የወገኖቻችን ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን፤ ለመፍትሔውም በጋራ እንነሳ!
የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ
በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ በከተማዋ ዙርያ ያሉ ወገኖቻችንን ማፈናቀል በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የሚፈናቀሉ ገበሬዎች የሁላችን ወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች ናቸው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የምንፈናቀለው ሁላችንም ነን። ይህን መሰሪ ፕላን በመቃወም ላይ ያሉት የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
በዚሁ ወቅት በጎንደር ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ ተከስቷል። ህወሓት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ያጎረበት እስር ቤት በእሳት ሲጋይ ዜጎች ተቆልፎባቸው እንዲነዱ ተደርጓል። ከእሳቱ በእድል ያመለጡት በጥይት ታድነዋል። ኢትዮጵ...ያዊያን እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የሚያውቁት በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ነው። ይህን ጥቃት በመቃወም ላይ ያሉ የአማራ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
ግፍ ያልተፈፀመበት የኢትዮጵያ ክፍል ባይኖርም ሰሞኑን በአማራና በኦሮሚያ ላይ በርክቷል። በሁለቱም የአገራችን ክፍሎች የንፁሀን ደም እየፈሰሰ ነው፤ በሁለቱም ቦታዎች የእናቶች ዋይታና እሪታ ጎልቶ እየተሰማ ነው። የህወሓት አገዛዝ የትውልድ ቦታ፣ ቋንቋና ዘር ሳይለይ በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ላይ የተደቀነ አደጋ መሆኑ ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ ግልጽ ሆኗል።
ለዚህ የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው? ዛሬም ኦሮሚያ ውስጥ የሚፈፀመው በደል የኦሮሞ፤ አማራ ውስጥ የሚፈፀመው በደል የአማራ ጉዳይ አድርገን እንወስዳለን? መቸ ነው ኦሮሚያ ላይ ለደረሰው ጥቃት አማራዉ፤ አማራ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኦሮሞው የሚቆረቆረው?
የሁላችን የጋራ ጠላት የሆነው ህወሓት መኖሩ በዘውግ የተከፋፈለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ አንድነት የሚያመጣ ታላቅ ኃይል ሊሆን ይገባል። ይህ የመከራና የመጠቃት ወቅት የምንቀራረብበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ይህ የመከራ ወቅት በህወሓት ላይ በጋራ የምንነሳበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ማኅበረሰቦች በሙሉ በፀረ-ህወሓት ትግል መቀናጀት ይኖርባቸዋል። ይህ ማድረግ ግዴታችን ነው።
ለችግሮቻችን መፍትሄ የምናገኘው ችግሮቹ ከተፈጠሩበት እርከን በላይ ሆነን ስናስብ እንጂ ችግሮቹ በፈጠሩበት ደረጃ ላይ ቆመን መሆን አይችልም። ችግሮቹ ከተፈጠሩበት እርከን በላይ ለመሆን አገር አቀፍ እይታ መኖሩ እጅግ ተፈላጊ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ሁሉ በተለይም የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን ይህንን ጉዳይ አበክረው እንዲያስቡበት አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያሳስባል።
ግፍ ሞልቶ የፈሰሰበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሆኑት ሕፃናት በፌዴራል ፓሊስ ጥይት የሚገደሉበት አሳዛኝ ወቅት ላይ ነን፤ ዜጎች በር ተዘግቶባቸው በእሳት እየጋዩ ነው። ሰፊ እና ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን በስጦታነት ለመስጠት ዝግጁቱ የተጠናቀቀበት ወቅት ላይ ነን። ከአስር ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተርቧል። በፍትህ እጦት እስር ቤቶች በንፁሃን ዜጎች ተሞልተዋል። ውሀ፣ መብራትና የቴሌፎን አገልግሎት ብርቅ ሊሆኑ ነው። ይህ ሁሉ እየሆነ ግን የሥርዓቱ አገልጋዮችና ደጋፊዎች በህንፃ ላይ ህንፃ እየገነቡ በድሀው ላይ ይሳለቃሉ። የህወሓት አገዛዝ ድህነትን፣ ችጋርን፣ ስደትን፣ የእርስበርስ ግጭቶችን እያባባሰ ኢትዮጵያን እየጋጠ የሚኖር አገዛዝ ነው። አገዛዙ በቀደደልን ቦይ ከተጓዝን ችግሮችን ማባባስ እንጂ ማርገብ እንኳን አንችልም። ይህንን ሥርዓት በቃህ ማለት የአማራ ወይም የኦሮሞ አጀንዳ አይደለም፤ ይህ የሁላችንም - የኢትዮጵያዊያን - ጉዳይ ነው።
ለቀምት፣ ሀረር፣ ሱልልታ እና ሌሎች በርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ለደረሱ ጥቃቶች ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ፣ አሶሳ፣ ሁመራ፣ ጋምቤላ ውስጥ ተቃውሞ መሰማት አለበት። በጎንደርና ባህርዳር ለደረሰውም ጥቃት አዳማ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና፣ ጅግጅጋ፣ አክሱም ላይ ተቃውሞ መሰማት አለበት። በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ለሚደርሰው በደል መላዋን ኢትዮጵያ ሊያሳምም ይገባል። መከፋፈላችን መከራችን አብዝቶታል፤ የህወሓት እድሜን አርዝሟል፤ ይብቃ!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የመከራ ጊዜዓችን እንዲያጥር በዘውግ ሀረግ፣ በብሔርና እና በሀይማኖትና ሳንታጠር የወገናችን ህመም ይሰማን፤ ተሰምቶንም ለጋራ ትግል እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Thursday, 3 December 2015
Wednesday, 2 December 2015
ለነፃነት፣ለማኅበራዊ ፍትህ ፣ ለዲሞክራሲ..
በጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ
ለነፃነት፣ለማኅበራዊ ፍትህ ፣ ለዲሞክራሲ.. ስፍነት ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተካሄደ ያለዉ የፀረ ጭቆና ትግል እስከዛሬዋ ቀን ድረስ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ለወደፊትም የሕዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ እስከሚያገኝ አይቆምም፡፡ በሠላማዊም፣ በትጥቅ አማራጭም፡፡
በማንኛዉም መልክ ለሚካሄደዉ ትግል ስኬታማነት ግን ድርጅት/አደረጃጀት ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡አንድ ሕዝብ ምንም ያህል በጭቆና ማጥ ዉስጥ ቢዘፈቅ፣ምንም ያህል ጨቋኞችን ቢጠላ፣ምንም ያህል ቢጮህና ቢንጫጫ እስካልተደራጀ ድረስ የቱንም ወንዝ አይሻገርም፡፡ ጩኸቱ ሁሉ የቁራ ጩኸት፣ሥራዉ ሁሉ የእምቧይ ካብ ይሆናል፡፡ በሥርዓት ያልተራጀ ዜጋ፣በሥርዓት ያልተቀናጀ ትግል በየትኛዉም የሰዉ ልጅ የትግል ታሪክ አሸንፎ አያዉቅም፡፡
የሀገራችንንም የቅርብ ጊዜ የተቃዉሞ ልምዶችን በአብዛኛዉ ብንመለከት ...አወቃቀራቸዉ ከላይ ወደታች እንጂ ከታች ወደላይ ስለአልነበረ ኃይለኛ ነፋስ በሚመጣበት ጊዜ መቋቋም እያቃተዉ ለመንገዳገድ ብሎም ለመናድ ሲበቃ አስተዉለናል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች ተነሳስተዉ ለተቃዉሞ አደባባይ ይወጣሉ፤ከአገዛዙ የታጠቀ ኃይል ጋር ይጋጫሉ፤ሰዉ ይገደላል፤ሰዉ ይቆስላል…ሌላዉ ወደየቤቱ ይመለሳል፡፡
ነገ ሌላ ቦታ ሌላ ተቃዉሞ ይነሳል፤ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰድበትና ይዳፈናል፡፡እንዲህ…እንዲህ እያለ ለዛሬዋ ቀን ደርሷል፡፡ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በምዕራብ ኦሮሚያ ሕዝቡ በአገዛዙ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ በአደባባይ እየገለፀ ያገኛል፡፡ አግባብና ሊደገፍ የሚገባ ትግል ነዉ፡፡
ይሁንና ዛሬም እንደትናንት፣ምዕራቡ ሲጮህና ሲሞት፣ ምስራቁ ዝም የሚል ከሆነ፣ ደቡቡ ሲፋለም፣ ሰሜኑ ‹‹በእኔ እስካልመጣ…››ብሎ የሚሳለቅ ከሆነ፣ አሁንም ሆነ ወደፊት በለስ ከባለጠመንጃዉ ጋር ነዉ፡፡ ትርፉም መስዋዕትነትን ማብዛት ይሆናል፡፡ስኬታማ ትግል በአነስተኛ መስዋዕትነት ድል የሚመዘገብበት መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ ዋናዉን እየበላ ትርፍ የሚያሰላ ተላላ ነጋዴ መሆን ነዉ፡፡
በሌላ በኩል፣ ትግሉን ከርቀት ሆነዉ የሚያንቀሳቅሱ ወገኞች ካሉ፣ ጥረታቸዉን ማድነቅ እንደተጠበቀ ሆኖ ማድረግ ያለባቸዉን ሁሉ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ያደርጉት ዘንድ መጠየቅም አግባብ ይመስላል፡፡ ለጋ ወጣቶች ሕይወታቸዉን ዋጋ የሚከፍሉበትን ትግል ለወሬ ፍጆታ ፋይዳ ብቻ ዘላቂ ጥቅም ወደሌለዉ አቅጣጫ መግፋት እንዳይኖር መጠንቀቅ የሚያስችል የሞራል ብቃት ሊኖር ይገባል፡፡
በስልታዊነት/በስሌታዊነት እንጂ በስሜታዊነት የሚደረግ ግፊትም ሆነ የሚወሰድ እርምጃ ዉጤቱ ፀፀት ይሆናል፤የሕዝብን መከራና የገዥዎችን ዕድሜም ያራዝማል፡፡
ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር/structure ፣ስልታዊ አመራር(በቅርበትም በርቀትም)…ስሜታዊ ሳይሆን ስሌታዊ የሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ/ተቃዉሞ…ለዉጤታማ ድል እንደሚያበቃ እያሰብን፣ ‹‹Aluta continua!›› እንላለን፡፡

