Friday, 27 November 2015

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ደግሶችን እናምክን!!!

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ደግሶችን እናምክን!!!
==============================
Nov 27, 2015 Editorial
የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ የተዋቀረችው በህዝብ ታሪካዊ አብሮነትና ተዛምዶ ላይ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብ ልዩነቶችን በማጥበቅና ልዩነትንም የርስበርስ ጥርጣሬና ግጭት ምንጭ እንዲሆን በማለም ነው። ልዩነት የግጭትና የጠብ ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተዋቀረውና ብፖለቲካ ደረጃ የተገፋው። አንዱ ብሔረሰብ ሌላው ብሔረሰብ ክልል ውስጥ ሲሆን ባዕድነት እንዲሰማውና እንዲሰጋ አንዱ አንዱን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ተደርጎ ነው ሀያ አራት አመት ሙሉ የተገፋውና እየተገፋ ያለው።
ይህም ሆኖ በዘመነ ወያኔ በየቦታው የተከሰቱ የብሔር ሌብሔርሰብ ግጭቶች በሙሉ የተቀሰቀሱት በራሱ በመንግስት ባለስልጣኖች እንጂ መቼም ህዝብ ለሕዝብ ሆኖ አያውቅም። በተለያዩ የደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች አማሮችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ለማባረር የተወሰዱት ርምጃዎች ራሳቸው ሰለባዎቹ እንደሚናገሩት ለስቃይ የዳረጋቸው ነዋሪው ሕዝብ ሳይሆን ባለስልጣናቱ መሆናቸውን በግልጽ ሲናገሩ ሰምተናል።
በቤኒሻጉልና ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሰሞኑን ይፋ መሆኑ የተነገረው በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተቀብረው የተገኙ አማሮች አስከሬን መገኘቱ ታውቋል። ይህም ወያኔ ባስለጠናቸውና ባዘዛቸው ካድሬዎችና ባለስልጣኖች የተከወነ እንጂ በሕዝብ ተነሳሽነት የተፈጸመ አለመሆኑ የታወቀ ነው። ቀደም ሲል በመንግስት ደረጃ የተቀነባበረ አማሮችን የማፈናቀል ዘመቻ ተከታይ ስራ መሆኑን ለማወቅ ብዙ አዳጋች አይደለም። በወገኖቻችን ላይ በሚዘገንን መንገድ የተፈጸመው ግፍ ዘልቆ ይሰማናል:: ሊሰማንም የገባል። ቁጭታችንና ሀዘናችን ግን ወያኔ ወደሚፈልገው የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ምክንያት እንዳይሆን ከፍተኛ ትዕግስትና ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
ሰሞኑን በታሪክ ሊዘገብ ከሚችል ልዩነት ውጭ ባኗኗር በባህልና ቋንቋ የማይለያዩትን የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች ቅማንትና አማራ በሚል ለማጋጨት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ሰይጣናዊ አካሔድ በወያኔ የፖለቲካ ተንኮል እየተመራ እንዳለ የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች አሉ። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉም ካላንዳች መድሎና ልዩነት ሀገሪቱ ላይ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ሁሉም በየበኩላቸው የሚያደርጉትን ጥረትና ትግል እንደግፋለን። በህዝባችን መካከል ያሉት ግንኙነቶች ሊሆን የሚችለው እንዱ አንዱን የማገዝ እንጂ ርስበርስ የመጋጨትም ሆነ የመናቆር አይደለም።
ኢትዮጵያውያን ብሄርና ዘር ሳንለይ ይህንን የወያኔ ተንኮል ችግሩ ወደባሰ ደረጃ ሳይሄድ መቋቋምና ማክሸፍ ይጠበቅብናል። ይህ ታሪክነታችንና ታላቅ ሕዝብነታችንን የማይመጥን አሳፋሪ የወያኔ ፖለቲካ እንደሀገር እንዳያጠፋን ሁላችንም በንቃትና በቁርጠኝነት መቋቋም ይኖርብናል።
አርበኞች ግንቦት ፯ ልዩነት ጌጥ እንጂ የጠብና የግጭት ምክንያት የማይሆንባት ሀገር ፥ የየብሔረሰቡ መብት ሁሉ የይስሙላ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠባት ሀገር ፥ ከነልዩነታችን በጋራ ራዕይ የምንተሳሰርባትና የምንገነባት ሀገር እንድትኖረን የሚያደርገውን ትግል ይቀጥላል። የቻልክ በአካል ተቀላቀለን። ያልቻልክ በያለህበት የወያኔ ዘራፊዎች ያሰቡትን የተንኮል ጉንጉን በመበጣጠስ ተሳተፍ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

