Wednesday, 26 March 2014

የመልካም አስተዳደር እጦት በወሎ] የዘረፈ፣ እግር የቆረጠ፣ ሕዝብን በጥይት እየገደለ ያለ ስልጣን ላይ ሆኖ ይንደላቀቃል



(የሰሜን ወሎ ሕዝብ በገበያ ላይ – ፎቶ ፋይል)
ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አዘጋጆች ክቡር ሰላምታየ ይድረሳችሁ ከዚህ በመቀጠል የዘወትር የፕሮግራምችሁ ተከታታይ ስሆን ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር አየር ላይ እንድታውሉልኝ እየጠየኩ እን ሁልግዜው ለሁሉም የምታቀርቡትን አስተያየት ሙያችሁ በሚፈቅደው መሠረት እንደምታቀርቡልኝ ወይም አየር ላይ እንደምታውሉልኝ በመተማመን ነው፡፡ በሰሜን ወሎና ዞን በሀብሩ ወረዳና በመርሳ ከተማ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ አካባባቢ በየግዜው የሚስተዋሉት የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግሮች ነዋሪውን የከተማና የገጠር ህዝብ እግር ተወርች ሰቅለው ይዘውታል፡፡ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከመንግስት ደቀመዛሙርት መሰል ሚዲያዎች የምንተነፍስበት ወይም ሃሳባችንን የምንገልፅበት አማራጭ አለመኖሩ ነው፡፡ ይህም የናንተ የዘገባ አድማስ ሁሉንም አካባቢዎች የሚሸፍን አለመሆኑ ይመስለኛል ፡፡

 