Tuesday, 1 December 2015
የጎንደር ማረሚያ ቤት በእሳት ጋየ እስረኞችም ተገደሉ
የጎንደር ማረሚያ ቤት በእሳት ጋየ እስረኞችም ተገደሉ
በጎንደር ከተማ የሚገኘውና ባሕታ በመባል የሚጠራው ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ማረሚያ ቤቱ ከፍተኛ የሆነ አደጋ የደረሰበት ሲሆን ቁጥራቸው ከ30 እስከ 50 የሚሆኑ ታራሚዎች መገደላቸውንና ከ300 እስከ 500 በላይ የሚሆኑ እስረኞች ደግሞ አምልጠው ከሕዝቡ ጋር ሲቀላቀሉ ከ100 በላይ የሚሆኑት እስረኞች በእሳት ቃጠሎው ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፌዴራል ፖሊሶች ከውስጥና ከውጭ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ታራሚዎችን መገደላቸውና መውጫ አጥተው በእሳት ቃጠሎ እያረሩና እየነደዱ መሆኑን የዓይን እማኞች ይናገራሉ። የፌደራል ልዩ ኃይልና የወሕኒ ቤቱ ፖሊሶች ቃጠሎውን ከማጥፋት ይልቅ በእስረኞቹና በነዋሪው ላይ በኃይል አሰቃቂ እርምጃዎችን በመ...ውሰድ አደጋውን የከፋ አድርገውታል። ሕዝቡ አንፈልጋችሁም ለቃችሁ ውጡልን ልጆቻችንን አትግደሉ በማለት ቁጣውን እየገለጸ ነው።ሞት ለወያኔ! ሞት ለብአዴን! የሚሉ መፈክሮች በማንገብ ሕዝቡ ደጀንነቱን አሳይቷል። ጎንደር የጦር ቀጠና ውስጥ ስትሆን ሕዝቡ የእስረኞቹን ሕይወት ለመታደግ አስፈላጊውን መስዋዕትነት መክፈሉን ቀጥሏል።የታራሚዎቹ ቤተሰቦች እና የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ በሆነ ሃዘን ውስጥ ከመርውደቃቸው በተጨማሪ የጉዳቱን መጠን በውል ማወቅ አልተቻለም። ተጨማሪ ጦር ከአዘዞና ከልዩ ልዩ ቦታዎች በመኪና ተጭኖ እየመጣ ነው፡፡እስረኞች ሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ በእሳት ይጋያሉ፣ ይገደላሉ፣ ታስረው እየተደበደቡ ከፍተኛ ስቃይና ግፍ እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ።እስከ አሁን ድረስ የክልሉ መንግስትና የፌደራል መንግስት ምንም ዓይነት መግለጫ አልሰጡም።

Sunday, 29 November 2015
ህወሀት ''ቅማንት'' የሚል አደገኛ ካርድ ስቧል
መሳይ መኮንን
ህወሀት ''ቅማንት'' የሚል አደገኛ ካርድ ስቧል። በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተፈጽሟል ለማለት የሚከብድ እጅግ ዘግናኝ ድርጊት ተፈጽሟል። የማንነት ጥያቄ ተገቢ ቢሆንም በህወሀቷ ኢትዮጵያ ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን ነው። የዲሞክራሲ ጥያቄ ባልተመለሰበት ሁኔታ፡ የማንነት ጥያቄ የጨቋኞችን ዕድሜ የሚያራዝም መድሃኒት ነው። ህወሀት ዲሞክራሲን ሊያመጣ ፈጽሞ የሚችል ድርጅት አይደለም። አፈጣጠሩና እወክለዋለሁ የሚለው ህዝብ የአናሳ ቁጥር ያለው በመሆኑ ከዲሞክራሲ መርህ(Majority rule-Minority right) ጋር የሚጻረር ነው።ቢፈለግ እንኳን አይቻለውም።
ለዚህም ነው የማንነት ጥያቄን በየቦታው እየቀሰቀሰ ህዝብን ከህዝብ እያናከሰ በስልጣን ላይ መቆየትን የመረጠው። እንዲህ አድርገን ካልገዛን በቀር ስልጣን ላይ መቆየት አንችልም ብለው ሟ...ቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በድብቅ የተናገሩት እንዳለ ነገ ከነገ ወዲያ ይጋለጣል።
