሬታቸው ለሱዳን ተላልፎ በመሰጠቱ ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት ሌላ ተለዋጭ መሬት የሰጣቸው ገበሬዎች በአካል አግኝቼ አነጋግርያቸዋለሁ። በጣም ብዙ አርሶአደሮች ተለዋጭ መሬት እንደተሰጣቸው አብራርተው የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውም ትክክል መሆኑ መስክረዋል።
...
ይገርማል። አንዳንዱ መሬቱ አሳልፎ ላለመስጠት ይሰዋል። ሌላ ደግሞ የሀገር መሬት በአሮጌ አውሮፕላን ይለውጣል፣ ይሸጣል። ወይ ህወሓቶች! የኢትዮጵያን መሬት እየቆረሱ ለመቸብቸብ ነው እንዴ ስልጣን የያዙ?
በቃ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱ ተረጋግጧል። ዉሳኔው ሕገወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው። መሬታችንን እናስመልሳለን።
በሐረር ትናንት ምሽት ከግምት ከሶስት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ልዩ ስሙ መብራት ሃይል ተበሎ በሚታወቀው የገበያ ቦታ በተነሳ እሳት አደጋ የበርካታ ነጋዴዎች 
ንብረት ከወደመ በኋላ “የእሳት አደጋውን የክልሉ መንግስት ሆን ብሎ ያቀነባበረው ነው” በሚል የአካባቢው ነዋሪ በዛሬው ዕለት ተቃውሞን ለመግለጽ አደባባይ ወጥቶ እሳቱን ለማጥፋት ውሃ ያልነበረው የክልሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ የተቃውሞ ሰልፈኛውን ለመበተን ውሃና አስለቃሽ ጭስ ሲጠቀም ዋለ። የክልሉ ፖሊስም በጥይት ሩምታ በማውረድ፣ በቆመጥ በመደብደብ ሰልፈኛውን ሲበትን መዋሉን ከስፍራው የደረሱ ዜናዎች አመልክተዋል።

Federal police scrambled to arrest female activists [pictures]

March 9, 2014
The notorious Ethiopian government federal police scrambled to arrest female activists, during protest broken out at women’s 5km run. Some of the arrested women are Negest Wondyfra, Woynshet Molla, Weyni Neguse, Emebet Girma, Meron Alemayehu and Mignot Mekonnen are some of the arrested Semayawi party members and supporters (both are female activists).

Sunday, 9 March 2014



ነፃነት እንፈልጋለን ያሉ ሴት እህቶች በአደባባይ ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ 6ቱ ወዲያው ታሰሩ

ሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ቡድን እንደዘገበው ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ የሰቶች ጉዳይ ባመቻቸው እድል የፓርቲው ሴቶች የሮጡ ሲሆን በሩጫውም ላይ የተለያዩ መፈክሮች ማለትም ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትፈታ፤ አቡበከር ይፈታ፣ እስክንድር ይፈታ፣ አንዷአለም ይፈታ፣ ነፃነት እንፈልጋለን እና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች አሰምተዋል::
ከመነሻው የጀመረው የተቋውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሩጫቸውን ጨርሰው ሊገቡ ሲሉ በፖሊሶች ተቆርጠው በአሁኑ ሰዐት ታስረው ይገኛሉ። በሩጫው ወቅት ተቋውሞ ሲያሰሙ የሚያሳይ ቪድዮ እና ፎቶ እንደደረሰን ምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን::
የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሴት አባላት እና ከእናርሱ ጋር የነበሩ ሴቶች በዛሬው እለት በተካሄደው ሩጫ ላይ ተሳትፈው ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ አንዳሉ በሩጫው መጨረሻ ላይ በፖሊስ ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአከባቢው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ጌታነህ ሴቶቹ መታሰራቸው ምንም አግባብነት እና ህጋዊ መሰረት የለውም በማለታቸው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የእስረኞች ስም ዝርዝር
1 ንግስት ወንድይፍራ(የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ)
2 ወይንሸት ሞላ (የምክርቤት አባል)
3 ወይኒ ንጉሴ(አባል)
4. እመቤት ግርማ(አባል)
5. ሜሮን አለማየሁ (አባል)
6. ምኞት መኮንን(አባል)
ለጊዜው የሴቶች ጉዳይ እና የህግ ጉዳይ ኮሚቴ የሆኑት ኢየሩስ ተስፋው እና ኤልሳ ወሰኔ ያሉበትን ልናውቅ አልቻልንም፡፡
ከነዚህ ሴቶች በተጨማሪም በቦታው የነበሩት የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አቶ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ እና የህዝብ ግንኑነት ኮሚቴ አቶ አቤል ኤፍሬም ናቸው፡፡
እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ አቤል ኤፍሬም በአካባቢው ስለነበሩ ብቻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉበትን ለማጣራት የሰማያዊ ወጣት ክንፍ አባላት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናችንን እያስታወቅን የደረስንበትን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡
ትግሉን በእስራት እና በግድያ ማስቆም አይቻልም::
 