ከዚህ በተረፈ ጉዳዩ አዲስና ልዩ ባይሆንም ድግግሞሽና አንደኛው ከሌለኛው ሲነፃፀር በጣም የከፋ እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አቤቱታው በምድር ላይ ያሉት ቱባ ባለስልጣኖች ጆሮ ነፊውን በየእምነቱ በፈጣሪው መፀለይ እና አቤት ለማለት ተገዷል እናም የናንተ የአቀራረብ ብስለት ታክሎበት መልዕክቱን ለአየር ታውሉልኛላችሁ ብዩ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ መቸም የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ሲነሳ ተነግሮ አያልቅም ነገር ግን ቀደም የተፈፀመው በደል ላያንሰው አዳዲስና ከፀሐይ ጋር አብረው ብቅ የሚሉት የትም የለሉ ቢሆንም የቅርቡን ለመግለፅ ያህል 1. በመርሣ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ 35 /ሰላሳ አምስት/ መንጃ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች በአማራ ክልል በቅርቡ እንዳያወጡ በመከልከላቸውና
ሙስና የበዛበት አሰራር ስላለ ወደ ተሻለውና አገሪቱን በበላይነት ወደ ሚመራው ክልል 1 ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በመሄድ መንጃ ፈቃድ አውጥተው አሁን በከተማው የትግራይ ክልል መንጃ ፈቃድ አማራ ክልል ላይ አይሰራም በማለት ታግደዋል ፡፡ ክልሉ በማንና በምን እንደሚመራ ካለመታወቁም በላይ የወያኔን መሪነት ብአዴን መካዱ ይሆን ወይስ በአንድ አገር ሁለት ዓይነት ህግ መኖሩ ነው መልስ ያጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡
2. በዚሁ በመርሣ ከተማ ዙሪያዋን በሚገኙ ወደ ከተማ የተከለሉ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ አራሽ ገበሬ ለፍቶና ጥሮ ለአመታት ጥሪቱን በሚያስጨርስ ሁኔታ የሰራውን ቤት ለምሳሌ አቧሬ አካባቢ የአቶ ሙመድ ሰይድ ቤት 8X9 የሆነ ቤት አገልግሎት በማይሰጥ መልኩ አፍርሰው ወደ ሌሎች መሰል ግለሰቦች ሲገቡ ነዋሪው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ባለስልጣኖቹን በመፈታተኑ እንዲባረሩ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በ25/6/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል / አካባቢ በዚሁ ከተማ ልዩ ቦታው መልካጨፌ ከተባለው አካባቢ የ8 /ስምንት/ ሰው አርሶ አደር ቤት አፍርሰው ወደቀጣዩ ሲሸጋገሩ ጉዳዩ ያበሳጨው ነዋሪ ህዝብ ከአንድ መቶ በላይ የሚቆጠር ፖሊስ ፣ሚሊሻ አመራር በመሆን ህዝቡ በአመፅ በመነሳት ከሃምሳ በላይ ጥይት ተተኩሶ ሁለት ግለሰብ አርሶ አደሮች የህዝብ ተወካይ ነን በሚሉ ታጣቂዎች ተመትተው ቆስለው ህክምና ላይ ሲገኙ የጣፋው ጠፍቶ ቀሪውን በትግል ማዳን ችሏል ይሁንና መብቱን መገፋቱ ሳያንሰው ብሎም በቤት ውስጥ የነበሩ መንታ የወለደች ሴት ሜዳላይ እንድትወድቅ ተደርጓል ድርጊቱን ለምን ተከላከላችሁ ተብለው ሁከት ፈጣሪ በመባል ማረሚያ ቤት ገብተው ይገኛሉ ፡፡ ቀሪዎቹ ነዋሪዎች የተተኮሰውን ጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡ ይህ የህዝብ ወገናዊነት ወይስ ምን ይሉታል ?
3. የህዝብን ሀብትና ንብረት ስልጣናቸውን ተጠቅመው የከበሩ የወረዳ አመራሮች ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ፓርላማ እንዲገቡ ለከፍተኛ ትምህረት ተቋም ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሬት በሽልማት የሚሰጥበት ለህገ-መንግስቱ መሬት መሸጥ መለወጥ ላሳር የተባለበትን ለካቢኔ በሽልማት የሚሰጥበትን ሁኔታ ሲኖር ከዚህ እንደሚቀጥለው ይሆናል
ለአብነት ያክል፡- • የቁጥር 27 ቀበሌን የገበሬውን መሬት የሸጡ ወይም እንዲሸጥ በቃለ ጉባዔ የያዙ የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲበረታቱ የቀበሌው አስተዳዳሪ ግን በ9/ዘጠኝ/ አይነት ክስ ተከሶ ማረሚያ ቤት ይገኛል
• በተጨማሪ11/አስራ አንድ ቤት /ያቃጠለ የአንድ ሰው እግር የቆረጠ ይባስ ብሎ በዚሁ ድርጊቱ ሳይበቃው ከሌላ የካቢኔ ጓደኛው ጋር በመሆን በሽጉጥ ከስደት ተመላሽ የሆነን ግለሰብ በሴት ምክንያት ጠግቦ አደሮች እጁ ላይ ተመትቶ በሆስፒታል በመረዳት ላይ ሲገኝ ይህ ሳያንስ ቤተሰቦቹ ተለቅመው እንዲታሰሩ ተደርጎ ሲቀጡ ጉዳዩን የፈፀሙት ባለስልጣኖች እድሜ ለስልጣን ብለው ሌላውን ባለተራ የጥይት ማረፊያቸውን ይጠብቃሉ።
4. የወረዳው አመራር /የሀብሩ ወረዳ ማለቴ/ ነው ከክልል በመጣ የኦዲት ባለሙያ በተረጋገጠው መሠረት አንድ አመራር ከ44 – 75 ሽህ ብር ከ365 ቀን በላይ በውሎ አበልና መሰል የወጭ ዘዴ ተጠቅሞ ከህግ ውጭ ማድረጋቸው ስለተረጋገጠ የክልሉ ኦዲተር ሪፖርት ቀርቦ እያለ እስካሁን ድረስ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚባለውን በነሱ ላይ ስለማይሰራ በፍታብሄርም ሆነ በወንጀል እንዳይጠይቁ ጠያቂና ተጠያቂ ጠፍቶ የአገር ሀብት ባክኖ ቀርቷል፡፡ አቤት የሚባልበት ቦታ ጠፍቷል ፡፡
5. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ማለትም የገጠር ወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ የሚፈፅማቸውን አላግባብ የሆኑ አሰራሮች መከታተልና መቆጣጠር የተፈፀመውንም ሆነ ችግሮች እንዳይፈፀሙ መከላከል ሲገባቸው ይባስ ብለው የወረዳው ፍ/ቤት ሰብሳቢ ዳኛ ከዳኝነት ነፃ የሆነው እንኳ ሳይቀር የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ካቢኔ ተብየው እነዚህ አመራሮችና ሙሰኞች በህግ እንዳይጠየቁ ምርመራ ሲጀመር ከዞን ጀምሮ ምርመራ እንዲቋረጥ እየተደረገ የዳኝነት ነፃነት በሚጋፋ መልኩ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው ተብሎ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 25 ላይ በግልፅነት ተቀምጦ እያለ ለአመራር /ተሿሚ / ህጉ የማይሰራበት ለሌች ዜጎች ግን ተተንትኖና ተዘርዝሮ የሚሰራበት ወረዳ በመሆኑ ህግ አልባነት ወይስ ህግ የተላበሰ አሰራር ይህን ሁሉም መልሶ አጥቶበታል።
በአጠቃላይ በከተማችንና በወረዳችን ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሰዎች ሰብዓዊ መብት አለመከበር ድብደባ ዛቻና ማስፈራራት በመጠቀም ስልጣናቸውን ለማራዘም ከላይ ታች የሚባዝኑ ስለሆነ ለሀገርም ሆነ ለህዝብ የማይጠቅም በመሆኑ ይህነን አስነዋሪ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የማይመጥንና የማይገልጽ ነውር ተግባር በህዝቡ ስምና በራሴ ስም ለአየር ይበቃ ዘንድ መልካም ትብብራችሁን ከአክብሮት ጋር እንደማትነፍጉኝ በመተማመን አቀርባለሁ፡፡