እናም ህወሀት ዘንድሮ የሳባት የቅማንት ካርድ መጥፎ አየር ይዛ መጥታለች። በጣም አሰቃቂ በሆነ መልኩ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ቪዲዮ በማህበራዊ መድረኮች ተለቋል። ተመልክቼው ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ደንግጬአለሁ። ከመነሻው ሂደቱን ስንከታተል ስለነበረ ማን ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት ጀርባ እንዳለ በሚገባ ተረድተነዋል። ኢትዮጵያውያን ከምንጊዜውም በላይ ጥንቃቄ ልናደርግ የሚገባን ግዜ ላይ ደርሰናል። ድንበሩን ለማስረከብ በመጪው ወር ቀጥሮ ተይዟል። በጎንደር ዘግናኝ ድርጊት እየተፈጸመ ነው።
እነዚህ ሁለት ክስተቶች በአንድ ወቅት ላይ እንዲሆኑ የተደረገው ያለምክንያት አይደለም። ስለድንበሩ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጹን እንዳያሰማ በመንደርና ጎጥ ተከፋፍሎ ሁሉም በየሰፈሩ እርስ በእርሱ እየተጠባበቀ፡ አጥር ሰርቶ፡ እየተደገዳደለ እንዲኖር አድርገውታል። በድንበሩ ጉዳይ ከሱዳንና ከህወሀት ወታደሮች ጋር እየተዋጋ የከረመው ይኧው የጎንደሩ ኢትዮጵያዊ ነው። ይህ ህዝብ ለድንበር ማካለሉ እንቅፋት እንዳይሆን ደግሞ ህወሀት ሌላ ካርድ ስቧል። የቅማንት የማንነት ጥያቄ። ጥያቄው ተገቢ አይደለም እያልኩኝ አይደለም። በህወሀት ተቀናብሮ ይህን ጊዜ ጠብቆ መነሳቱ እንጂ።
ጎንደር ሰሞኑን በተከሰተው ዘግናኝ ድርጊት ተወጥራለች። ለመጪው ሌላ የዕልቂት ዳመና አርግዟል። በመሃል የድንበሩ ማካለል ተፈጻሚ ይሆናል። ምን ይበጃል?
ድንበሩ የጎንደር ብቻ አይደለም። በስለት ተከታትፎ እየተገደለ ያለው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ነው። እኔ እዚህ ቪዲዮውን መለጠፍ አልፈለኩትም። በየቦታ ስላለ ማየት የሚቻል ይመስለኛል።
ኢሳት ይህን የህወሀት የዕልቂት ድግስ ለማክሸፍ የሚቻለውን ያደርጋል። እንደ ዜጋ፡ እንደ ኢትዮጵያዊ፡ ከምንም በላይ እንደ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር፡ እኔም አቅሜና ሙያዬ በሚሰጠኝ ጉልበትና ዕድል ተጠቅሜ ይህን ኢትዮጵያውያን ላይ የተወረወረውን የጥፋት ሰይፍ ለመመከት ቃል እገባለሁ። ጎበዝ እንደ ትውልድ የምንፈተንበት ዘመን ላይ ነን። መሃሉ ላይ ነን። ወጀብ ከግራና ቀኝ ይዞናል። ተያይዘን ካልወጣን መሃሉ ላይ እንቀራለን። .....ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን ይታደጋት!!!!

Saturday, 28 November 2015
አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ከሳሽም ምስክርም ሆኖ ፍ/ቤት ቀረበ
አንጋፋው ተዋናይ አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም በሽርክና የሚያሳትመውን የመረጃና የስልክ አድራሻ ማውጫ ዳይሬክተሪ፤ አመሳስለው በማዘጋጀት ለገበያ አቅርበውብኛል ባላቸው አካላት ክስ መስርቷል “እንደ ልጄ የማየውን ሥራዬን ነው የወሰዱብኝ” ብሏል – አርቲስቱ፡፡
በአቃቤ ህግ የቀረበው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው፤ ዌብ ፕላኔት አይቲ ሶሉሽን እና ስራ አስኪያጁ አቶ ዳንኤል ታፈሰ በ1999 የንግድ ፍቃድ የተሰጠው የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የኪነ ጥበብና የማስታወቂያ ስራዎች ድርጅት፣ “የኢትዮጵያ የመረጃ እና ግብይት ዳይሬክቶሪ” የተሰኘ የአድራሻና የመረጃ ዳይሬክትሪን የመረጃ ቅንብር (ዳታ ቤዝ) በማመሳሰል፣ “National Info and Business Directory” በሚል ርዕስ አዘጋጅቶ በ117 ሺህ ብር የማስታወቂያ ክፍያ በመሸጥ በተበዳይ ላይ ጉዳት አድርሰዋል::
