Thursday, 9 October 2014

የVOA ጋዜጠኞች ቅሌት ዛሬም ቀጥሏል
VOA ማክሰኞ በቦታው ተገኘሁ ብሎ የሰልፈኞቹን ብዛት በተዛባ ሁነታና በቅጥፈት 15ና 20 ናቸው ብሎ ተናግሮ ሲያበቃ፤ ዛሬም ወያኔን ለመጥቀም መረጃ ማዛባቱን ቀጥሎበት ለአድማጭ ያልተረጋገጠ፣ ለማያውቁ የዋሆች ክርክር ውስጥ የሚያስገባና፣ የበረራ ቲኬት ተገዝቶላቸው በመከራ ከየ እስቴቱ መጥተው በመዋጮ የተሰባሰቡትን ሆዳሞች ተጨምረውበት እንኳን እጅግ አናሳ የነበሩትን የወያኔ ደጋፊዎችን በማምታታት አብዝቶ ለማሳየት፤ ከጋዜጠኛ የማይጠበቅ እጅግ የወረደ ዘገባ አቅርቧል።
እንደው እስኪ ፍረዱ ሰልፉ ከተጠናቀቀ ከ24 ሰአታት በላይ ካለፉ በሗላ ጠይቆ የተሰላፊዎቹን ተወካዮች ለአድማጭ አሃዞችን እንደ እውነት ማቅረብ ምን ይባላል!? ወያኔ ተዋሸለትም፣ ተደበቀለትም፤ ከህዝብ ትከሻ ላይ አሽቀንጥረን የምንጥልበት ጊዜው በጣም ቀርቧል። ለነገሩ ለተከፈለው ገንዘብ ብሎ የተጠራቀመ፤ የገዛ ባንዲራውን እንኳን የማይለይ ሆዳም ቢሰባሰብ ምን ይፈይዳል!? “ሺሺሺ… አንድ ጎማ አይነፋም” ይሉ የለ… !

Wednesday, 8 October 2014

በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተኩስ የከፈቱት ዲፕሎማት ላይ የእስር ማዘዣ ወጣ
ባለፈው ሰኞለት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለተቃውሞና ለአቤቱታ የተሰባሰቡ ሰዎች ላይ ሽጉጥ በመምዘዝ የተኮሰው የኢምባሲ የጥበቃና ደህንነት ክፍል ሰራተኛ፤ የዩናይትድ ስቴይትስ አቃቢ ህግ ቢሮ እስከ 30 ዓመት በሚያስቀጣ ወንጀል ክስ ከፍርድ ቤት እስር ማዘዥ እንደተሰጠው አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥበቃና ደህንነት አታሼ የ46 ዓመቱ አቶ ሶሎሞን ታደሰ ገ/ስላሴ የተከሰሱበትና የእስር ማዘዣ የወጡበት ህግ “ለመግደል በማሰብ ጥቃት ማድረስ” የሚል ነው። የወንጀል ደረጃውም እስከ 30ዓመት የሚደርስ ከፍተኛ ቅጣት የሚጣልበት እንደሆነ በዩናይትድ ስቴይትስ አቃቢ ህግ ቢሮ የዋሽንግተን ዲሲ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ዊሊያም ሚለር ለቪኦኤ በጽሁፍ ገልጸዋል። ሰኞ መስከረም 19 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለተቃውሞ ሰልፍና ለአቤቱታ የወጡ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ኢምባሲው ቅጥር ግቢ ከገቡ በኋላ በተፈጠረ ሁኔታ አቶ ሰሎሞን ተኩስ ከፍቷል። በዚህ የወንጀል ምርመራ፤ የዝግጅት ክፍላችን ከዚህ ቀደም ለፍትህ ምንስቴርና ለውጭ ጉዳይ ምንስቴር ባቀረበው ጥያቄ፤ የምርመራው አትኩሮት በተኳሹ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው? ለሚለው ጥያቄ የዲሲ አቃቢ ህግ ቢሮ ሲመልስ ዝርዝሩ የሲክሬት ሰርቪስ ቢሆንም “በዚህ ክስተት ላይ ሌላ ክስ የቀረበበት ሰው የለም” ብለዋል።
http://amharic.voanews.com/