ከአምቦ ተፈናቅለው በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተጠለሉ የአማራ ተወላጆችን አስመልክቶ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የተቀነባበረ ዘጋቢ ፊልም


Tuesday, 25 March 2014



Ethiopia: Concern Mounts Over Humanitarian Crisis in Lower Omo
24 March 2014


PRESS RELEASE



Politicians in Europe and America are adding their voices to the international concern about the Gibe III dam and associated irrigated plantations. The projects will have a catastrophic impact on one of the most culturally and biologically diverse places on earth.
The Lower Omo river valley in Ethiopia and Kenya's Lake Turkana are home to 500,000 tribal people and renowned UNESCO World Heritage sites on both sides of the border.
Italian MEP Andrea Zanoni has asked questions in the European Parliament about the human rights violations surrounding the projects. He has also addressed the involvement of the Italian company Salini Construttori, which is building the Gibe III dam in the Lower Omo.
Lord Jones, a British parliamentarian, has asked questions in the UK Parliament about the use of funds provided by the Department for International Development (DfID) in these forced evictions.
Mark Durkan, a British Member of Parliament, has also written to DfID directly on the subject.
International Rivers has released a video that illustrates how the Gibe III dam, together with the associated sugar, cotton and palm plantations, poses serious hydrological risks to the region.
The projects will also have extreme human costs, by destroying the fisheries, grazing grounds and sophisticated farming systems on which the region's indigenous inhabitants depend. Human Rights Watch has created a set of compelling infographics using satellite imagery, which shows the rapid rate at which these landgrabs are taking place.
Survival and other NGOs have repeatedly denounced the forced eviction of hundreds of Bodi and Kwegu from their homes into resettlement camps, as the government seizes their best agricultural lands to convert into large-scale commercial sugar cane plantations.
International donors such as the United States Agency for International Development (USAID) and DfID have repeatedly failed to investigate the crisis in the region, despite receiving consistent accounts of serious abuse. However, the US Congress last month exposed USAID's cover-up of the situation by legally requiring that US taxpayers' money not be used to fund forced resettlements in Lower Omo.
The British government, however, has yet to introduce similar safeguards and to explain if and when it will apply its 'Good Practice Guidelines and Principles Regarding Resettlement'.