ተከሳሹ የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው ዳይሬክተሪውን አሳትመው ማሰራጨታቸውም በክሱ ተጠቅሷል፡፡ አቃቤ ህግ 7 የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ባለፈው ማክሰኞ ሰባቱም ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከአቃቤ ህግ ምስክሮች አንዱ ሆነው የቀረቡትና በአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የኪነ ጥበብና ማስታወቂያ ድርጅት ውስጥ የ50 በመቶ ድርሻ ያላቸው ኢ/ር ብስራት ዳንኤል በሰጠው ቃል የዳይሬክተሪውን ሙሉ የመረጃ ቅንብር (ዳታ ቤዝ) እሳቸው እንዳዘጋጁት ጠቁመው፣ ተከሳሽ የመረጃ ቅንብራቸውን ሙሉ ለሙሉ በመገልበጥ ማሳተማቸውን ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮ 4 ተከታታይ ህትመቶችን ማውጣቱን የገለፁት ምስክሩ፤ የተወሰደባቸው የመረጃ ቅንብር ለ2012/13 እ.ኤ.አ ያዘጋጁት ሲሆን ተከሳሹ ለ2014/15 በሚል ወቅታዊ አድርገው ማሳተማቸውን አስረድተዋል፡፡
ሐምሌ 20 ቀን 2006 ዓ.ም ህትመቱን ከቻይና ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቡት ተከሳሹ፤ ነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከጉምሩክ በማስወጣት፣ ማሰራጨት መጀመራቸውን ምስክሩ ጠቅሰው ለተለያዩ ድርጅቶች በአጠቃላይ በ117ሺ ብር አሰራጭተዋል ብለዋል፡፡ የተከሳሹ ዳይሬክተሪ በድርጅታቸው ከሚታተመው ዳይሬክተሪ ጋርም በስያሜ፣ ውስጥ ባሉ መረጃዎችና አቀማመጣቸው፣ በወረቀትና ቀለም አጠቃቀምና በማስታወቂያ አቀማመጥ እንደሚመሳሰሉ ተናግረዋል፡፡
ተከሳሹ፤ በአርቲስት ፍቃዱ ድርጅት ውስጥ የሽያጭ ሰራተኛ አስተባባሪ ሆነው ይሰሩ እንደነበር ያስታወሱት ምስክሩ፤ በ2002 ከድርጅቱ ከወጡ በኋላ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን የማስገባት ፍቃድ እንጂ የማስታወቂያ ስራ ፍቃድ ሳይኖራቸው ነው ዳይሬክተሪውን ያሳተሙት ሲሉ ለፍ/ቤቱ አብራርተዋል፡፡ ተከሳሹ ጉዳዩ በፍ/ቤት ተይዞ ሳለም ሁለተኛ ህትመት ማሳተማቸውንም ምስክሩ ተናግረዋል፡፡
ሁለተኛ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆኖ የቀረበው ራሱ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ሲሆን፤ “ከቲያትር ስራ ጡረታ ከወጣሁ በኋላ መጦሪያዬ ይሆነኛል ያልኩትንና እንደ ልጄ የማየውን ስራዬን ነው ተከሳሽ የወሰዱብኝ” ብሏል፡፡ “ስምንት ዓመት የለፋንበትን ነው ገልብጠው ያሳተሙብን” ያለው ምስክሩ፤ ስራችን የመንግስት አካላት ተገቢ እውቅና የሰጡበት ነው ብሏል፡፡
ፍ/ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን በሙሉ ካደመጠ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከሉ በማለት ምስክሮችን ለመስማት ለጥር 3 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

Addis Admass
Friday, 27 November 2015
የሴም ዘር ማን ነው? የኩሽ ዘርስ የቱ ነው? ሐበሻ የሚባሉትስ እነማን ናቸው?