Monday, 6 October 2014

የአዜብ ዱላ
አርአያ ተስፋማሪያም
Oct 5,2014
ጋዜጠኛ ሰሎሞን አስመላሽ ለብዙዎች እንግዳ አይደለም። የ120 መዝናኛ አዘጋጅ ነበር። ከኢቲቪ ከወጣ በኋላ ሜጋ አመራ። (በ1989ዓ.ም ከሳምሶን ማሞ ጋር በታዋቂ አትሌት ላይ የሞከሩት የፔፕሲ ማስታወቂያ ማጭበርበር ድርጊት ነበር፤ ጉዳዩን ለጊዜው እንለፈው) የሜጋ ሃላፊዎች እግር ስር ወድቀው ከወጡ በኋላ ሰሎሞን አስመላሽ የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት ከፍቶ መስራት ቀጠለ። በአደባባይ የገዢው ፓርቲ ደጋፊና አቀንቃኝ መሆኑን የሚናገረው ጋዜጠኛ ሰሎሞን ከአራት አመት በፊት በምሽት መዝናኛ ውስጥ መጠጥ እየተጐነጨ ነበር። በድንገት መብራት ድርግም ይላል። ሰሎሞን ጮክ ብሎ « አዜብ መስፍን ያስገባቸው ጄኔሬተር ተቸበቸበ! ሆን ተብሎ ነው መብራት የሚጠፋው..የአዜብን ጄኔረተር ለመሸጥ!» እያለ ተናገረ። በሚገርም ፍጥ...ነት ይህቺ ቃል አዜብ መስፍን ጆሮ ደርሳለች። አዜብ ወዲያው በቀጭን ትእዛዝ ወደ መዝናኛው ደህንነቶች አዘመቱ። በዛው ሰሞን ሰሎሞን በውድ ዋጋ እጅግ ዘመናዊ አውቶሞቢል ሸምቶ ነበር። በስፍራው የደረሱት ደህንነቶች የመኪናዋን መስተዋት በመሰባበርና ጐማዎቿን በማስተንፈስ ተልእኳቸውን ጀመሩ። ሰሎሞን አስመላሽ ከመዝናኛው ሲወጣ አንድም የሰውነት አካሉ ሳይቀር በዱላ ቀጥቅጠው መንገድ ዳር ዘርረውት ሄዱ። አዜብ « እንዳትገድሉት ግን ሰባብራችሁ ጣሉት» በማለት አዘው ስለነበረ ያንን ደህንነቶቹ እንደፈፀሙ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋልጦዋል።…በነገራችን ላይ መስከረም 1 ቀን 1995ዓ.ም ፒያሳ ትግራይ ሆቴል በገዢዎቹ ተቀነባብሮ የተፈፀመው የፈንጂ ጥቃት በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱት 60 ንፁህ ሰዎች አንዱ የሰሎሞን አስመላሽ ታናሽ ወንድም ይገኝበታል። ይህ ዘግናኝ ድርጊት እንዴት እንደተፈፀመ ጋዜጠኛው ካወቀ በኋላ ሞቅ ሲለው ይናገር ነበር።..በ1990 ዓ.ም ሰሎሞን አስመላሽ እጅግ ውብ የሆነች ፍቅረኛውን ተነጥቋል። በአሜሪካ ትኖር የነበረችው ፍቅረኛውን አንድ ለባለሃብቱና ለገዢው ባለስልጣናት ቅርብ የሆነ ግልገል “ቱጃር” የግሉ አድርጓታል። .. ጋዜጠኛው አሁንም የገዢው ደጋፊ ነው።


Saturday, 4 October 2014

የጋምቤላው ግጭት ተፈናቃዮችና ታካሚዎች
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጋምቤላ መስተዳድር በጎደሬ ወረዳ ለረጅም ጊዜ በዚያ ሠፍረው ይኖሩ በነበሩ ና በአካባቢው መዠንገር ነባር ብሔረሰብ አባላት መካከል በተከሠተ ግጭት ብዙ ሰዎች መሞታቸው ተነግሮአል። ወደተለያዩ ቦታዎች የተሰደዱትም ጥቂቶች አይደሉም።
ቆስለው ለህክምና አዲስ አበባ በመግባት በ መ ኢ አ ድ ቅጥር ግቢ ከሠፈሩት መካከል 2 ሰዎች እንዲሁም የድርጅቱን ቃል አቀባይ አነጋግረናል።
ተክሌ የኋላ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