Source allAfrica.com 

የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በተፈናቃዩች ተጥለቀለቀ

ሰበር ዜና
የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በተፈናቃዩች ተጥለቀለቀ
ተፈናቃዩቹ ከጎንደር አካባቢ ተነስተው ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ በመውረድ በእርሻ ስራ የተሰማሩ ገበሬዎች ናቸው፡፡ከ1996ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ደረጃ ‹‹ክልላችንን ለቅቃችሁ ውጡ››ሲባሉ ቆይተዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያው ወደ ግድያ፣ድብደባና ወከባ በማደጉ ለአቤቱታ አካባቢያቸውን ጥለው አዲስ አበባ ለመግባት ተገደዋል፡፡ከተፈናቃዩቹ መካከል የተወሰኑት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን ጽ/ቤት በማምራት አፈ ጉባኤውን ለማናገር ቢሞክሩም ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡የአፈ ጉባኤው ጸሐፊ ጉዳያችሁ ታይቷል ወደ መጣችሁበት ተመለሱ››ያለቻቸው ቢሆንም ተፈናቃዩቹ ‹‹ብንመለስ ሊገድሉን ስለሚችሉ አንመለስም››የሚል አቋም ይዘዋል፡፡
ከ26 የሚልቁ ሰዎች በአደባባይ ድብደባ ደርሶባቸው እጅና እግራቸው እንደተሰበረ የሚናገሩት ተፈናቃዩቹ‹‹አቶ ጌጡ ክብረት የተባለ ግለሰብ በገበያ ቦታ በገጀራ ተቆራርጦ ህይወቱ ማለፉን በሀዘን ስሜት ተውጠው ይናገራሉ፡፡
በአዲስ አበባ ማረፊያ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን የሚገልጹት ተፈናቃዩቹ ወደ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ጽ/ቤት በመምጣት ‹‹ፍትህ እንድናገኝ ለኢትዩጵያ ህዝብ ሰቆቃችንን አሰሙልን››በማለት ተማጽነዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ ‹‹ህገ መንግስቱ በግልጽ እያንዳንዱ ዜጋ በፈለገው ክልል በመሄድ ንብረት ማፍራት እንደሚችል ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ህገ ወጥና አስቸጋሪ ነው››ብለዋል፡፡
ሰበር ዜና
የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በተፈናቃዩች ተጥለቀለቀ
ተፈናቃዩቹ ከጎንደር አካባቢ ተነስተው ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ በመውረድ በእርሻ ስራ የተሰማሩ ገበሬዎች ናቸው፡፡ከ1996ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ደረጃ ‹‹ክል...ላችንን ለቅቃችሁ ውጡ››ሲባሉ ቆይተዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያው ወደ ግድያ፣ድብደባና ወከባ በማደጉ ለአቤቱታ አካባቢያቸውን ጥለው አዲስ አበባ ለመግባት ተገደዋል፡፡ከተፈናቃዩቹ መካከል የተወሰኑት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን ጽ/ቤት በማምራት አፈ ጉባኤውን ለማናገር ቢሞክሩም ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡የአፈ ጉባኤው ጸሐፊ ጉዳያችሁ ታይቷል ወደ መጣችሁበት ተመለሱ››ያለቻቸው ቢሆንም ተፈናቃዩቹ ‹‹ብንመለስ ሊገድሉን ስለሚችሉ አንመለስም››የሚል አቋም ይዘዋል፡፡
ከ26 የሚልቁ ሰዎች በአደባባይ ድብደባ ደርሶባቸው እጅና እግራቸው እንደተሰበረ የሚናገሩት ተፈናቃዩቹ‹‹አቶ ጌጡ ክብረት የተባለ ግለሰብ በገበያ ቦታ በገጀራ ተቆራርጦ ህይወቱ ማለፉን በሀዘን ስሜት ተውጠው ይናገራሉ፡፡
በአዲስ አበባ ማረፊያ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን የሚገልጹት ተፈናቃዩቹ ወደ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ጽ/ቤት በመምጣት ‹‹ፍትህ እንድናገኝ ለኢትዩጵያ ህዝብ ሰቆቃችንን አሰሙልን››በማለት ተማጽነዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ ‹‹ህገ መንግስቱ በግልጽ እያንዳንዱ ዜጋ በፈለገው ክልል በመሄድ ንብረት ማፍራት እንደሚችል ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ህገ ወጥና አስቸጋሪ ነው››ብለዋል፡፡

Nigerian Adeola Fayehun SaharaTV host “Keeping It Real With Adeola” talks about Semyawi party girls (Taitu’s daughters) who arrested for voicing Difficult LIFE of Ethiopians.