በከተማ ዋቅጅራ
ኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ ከአንዱ የተለያየን አድርጎ ማቅረብ አሁን አሁን በሰፊው እየተሰማ ነው። ኢትዮጵያ ብዙ የሚባሉ የታሪክ ሙሁራን ቢኖራትም ሙህራኑ በአገር ጉዳይ በያገባኛል መንፈስ በአንድነት ተሰባስበው ከመመካከር እና ከማስተማር ይልቅ ዝምታን መርጠዋል። የኢትዮጵያን እውነተኛውን ታሪክ ለህዝባቸው ከማሳወቅ ችልተኝነት ማሳየታቸው ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ እየሰራ ያለው ወያኔ ያስደስት ይሆናል። ወያኔ አሁን አሁን እየተከተለ ያለው የአረብ አብዮትን ነው። አረቦች ጥያቄአቸው እንዲመለስላቸው የሚፈልጉት በሁከት ነው። ግዛታቸውንም ማስከበር የሚፈልጉት በሁከት ነው። ሃሳባቸውን ሌላው እንዲቀበላቸው የሚፈልጉት በማስፈራራት እና በሁከት ነው። እየገደሉ ሞተብን ብለው ይጮሃሉ እያፈነዱ አፈነዱብን ብለው ይናገራሉ በሁሉ ነገር በደል ፈጻሚ ቀዳሚዎቹ እነሱ ሆነው ሳለ ምላሽ የሚሰጣቸውን አገር አረብን ሊያጠፋ ነው ብለው ሁሉም እንዲነሱላቸው ማሳደም መቀስቀስ ይጀምራሉ አንድ ችግር ሲያጋጥማቸው ይሄንን ያደረሱብን እንደዚህ የምትባል አገር እና እንደዚህ የተባሉ አገር ናቸው ብለው በራሳቸው የተፈጠረውን ጥፋት ከማመን ይልቅ ወደሌላ አገር ላይ በመለጠፍ አረብ አገር በሙሉ እና ወዳጅ አገሮታቸውን ጥላቻ እንዲቀረጽባቸው አድርጎ መመረዝ ነው። ወያኔም እየሄደበት ያለው አካሄድ ይሄንኑ ነው።
ኢትዮጵያ መሽቶ በነጋ ቁጥር አዳዲስ ነገሮችን የሚሰማባት አገር ሆናለች። እድሜ ለወያኔ በዘር ፐውዞ ፐውዞ አንተ አበሻ ነው እኔ አበሻ አይደለሁም። አንተ ሴም ነህ እኔ ኩሽ ነኝ። አንተ እንደዚህ ነህ እኔ እንደዚ አይደለሁም። አንተ ከገሌ ወገን ነህ እኔ ከእገሌ ወገን አይደለሁም የሚል ጫጫታ በስፋት እየተሰማ ይገኛል። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት የተማረው እና ታሪክ ጠንቅቀው የሚያውቁት ሙህራኖች በአንድላይ ተሰባስበው ስለ አገር በማሰብ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር እውነተኛውን ታሪካችንን ከማስተማር እና ከማሳወቅ ይልቅ ዝምታን በመምረጣቸው የተነሳ ወያኔ እና መድረኩን የፈቀደላቸው የማያውቁትን ታሪክ የየራሳቸውን ሃሳብ በማንጸባረቅ በተደጋጋሚ እየተነገረ እና በመጽሃፍም ጭምር እውነትነት የሌለው ታሪክ አስመስለው እየተጻፉ በመሆኑ እንደዚህ የተዛቡ ታሪኮች ሲነገር በአጉል ተስፋ ሰዎችን ስለሚሞላቸው የኢትዮጵያን ታርክ የኛ ታሪክ አይደለም ብለው እስከማመን እያደረሳቸው ነው። በዚህ የተነሳ የኛ ታሪክ ወድቋል፣ ጠፍቷል፣ ተሰርዟል፣ ተረግጧል…… ሌላም ሌላም እየተባለ ስለሆነ እውነተኛ ታሪክን እያፋለሱ ያሉትን ሰዎች ወደ ሚዲያው በማውጣት ከታሪክ ሙሁራኑ ጋር ፊት ለፊት በማገናኘትና በማነጋገር ኢትዮጵያን የማዳኑን ስራ ትሰሩ ዘንድ ጋዜጠኞች ትልቅ ድርሻም አደራም አለባችሁ።
ሴም ወይንም ሴሜቲክ ማን ነው? ኩሽ ወይንም ኩሸቲክ ማን ነው? ሐበሻ የሚባሉትስ እነማን ናቸው? የሚለውን እንመልከት
ኖህ፡- ሴም፣ ካም፣ እና ያፌትን ወለደ ዘፍጥረት ፲+ ፩-፴፪ (10+1-32)
ሴም፡- ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሎድ፣ አራም፣ ቃይናን ወለደ።
ካም፡- ኩሽ፣ ምስራይም፣ ፍጥ፣ ከነዓን ወለደ።
ያፌት፡- ጋሜል፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያህያን፣ ያልሳ፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስን ወለደ።