Wednesday, 25 November 2015

ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው የድንበር ሊካለል ነው ተባለ

ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው የድንበር ሊካለል ነው ተባለ።
በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ የድንበር ማካለሉ ስራ ሙሉ በሙሉ እንደሚከናወን ባለፈው አመት መጨረሻ አለያም በዚህ አመት መጀመሪያ አካባቢ ተካሂዶ በነበረው የአልበሽር በአለ ሲመት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለሱዳን ባለስልጣናት ማረጋገጫ ሰጥተው እንደተመለሱ በጊዜው በደረሰን መረጃ መሠረት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ አሳውቀን ነበር ። አሁን ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ የድንበር ማካለሉ ስራ በሚቀጥለው ወር ውስጥ እንደሚከናወን ገልፆ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የሱዳኑ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ መግባታቸውን ገልጿል። ከኤርትራ እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ድረስ 1600 ኪሎ ሜት ርዝመት ባለውና ወደ ኢትዮጵያ ከ40 ኪሎ ሜትር በላይ ዘልቆ ወደ ውስጥ የሚገባው የሱዳን የድንበር ይገባኛል ጥያቄ አብዛኛውን የሀገሪቱን ለም መሬት በስፋት ለሱዳን የሚሰጠውና ከዚህ ወር መጠናቀቅ በሗላ የሚተገበረው ስምምነት ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅናና ይሁንታ ውጪ በህውሃት/ኢሕአዴግ ጁንታ ባለስልጠናት ውሳኔ የሚተገበር ነው። ይህ የድንበር ማካለል በትግበራ ላይ ከዋለ በህውሃት የአገዛዝ ዘመን ከተፈፀሙና ታሪክ ከማይዘነጋቸው በርካታ ስህተቶች መካከል አሰብ ለኤርትራ ከተሰጠበት መራር እውነት ቀጥሎ በጥቁር ቀለም የቀለመ ሁለተኛው ግዙፍ ስህተት ሆኖ ይመዘገባል፡፡

ሕወሓት መራር የሽንፈት ፅዋን ዳግም ተጎነጨ!!


ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋንና ድርጅታቸው አርበኞች ግንቦት 7 ‘’በአሸባሪነት’’ እንዲፈረጅላቸው ሌት ተቀን የአውሮጳ ህብረትን ሲማፀኑ የነበሩት ሕወሓቶች ዳግም የሽንፈት ፅዋን ተጎነጩ። የአውሮጳ ህብረት አርበኛው ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን በመጭው ማክሰኞ (Dec 1) በአውሮጳ መዲና በብራስልስ ''ድርቅና ረሀብ በኢትዮጵያ'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ህዝባዊ ውይይት ንግግር እንዲያደርጉ በክብር በመጋበዝ ህብረቱ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ያለውን ድጋፍና አጋርነት ከማሳየቱም ባሻገር በኢትዮጵያ አሸባሪው ማን እንደሆነ ጠቁሞ አልፏል።
እንግዲህ በሕወሓት ካምፕ እንቅል የሚባል ነገር አይታሰብም!! አሸባሪው ማን እንደሆነ በአውሮጳ ህብረት ዘንድ በግልጽ ተለይቷልና!!
ለማነኛውም እንዳያመልጣችሁ!!!
ከአርበኛው ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ቆራጥ አመራር ጋር ወደፊት!!!

Wednesday, 18 November 2015

“15 ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል” (በውቀቱ ስዩም)


ባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ ስለዚህ ጌቶች ያስንቀናል ብለው የሚያስቡትን ነገር በሙሉ ጠምድው ይይዙታል፡፡ ይዋጉታል፡፡ ኢትዮጵያ- ጌቶች ለኩራታቸው፤ ዜጎች ለራታቸው የሚታገሉባት መድረክ ናት፡፡
Ethiopian author and poet, Bewketu Seyoumብዙ ጊዜ ረሀብ ሲከሰት ጌቶች ራብተኛውን ሁሉ ሰብስበው ጎተራ ውስጥ ሊደብቁት ይቃጣቸዋል፡፡ የድሆች የተራቆተ ሰውነት የገጠጠ ኣጥንት፤ የጌቶችን የመከበር ፍላጎት ያከሽፈዋል፡፡ ባንድ ወቅት በቦሌ መዳኒያለም ዳርቻ ስራመድ ኣካባቢው ኣለወትሮው በለማኞች ኣለመሞላቱን ታዝቤ ተገረምሁ፡፡ያዲሳባ ኣስተዳደር ፤ ለማኞችን“ በጥቃቅንና ኣነስተኛ ” ኣደራጅቶ ያሳለፈላቸው መስሎኝ ነበር፡፡ እንደተሳሳትሁ ለመረዳት ጥቂት ደቂቃ በቦታው መቆም ነበረብኝ፡፡ ኣንዲት ተመጽዋች ሴት ልጇን ይዛ ከቅጽሩ ስር ለመቀመጥ ስታነጥፍ ፖሊስ በቆረጣ ገብቶ “ዞር በይ ነግሬሻለሁ” እያለ ሲያዋክባት ተመለከትሁ ፡፡ የደነገጠ ልጇን እየጎተተች ተወገደች፡፡ ከዚያ ወዲያ ከኣቡነ ጳውሎስ ሃውልት በቀር ባካባቢው ደፍሮ የቆመ ኣልነበረም፡ ፡ ወደ ቤቴ ከመሄዴ በፊት ያቡኑን ወፍራም ሀውልት ዞር ብየ ሾፍኩት፡፡ እጁን እንደ ራሱ ሀይሉ ሙርጥ ገትሮ ከፊትለፊት ያለውን “ሬድዋን ህንጻ” ሲባርክ ነበር፡፡
“ገጽታ ግንባታ?”
በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የፍርድ ምኒስተር የነበሩት ኣፈንጉስ ነሲቡ የሌባ ብዛት ቢያስቸግራቸው ኣንድ መላ መቱ፡፡ ሲሰርቅ የተገኘ ወሮበላ ግንባሩ ላይ በጋለ ስለት ምልክት እንዲደረግበት ደነገጉ፡፡ ታድያ ሌቦች የዋዛ ስላልነበሩ ሻሽ በመጠምጠም የግንባራቸውን ጠባሳ ሊሰውሩት ሞክረዋል፡፡ በጊዜው ደግሞ ሻሽ መጠምጠም ካክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የወረደ የነገስታቱና የመሳፍንቱ ወግ ነበር፡፡ ጮሌ ሌቦች ውርደታቸውን ከመሸፈን ኣልፈው የንጉስ ገጽታ ተላብሰው ብቅ ኣሉ፡፡
በዘመናችን የተራቡ ዜጎችን መደበቅ እንደ ገጽታ ግንባታ የሚቆጥሩ ሰዎችን ከባለሻሽ ሌቦች ለይቼ ኣላያቸውም፡፡
በነገራችን ላይ፤ ብርቱካን ኣሊ ግለሂስ ያደረገችበትን ዘገባ ካየሁ በኋላ ለጊዜው ለመናደድ እንኳ ቸግሮኝ ነበር፡፡ ዘገባውን የሠራው ጋዜጠኛ እንዲህ ኣይነቱን ካንድ ድንጋይ የተጠረበ ደደብነት ተሸክሞ የመኖር ችሎታው በጣም ኣስደነቀኝ፡፡ በዚህ በሰላቢው ቀን ይቅርና፤ በደህናው ቀን እንኳ የባላገሩን ራብና መከራ ከጉያው የበቀልን ልጆቹ እናውቀዋለን ፡፡ ኣስራ ኣምስት ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል፡፡ መመፍትሄው በተቸገሩ ሰዎች ጫማ ቆሞ ነገሮችን መመልከት ነው፡፡ ለነገሩ ችግርን ያልቀመሰ ሰው ለችግረኛ መራራት እንዴት ይቻለዋል?
ኣብን ተውትና ፤ንገሩት ለወልድ
ተገርፏል ተሰቅሏል ፤ እሱ ያውቃል ፍርድ
እንዲል ባላገር፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር መገደዱን ገለፀ