Monday, 24 March 2014

ኑ! እንዋቀስ፤ ኢህአዴግንም እናፍርሰው! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)
March 24/2014

(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም)
ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ ደርሷል፡፡ ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ እንዳላልኩ ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው፡፡ እንዲህ ያለ አቋመ-ብርቱነት ደግሞ ድሮ በያ ትውልድ ጊዜ ቀርቷል፡፡ በዘመነ-ኢህአዴግ የተንሰራፋው ጥቅመኝነት (በእነርሱ ቋንቋ ኪራይ ሰብሳቢነት) ብቻ ነው፡፡ ለዚህም በደቡባዊቷ አዋሳ ከተማ ስድስተኛው የድርጅቱ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት፣ አቶ በረከት ስምኦን በብስጭት እየተትከነከነ በደፈናው ለጥቅም ድርጅቱን የተቀላቀሉ አባላት በርካታ መሆናቸውን አምኖ በአደባባይ መናገሩ አስረጂ ሊሆነን ይችላል፡፡ ይህን ንግግሩንም አፍታተን ስናብራራው እንደሚከተለው ሆኖ እናገኘዋለን፡- የግንባሩ አባላት ቁጥር ሰባት ሚሊዮን ገደማ የደረሰው በጥቅም በመደለል፣ በአንድ ለአምስት የጥርነፋ መዋቅር በፍርሃት ተጠፍንጎ በመያዙና በመሳሰሉት ነው (መቼስ አቶ በረከት ከድርጅቱ ጉምቱ መሪዎቹ አንዱ ነውና ዘርዝሮ እንዲያስረዳን
አይጠበቅበትም 


የሆነው ሆኖ አባላቱ እንዲህ የመብዛታቸው ምስጢር የድርጅቱ አምባ-ገነንነት ባህሪይ መገለጫ እንጂ አመላይ አጀንዳ አሊያም
ምትሀታዊ ችሎታ እንዳለው የሚያሳይ አይደለም፡፡ ይህ የትኛውም መሰል ሥርዓት ከተጠናወተው ሁሉንም ከመቆጣጠርና መጠቅለል
(Totalitarianism) አስተሳሰብ የሚሰርፅ ማኪያቬሊያዊ አስተምህሮ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ‹‹አምባገነኖች የአንድ እናት መንትያ ልጆች
ናቸው›› እንዲሉ፤ በ‹‹ቆራጡ መሪ›› ዘመነ-መንግስትም በጊዜው ከነበረው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር አኳያ መሳ-ለመሳ ሊባል በሚያስደፍር
ሁኔታ ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሰማያዊ ካኪ ለባሽ የኢሠፓ አባል ሆኖ ነበር፡፡ ግና፣ ያ ካኪ ለባሽ ሕዝብ፣ የልቡን በልቡ ይዞ ‹‹ቪቫ መንጌ!›› እያለ
አሳስቆ በስተመጨረሻ ጉድ እንደሰራው ሁሉ፤ ‹‹ይህ የህዝብ ማዕበል…›› ተብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ የተሞካሸው የ97ቱ የቅዳሜው መሬት
አንቀጥቅጥ የሰልፍ ትዕይንትም፣ በድጋፍ ሳይሆን በግዳጅ የሰመረ መሆኑን ለማየት፤ አይቶም ለመመስከር ከሃያ አራት ሰአት ጊዜ በላይ
አልወሰደብንም፡፡ እንዴት? ቢሉ በማግስቱ (ሚያዚያ 30) ለተቃውሞ ከወጣው ሕዝብ የቅዳሜዎቹም በብዛት መሳተፋቸውን በራሳቸው
አንደበት ‹‹ትላንት ለቲሸርት፤ ዛሬ ለነፃነት!›› በሚል ሕብረ-ዝማሬ ከአደባባዩም አልፎ ከተማዋን በሚያናውፅ የለውጥ ጩኸት
የመሰከሩበት ‹‹ፖለቲካ›› መቼም ቢሆን አይዘነጋምና፡፡