Thursday, 2 October 2014

የፓርቲዎቹ አባላት ጠበቃ ደረሰብኝ ባሉት ጫና ለጊዜው ሥራቸውን ማቆማቸውን አስታወቁ

Oktober 1,2014
በ  አሸናፊ ደምሴ
በሕገመንግስቱ መሠረት ለደንበኞቼ አገልግሎት መስጠት አልቻልኩም፤ ከፍርድ ቤትና ከፖሊስም ማስፈራሪያ ደርሶብኛል ያሉት የአንድነት፣ የሰማያዊና የዓረና ፓርቲ አባላት ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ። ደንበኞቼ የምርመራ ቃላቸውን ለፖሊስ ከመስጠታቸው በፊት ላገኛቸው ሲገባ ይህ አልተደረገም ያሉት ጠበቃው፤ የጊዜ ቀጠሮው ችሎት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለቀጣዩ አንድ ወር ደንበኞቻቸውን እንደማያገኙና ሕግን ባልጠበቀ መንገድ ለሚከናወን ተግባር የፕሮፓጋንዳ ሽፋን መሆን እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል።
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለአንድነት ፓርቲ አባላቱ ለሀብታሙ አያሌውና ለዳንኤል ሺበሺ፤ ለአረናው አብርሃ ደስታ እና ለሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ ጠበቃ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኙ የነበሩ ሲሆን፤ ደረሰብኝ ባሉት ጫና እና ኢ-ሕገመንግስታዊ አሰራር ምክንያት ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለጊዜውም ቢሆን ማቋረጣቸውን ለፓርቲዎቹ አመራሮች መግለፃቸውን አስረድተዋል። ይህም በመሆኑ ሦስቱ ፓርቲዎች (ማለትም አንድነት፣ ዓረና እና ሰማያዊ) በእስረኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት በተመለከተ ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም በአንድነት ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እንደማንኛውም ጠበቃ ደንበኞቼን ማግኘት ቢኖርብኝም፤ ላገኛቸው አልቻልኩም፤ በፍርድ ቤት የምናቀርባቸው አቤቱታዎች እና ስሞታዎች በሙሉ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ ይደረጉብናል፣ ይባስ ብሎም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር በመኖሩ ለስርዓቱ ሕጋዊ ከለላ መሆን አልፈልግም የሚሉት አቶ ተማም አባቡልጉ፤ በዚህም ምክንያት የታሰሩት የፖለቲከኛ እስረኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ ከለላ ማግኘት አልቻሉም ሲሉ ነገ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደሚያነሱ ምንጮች ጠቁመዋል።
በጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ በጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡት ያለጠበቃ ቢሆንም፤ ምናልባትም ከወር በኋላ ዐቃቤ ሕግ ክስ የሚመሰርት ከሆነ፤ በችሎት ተገኝቼ ደንበኞቼን አገለግላለሁ የሚሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ፤ ደንበኞቼ ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት እኔን ማግኘት ሲገባቸው ሳያገኙኝና ቃላቸውን ሰጥተው ከፈረሙ በኋላ ባገኛቸው ምን አደርግላቸዋለሁ? ሲሉ ጥያቄ አዘል ኀሳባቸውን ይሰነዝራሉ። ከዚህም ባሻገር ደንበኞቼ ከተጠረጠሩበት ጉዳይ ውጪ በሆነ መልኩ የሚደረግባቸው ምርመራ በፓርቲ ጉዳይ ላይ ሆኗል ሲሉ ቅሬታቸውን የሚያቀርቡት ጠበቃው፤ ለዚህም ጠንካራ አባል ማነው? የገንዘብ ምንጫችሁ ከየት ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው እንደነበር ደንበኞቼ ለፍርድ ቤት ቀርበውም አመልክተዋል ሲሉ ያስረዳሉ።
      ይህም በመሆኑ የተላላኪነት ስራ ከመስራት ውጪ የምፈይደው ነገር የለም በሚል ለጊዜው ከደንበኞቼ ጋር መገናኘቱን አቁሜያለሁ ያሉት ጠበቃ ተማም፤ በዚህ አጋጣሚ ደንበኞችዎ ምን ሊያጋጥማቸው ይችላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “የሚደርስባቸው ሁሉ ደርሶባቸዋል፤ እኔም ኖሬ ምንም አይነት የሕግ ከለላ አላገኙም” ሲሉ መልሰዋል።
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

Wednesday, 1 October 2014

US Department of State Spokesperson remarks on shooting incident at Ethi...

breaking news ዋሸግተን ዲሲ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተቀጣሪ በኢትዮዽያኑ ላይ የተኮሰው የኤንባሲ ሰራተኛ ሰለሞን ውይም ወዲ ወይኒ የተባለው ግለሰብ ዛሬ ከዋሽግተን ዲሲ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዲፖርት ተደረገ ሰለሞን ዎይም ወዲ ወይኒ ነገ ሃሙስ ኢትዮዽያ ይገባል ኢሳት ከቦታው ሆኑ ወዲ ዎይኒን ለማግኘት ያረገው ሙከራ አልተሳካም አሸባሪው ለብቻው በሌላ መንግድ እደገባ ኢሳት ገልፅዋል