Saturday, 8 March 2014

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሴቶች ክፍል በዛሬው እለት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8, 2014 ምክንያት በማድረግ ዝግጅቱን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።

ዝግጅቱ ከቀኑ 11፡00በዲሞክራሲያዊ ለውጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሊቀመንበር አጭር ንግግር አድርገዋል። ሴቶቹም በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች እህቶቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የሰብአዊ መብት እረገጣ በማጋለጥና በመቃወም ገንቢ ውይይት ያደረጉ ሲሆን የድርጅቱ የሴቶች ክፍል ሰብሳቢ የመግቢያ ንግግር እና ጣይቱ ቡጡልን የሚያስታውስ ግጥም አቅርበዋል በመቀጠል ምክትል ሰብሳቢዋ እንዲሁ አድዋን በተመለከት አጠር ያለ ግጥም እና አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ አጭር ገለፃ አቅርበዋል በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ግጥሞች እና ንግግሮች እንዲሁም አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ጭውውቶች ፤ የጥያቄና መልስ ጊዜም ነበር። በተጨማሪ የምሳና እና ሻይ ቡና ግብዣ አድርገዋል በዚህ ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በእንግድነት ታዳሚያችን ነበረች።

መቀጠል ከ14፡00 ጀምሮ አጠቃላይ ኖርዌጅያን እና በኖርዌ የሚኖሩ ሴቶች በሙሉ በአሉን በጋራ በሚያከብሩበት ቦታ በመሄድ በተለያዩ የአረብ ሃገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ ህይወታቸው ላለፈውና ለሚሰቃዩ ሴቶች እህቶቻችንን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ እና የሻማ ማብራት ስነስርአት የተከናወነ ሲሆን ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ በዝግጅቱ ላይ በእንግድነት ተገኝተው ሴቶችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል የተለያዩ ሴቶች እህቶቻችንም በቦታው በመገኘት ንግግርና አስተማሪ ግጥሞችን አሰምተዋል። ኢትዮጵያውያን ሴቶቹ በሃገራችን በሴቶች እህቶች ላይ የሚደርሰውን ያላግባብ እንግልት እና እስር እንዲቆም በተለይ ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ከእስር እንድትለቀቅ እና በቂ ህክመና የማግኘት መብቷ እንዲከበር የርዮትን ምስልና በተለያዩ አረብ ሃገራት እድሜያቸው ለስራ ያልደረሱ ሴቶችን ለሽያጭ ማቅረቡን የኢትዮጵያ ገዢው መንግስት እንዲያቆም እንዲሁም በየአረብ ሃገራቱ በግፍ ህይወታቸው ላለፈው ዜጎቻችን እና እየተሰቃዩ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተጠያቂው የወያኔ መንግስት መሆኑን የሚያጋልጡ መፈክሮችምን በመያዝ በኢዮጵያ ውስጥ በሴቶች ላይ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለአለም በማጋለጥ የመጨረሻውን የእግር ጉዞ ፕሮግራም በመካፈል ዝግጅቱ በ17፡00 ተጠናቋል።

Friday, 7 March 2014

ሰሞኑን የወያኔወች ተላላኪ ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳን ጋር በድንበሩ ጉዳይ እየተዳደረና ተግባራዊ እያደረገ ያለው የቀድሞወች የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት እና የደርግ መንግስት ተፈራርመውት የነበረውን ነው ብሎ ተናግሮት የነበረውን አስመልክቶ የደርግ መንግስት ከሱዳን ጋር ምን የተፈራረመው ነገር አለ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ መንግስቱ ኃይለማርያም መስል ሲሰጡ ምንም የተፈራረምነው ነገር የለም ብለዋል:: ሊንኩን በመጫን ያድምጡት
 http://youtu.be/HbilEYVjxZ4