እንግዲህ ይህ ሁሉ ታሪካዊ ሀቅ የሚገልፅልን አንድ ታላቅ እውነት-በጥቅም እየደለሉ አባልን ማብዛት በክፉ ቀን የማይታደግ መሆኑን ነው፡
፡ ጥቅመኝነት ግፋ ቢል የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹‹ፀበል›› ያስጠምቅ፣ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›ን ያስፎክር ያሸልል ይሆናል እንጂ
የኢትዮጵያን ትንሳኤ መሻትን አያስቀይርም፡፡ ነብር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይለውጠው ሁሉ የኢህአዴግ አባላትም ምንም ቢሆን ምን፣
እንደሌላው ሕዝብ የሀገር አንድነት የሚያሳስባቸው፣ ብሔራዊ ውርደት (ረሀብተኝነት) በቁጭት የሚያንገበግባቸው፣ ከዘውግ ልዩነት
የሕዝብ ለሕዝብ መተማመንና አንድነታዊ ጥንካሬው የሚበልጥባቸው፣ የኃይማኖት ነፃነት የሚያስተቃቅፋቸው… ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
ምክንያቱም ጥቅመኝነት የእጦትን ክፍተት ለመሙላት ለጊዜው ያሰግዳል እንጂ ክብርንና ማንነትን አስሽጦ በባርነት ቀንበር አያሳድርም-
በተለይም ዥንጉርጉርነቱን ጠንቅቆ ለሚያውቀው ኩሩ-ሀበሻ! 

ደግሞስ ምን ያህሉ አባል ነው፣ የድርጅቱን መታወቂያ በመያዙ ብቻ የረባ ጥቅም ያገኘው? በግላጭ እንደሚታየው በግል ጥቅምም ሆነ በተጭበረበረው የዘውግ ፖለቲካ ሳቢያ ኢህአዴግን የተቀላቀሉ የአብዛኞቹ አባላት የኑሮ ደረጃ ዛሬም እንደ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከችግር የመቆራመድ አስከፊ ሕይወት አልተላቀቀም፡፡ ፓርቲውን መታከካቸውም በማይጨበጥና በማይታይ እንቅልፍ የለሽ ሕልም አናውዞ ይበልጥ ደቁሷቸዋል እንጂ በቀን ሶስቴ መመገብ እንኳ አላስቻላቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የድርጅት አባልነታቸው እንደተርታው ሕዝብ በአድሎአዊ አሰራር መማረርን እንዳላስቀረላቸው በርግጠኝነት መመስከር ይቻላል፡፡

ይህ አይነቱም እርግጠኝነት ነው ‹ኑ! እንወቃቀስ (እንነጋገር)፤ እንተማመንምና ሀገርና ትውልድ እየገደለ ያለውን ፓርቲያችሁን አብረን
ተጋግዘን እናፍርሰው› የሚል የማንቂያ ደውል ላሰማችሁ ገፊ-ምክንያት የሆነኝ፡፡ እናም ድርጅታችሁን ትመረምሩ ዘንድ ወደድኩ፡-
ድርጅታችሁ ሥልጣን ላይ ተፈናጥጦ ባሳለፋቸው ሁለት አስርታት የተጓዘበትን መንገድ በአስተውሎት ብትመረምሩ፤ በእርግጠኝነት እንደ
ግዙፍ ዐለት ካገጠጡ ሀገራዊ ውድመቶች እና ከበባድ ኪሳራዎች ጋር መፋጠጣችሁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በቅድሚያ በተልካሻ
ፕሮፓጋንዳ ያሰለቸንን የብሔር ጉዳይ (የተወሰኑ ሰዎችን አማልሎ አባል ለማድረግ አስተዋፆ እንዳለው ባይካድም) ወደጎን ብለን፤
የትኛውም ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶቹን ማክበር፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋው መጠቀም… የፖለቲካ ፓርቲ በችሮታ የሚሰጠው ሳይሆን፣
የማንም ተፈጥሮአዊ መብት መሆኑን ማስረገጥ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ይህ ማለት ግን የድርጅታችሁ ሀቲት፡- ‹አንዱ በሌላው እድሜውን
ሙሉ ሲጨቆን እንደኖረ፤ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ እንደሆነ፤ ከብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ይልቅ የክልሉን እንዲያስቀድም
መቀስቀስና መስበክን የብሔር ብሔረሰብ መብትን ማክበር ነው› የሚለውን አምኖ መቀበል አይደለም፡፡ በግልባጩ ስርዓቱ እንዲህ አይነት
ጉዳዮችን ሰማይ ጥግ አጉኖ፣ ሕዝብን ከፋፍሎና በጥርጣሬ (በጎሪጥ) ወደሚተያይበት ጠርዝ ገፍቶ፣ የሥልጣን ዕድሜውን ያራዘመበት
ሁለት አስርታትን ያሳለፈ ስልቱ መሆኑን መረዳት አይሳናችሁም ብዬ አስባለሁ፡፡