ከላይ የዘረዝርኳቸው የኖህ ልጆች እና የኖህ የልጅ ልጆች የሆኑ ናቸው።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በሆነ የዘር መጠላለፍ የሚታየው ይሄንን እውነት ካለመረዳት ነው። ሴም በሉት ሴመቲክ ኩሽ በሉት ኩሸቲክ ለሴም አባቱ ለኩሽ አያቱ የሆነው ኖህ ነው። ታዲያ የአንድ ዘር ግንድ የሆንን ወንድማማቾች ይሄንን ያህል መጠላላት እና መለያየት ለምን አስፈለገ? ዛሬ ሴሜቲክ ነን እያልን የምንፎክር ዛሬ ኩሸቲክ ነን ብለን የምንፎክር አባታችን አንድ እንደሆነ ሲነገረን መደምደሚያችን ኖህ እንደሆነ ስናውቅ ምን ይሆን መልሳችን። ከየት ተነስተን ወደ የት ነው የምንሄደው? ወዴየትስ ነው መሄድ የምንፈልገው? ከማንስ ተፈጥረን ነው የሌላ ነን የምንለው ዛሬ እኛ ሴም ነን እኛ ኩሽ ነን ብለን የምንናገረው የተፈጥሮ ዑደታችን እውነቱ ይሄ ነው። ለዚህ ነው ብንጣላ የማንኮራረፈው ብንሰዳደብ የማንራራቀው የአንድ ቤተሰብ ልጆች ስለሆንን ነው። ነገሮችን ጠለቅ ብለን ስናውቅ ማንነታችንን እናውቀዋለን ማንነታችንን ስናውቅ ታሪካችንን እንወዳለን ታሪካችንን ስንወድ አገራችንን እንገነባለን አገራችንን ስንገነባ ለአለም ሁሉ የፍቅር፣ የሰላም የአንድነት የስልጣኔ መሰረት ሆነን እንታያለን።
ሌላው ሐበሻ ሴሜቲክ ናቸው እንጂ ኩሸቲክ አይደሉም ይሉናል። ከመነሻው እንዳየነው ሴም ለኩሽ አጎቱ ነው የኩሽ አባት እና ሴም ወንድማማቾች ናቸው ማለት ነው። በቃ የኛ አመጣጥ እዚህ ጋር በአራት ነጥብ ተዘግቷል። ኩሸቲክ እና ሴመቲክ የአንድ ዘር ልጆች ነን። ታዲያ ሐበሻ የሚለው ቃል የመጣው ከየት ነው? ከተባለ መልሱ ከአረቦች ነው።
ነብዩ መሃመድ ከቆሬሾች ጋር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በነበረበት ወቅት በጃፋር መሪነት የነብዩ የቅርብ ሰዎች የነበሩትን ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ የተናገሩትን ቃል እጠቅሳለው ቃሉ ቃል በቃል ከቁርአን ነው የተወሰደው << ሐበሻ (ኢትዮጵያ) የእውነት አገር ናት በውስጧም ሰውን የማይበድል እርሱም ዘንድ አንድም የማይበደል ንጉስ አለና ወደዚያ ብትሄዱ መልካም ነው>> ይላል። ነብዩ መሃመድ በእስልምና እምነት አማኞች ዘንድ ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰው ናቸው። ሐበሻ የሚለውን ስም እስካሁንም ድረስ አረቦች ይጠቀሙበታል። ታዲያ በነብዩ መሃመድ እንዲህ የተገለጹት ደግ በደልን የማያደርጉ ህዝብን የማይበድሉ መሪ ኢትዮጵያ ነበራት። እኚህ መሪ የሴምም የኩሽም ልጅ የሴምና የኩሽ ሃረግ የነበራቸው መሪ ናቸው እንጂ ዛሬ ዛሬ እንደሚነገረው የወያኔ ፖለቲካ እና የወያኔ አካሄድ የሚከተሉ እንደሚሉት ሐበሻ ስለተባሉ የሴም ወገን ናቸው ተብሎ መነገሩ የራስን ታሪክ ጠንቅቆ ካለመረዳት እና የፖለቲካን ትርፍ ለማግኘት ተብሎ ታሪክን በገዛ ፍቃድ እንደመጣል ይቆጠራል። ለኢትዮጵያ የሚሰጥ የታሪክ፣ የጀግንነት፣ የስልጣኔ፣ የሃይማኖት፣ የስነ ፈጠራ፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ ድርሻ የሴምም የኩሽም እኩል ታሪክ ነው። ማንም ከማንም የተነጠለ ታሪክ የለንም። ማንም ከማንም የሚለያይ ስራም የለንም። ወያኔ ለአገዛዙ ማቆያ ለስልጣኑም ማራዘሚያ በማሰብ መጀመሪያ እና መሃል የሌለው ጫፍ ብቻ ያለው ታሪክ ይነግረናል። ጫፉ ላይ ወጥተን ከማንነታችን ውጪ ግዜአዊ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ ማንነታችንን እና አገራችንን አደጋ ላይ መጣል ተገቢ አይደለም ነገም ታሪክ ይጠይቀናል ማንም ከተጠያቂነት አያመልጥም። ስለዚህ ወደ እውነተኛው ማንነታችን መመለስ ያስፈልገናል።
እንደ ማሳሰቢያ መናገር የምፈልገው አንድ ሰው የተለየ ሃሳብ ለምን አመጣ ተብሎ አይከለከልም ማንም የፈለገውን ሃሳብ ማምጣት ይችላል ያንን ሃሳብ ግን በማስረጃ ሊያቀርብ ያስፈልጋል። በነጻ ሚዲያ ዘርፍ የተሰማራችሁ ጋዜጠኞች በታሪክ ዙሪያ የተለየ ሃሳብ ያለው ሰው ካለ ወደሚዲያው በመጋበዝ ከታሪክ ሙሁራኑ ጋር ግልጽ ትንታኔ ከሁለቱም ወገን እንዲሰጡበት በማድረግ እና ጥያቄአቸውን በማስረጃ እንዲመልሱ በማድረግ እውነታውን ህዝቡ እንዲያውቀው የማድረጉን ስራ ቢሰራ በህዝቡ ዘንድ የሚኖሩትን ብዥታዎች ያጠራዋል። ህዝብን በመከፋፈል ዙሪያ ወያኔ የሚጠቀምበትን መንገድ አንድ አንዶችም በመከተል ላይ ስለሆኑ የፈረሰውን በመገንባት የሃሰት ታሪካዊ ወሬዎችን እውነተኛ በሆነው ታሪክ በማነጽ ያስፈልጋል። ጥያቄ አንሺውን እና ሙሁራኑን በማገናኘት በየግዜው ትንታኔ እንዲሰጥበት በማድረግ በጋዜጠኝነት ሙያውስጥ ያላችሁ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለአገራችሁ ታሪክ ስሩ። ኢትዮጵያን ወደ ሰላሟ እና ወደ እረፍቷ የሚያመጣት መልካም መንገድ ነውና።