ሰማያዊ ፓርቲ ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር መገደዱን ገለፀ
• ‹‹ከደህንነትና ፖሊሶች ጋር ካልተነጋገርኩ አልፈቅድም›› አስተዳደሩ
• ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እነሱን መለማመጥ አያስፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ለመነጋገር ህዳር 18/2008 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አቅዶ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ አስተዳደር በፈጠረበት መሰናክል ምክንያት ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር መገደዱን ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ባስገባው የእውቅና ደብዳቤ ላይ ‹‹ህዳር 18 አልፏል፡፡ ይቀመጥ!›› ብሎ መርቶበት የነበረው አስተዳደሩ ፓርቲው ‹‹ህዳር 18 አላለፈም›› ባለው መሰረት ‹‹በስህተት ነው፡፡ ሰኞ ኑ!›...› ብሎ ሰኞ ህዳር 6/2008 ዓ.ም ተቀጥረው እንደነበር እና ወደ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል መመራቱን ተገልጾላቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ሰኞ ሲሄዱ ‹‹ዛሬ አይመችም፣ ነገ ኑ›› ተብሎ ለረቡዕ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ዛሬ ህዳር 8/2008 ዓ.ም በቀጠሯቸው መሰረት ከህዳር 6 ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ፤ እውቅናውን ከጠየቀ በኋላ በአጠቃላይ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ሲሄዱ የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ‹‹ከደህነትና ፖሊስ ጋር እየተማከርኩ ነው፡፡ ከእነሱ ጋር ሳልማከር አልፈቅድም›› ብሎ እንደመለሳቸው ገልጸዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ለአስተዳደሩ ደብዳቤ መፃፍ ከጀመረ 15 ቀናት ያለፉት ሲሆን ለ6ኛ ጊዜ ደብዳቤውን ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ አስተዳደሩ የሰላማዊ ሰልፍ ወይም የስብሰባ እውቅናን መከልከል እንደማይችል፣ ነገር ግን የደህንነት አሊያም የቦታ ችግር ካለ ቦታ ወይንም ጊዜ ሊቀይር ብቻ እንደሚችል የገለፁት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በተደጋጋሚ ለአስተዳደሩ ደብዳቤ ለማስገባት የተገደዱት የአዳራሽ ኪራይ ለመክፈል አስደዳደሩ እውቅና ስለሚያስፈልግ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ይሁንና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለአስተዳደሩ አሳውቆ በ48 ሰዓት ውስጥ መልስ ካልሰጠ እውቅና እንደሰጠ ስለሚቆጠርና የአስተዳደሩን መሰናክልም ስለሚቀንሰው ስብሰባውን ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር እየተገደዱ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ‹‹መስተዳደሩ እንዲህ የሚጠመው የስብሰባ አዳራሽ እንዳናገኝ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ከሆነ ግን እነሱን ይህን ያህል መለማመጥ አያስፈልግም፡፡ በመሆኑም እንደተለመደው የወሰዱትን እርምጃ ቢወስዱም ስብሰባውን ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀየር እየተገደድን ነው›› ብለዋል፡፡

እነ ማቲያስ መኩሪያ ጥፋተኛ ተባሉ

እነ ማቲያስ መኩሪያ ጥፋተኛ ተባሉ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
አይ ኤስ በኢትዮጵውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ድርጊት ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ እና መሳይ ደጉሰው ዛሬ ህዳር 8/2008 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ችሎቱ በቢሮ ከመታየቱም ባሻገር ችሎት አስከባሪው ‹‹መግባት አይቻልም፡፡ ተከልክሏል፡፡ የከለከልኩት ግን እኔ አይደለሁም፡፡›› በማለቱ ማንም እንዳይገባ ተከልክሎ በዝግ ታይቷል፡፡ ፖሊስ ተከሳሾቹ ላይ የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ በማለቱ ተከሳሾቹም ‹‹የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም በመከላከያ ማስረጃነት ስለሚያገለግለን ይቅረብልን›› ባሉት መሰረት ቪዲዮውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለወራት ሲቀጠርባቸው ቆይቷል፡፡
ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት ተከሳሾች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ተከሳሾቹ ከታሰሩ ከ6 ወር በላይ የሆናቸው ሲሆን በፍርድ ሂደቱ ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ እነ ማቲያስን ጥፋተኛ ያለው ፍርድ ቤቱ ለህዳር 22/2008 ዓ.ም ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የወልቃይት ህዝብ ለነፃነቱ ሊታገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በአንድነት መነሳቱ ታወቀ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የወልቃይት ህዝብ ለነፃነቱ ሊታገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በአንድነት መነሳቱ ታወቀ፡፡
====================================================
የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡
ህወሓት የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የጀመረውን የነፃነት ትግል እንቅስቃሴ ጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ለመደፍጠጥ ወደ አካባቢው ያለማቋረጥ ሰራዊት እያዘመተ አሰቃቂ የህዝብ ጭፍጨፋ በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡...
ሆኖም ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ በጥይት በመግደል ዝም ማሰኘት ሳይችል ቀርቶ ዛሬ የበለጠ ተደራጅቶበት ጠብመንጃውን ወልውሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡ ወደ በረሃ እየወረደ አርቨኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን አርበኝነት የሚቀላቀለውም ከዕለት ዕለት ቁጥሩ በእጅጉ አይሏል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የወልቃይት ሰው ማር ዘነብ ልዩ ቦታው ቴፍ ላይ በመሰባሰብ ስለነፃነቱ መክሯል፤ የትግል መሪዎቹንም መርጧል፡፡ በጉባኤው ላይ የአርማጭሆ ህዝብም ተገኝቶ በጋራ ጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያሳርፉ ቃል ተገባብተዋል፡፡