ከተማ ዋቅጅራ
በኢትዮጵያ ህዝቡ የመንቀሳቀስ ነፃነቱ ጠብመንጃ በታጠቁ የአገዛዙ ቡድኖች መገፈፉ ታወቀ፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ደግሞ በሰሜኑ ክፍል እንደልብ ከቦታ ቦታ መዘዋወር እጅግ በጣም ከባድ እየሆነ እንደመጣና ህዝቡ የመንቀሳቀስ ነፃነቱ ጠብመንጃ በታጠቁ የአገዛዙ ቡድኖች መገፈፉ ታወቀ፡፡
በእጅጉ እየተፋፋመ ከሚገኘው ባንዳነትን በአርበኝነት ከማስወገድ የመሳሪያ ትግል ጋር በተያያዘ ህወሓት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ባሰማራቸው ክፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሰራዊት ጦር እንዲሁም ደህንነቶቹ በየጥቂት ኪሎ ሜትሮች የርቀት ልዩነት ቁጥር ስፍር የሌላቸው የፍተሻ ኬላዎችን በማቋቋም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ሰላማዊ ዜጎችን በብርበራ ስም ክፉኛ እያዋከበ፣ እያሸማቀቀና እያሸበረ ይገኛል፡፡
...

ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደርና ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ በሚወስዱ ጎዳናዎች ላይ የፍተሻ ኬላዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክረው የመንገደኞችን ሰብዓዊ መብት በረገጠ መልኩ ብርበራ፣ ማዋከብና ማሸብር እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ ደሴ በተዘረጋው መስመር በቅርቡ በተጀመረው ከዚህቀደም ታይቶ የማያውቅና ያልተለመደ ጥብቅ ጥበቃ፣ ቁጥጥር፣ ብርበራና በጦር መሳሪያ ማስፈራራት ጋር በተያያዘ ህዝቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በአካባቢው ገብተዋል በሚል ግምት የትግል መንፈሱ እንደተነሳሳ እና የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ውስጥ ለውስጥ እየገለፀ እንደሆነ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
በተለይም ደግሞ ከጎንደር ሁመራና ከጎንደር መተማ በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ገደብ የሌለው ቁጥጥር ስለሚደረግ ህዝቡ በተለይም ደግሞ ወጣቶች ፈፅሞ በነፃነት መንቀሳቀስ ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ከጎንደር ወደ አርማጭሆ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴና መተማ ለስራ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች አርበኞች ግንቦት 7ን ለመቀላቀል እየተጓዛችሁ ነው በሚል በየቀኑ በገፍ እየታፈኑ ወደ ወህኒ በመጋዝ ላይ ናቸው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የህወሓት አገዛዝ የተለያዩ ወንጀሎችን ራሱ በማቀነባበር ደጋፊዎቹ ያልሆኑ መንገደኞችንና አሽከርካሪዎችን ወንጀል ሲሰሩ እጅ ከፍንጅ እንደያዛቸው በማስመሰል በቁጥጥር ስር አውሎ በሃሰት እያሰራቸው ነው፡፡ የህወሓት ደህንነቶች ከጭልጋ ወደ ጯሂትና ደልጊ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚመላለሱ የህዝብ መጓጓዣ ሚኒባሶች ላይ የጦር መሳሪያዎችን በስውር እየጫኑ ማጥቃት የሚፈልጉትን ግለሰብ ጠብቀው አሳበው በቁጥጥር ስር እያዋሉ እንደሆነ በተደጋጋሚ ከቦታው እየደረሱን የሚገኙት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከሰሞኑ የህወሓት ደህንነቶች የሰሌዳ ቁጥር 11243 የሆነች ሚኒባስ ላይ ወደ አስር የሚጠጉ ክላሽን ኮቮችን በድብቅ በማስጫን ሚኒባሷን ከጭልጋ ደልጊና ጯሂት በሚወስደው መስመር ከምትገኘው ብሆና ላይ ጠብቀው በቁጥጥር ስር በማዋል ከተሳፋሪዎቹ መካከል ሊበቀሉት በሚፈልጉት ሰው ላይ እርምጃ ወስደዋል፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)