ሌላ ሌላውን ትተን እንኳ የኢህአዴግን አመሰራረት ብንመለከት ግንባሩን ከፈጠሩት አራቱ ድርጅቶች መካከል ከሞላ ጎደል ህወሓት እና
ኢህዴን/ብአዴንን እንደ ፖለቲካ ድርጅት መውሰድ ይቻል ይሆናል እንጂ፤ ኦህዴድና ደኢህዴን፣ በህወሓት ‹‹አባ መላ››ዎች እንደ
የፋብሪካ ሳሙና በሚፈለጉበት መጠንና ቅርፅ ተጠፍጥፈው ከተሰሩ በኋላ በኦሮሞና በደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች ላይ እንደ አለቅት
የተጣበቁ የመሆናቸውን ምስጢር እነርሱም ራሳቸው የሚክዱት አይመስለኝም (ምናልባት በሽግግሩ የመጀመሪያ ዓመት ላይ
እንደአስተዋልነው ከኦህዴድ ይልቅ፣ ኦነግ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን ወክሎ ቢቀጥል ኖሮ ይህ ጉዳይ በዚህ አውድ ላይነሳ ይችል ነበር፡፡ የሆነው
ግን ተቃራኒው ነው፤ የራሱ የፖለቲካ ቁመናና ራዕይ የነበረው በኃይል ተገፍቶ፤ በምትኩ በሌሎች እስትንፋስ ህልው ሆኖ
‹‹የሚያስተዳድረው››ን ሕዝብና ራሱንም ጭምር ቀን ከሌት ‹‹ከብሔር ጭቆና ነፃ አወጣናችሁ›› ስለሚሉት ሞግዚቶቹ ገድል መተረክን
‹‹ፖለቲከኛነት›› አድርጎ የወሰደው ኦህዴድን ያነገሰ ነውና)

በነገራችን ላይ የፖለቲካ ፓርቲን እንደ ፋብሪካ ምርት ጣጣ-ፈንጣጣው ተጠናቅቆለት ሲያበቃ የመጫኑ አሰራር በሁለቱ ክልሎች ብቻ
ተገድቦ የቀረ አይደለም፤ አጋር ፓርቲዎችንም ይመለከታል፡፡ ከአፋር እስከ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል፤ ከሀረር እስከ ሶማሌ ሲተገበር
በትዝብት የተመለከትነው ጉዳይ ነው፡፡ መቼም ገና ከስር መሰረቱ ‹‹እኛ እናውቅልሀለን!›› በሚሉ ‹‹የፖለቲካ ሞግዚቶች›› የተፈጠረ
ድርጅት በምደባ ቦታውን ያገኙ የአመራር አባላቱን በቅምጥል ኑሮ ከማንፈላሰስ በዘለለ፣ ‹‹እወክለዋለሁ›› ለሚለው ሕብረተሰብ ትርጉም
ያለው ስራ ይሰራል ተብሎ የሚታሰብ አይደለምና ‹በኦሮሚያ ሙስና እንደሰላምታ እጅ መጨባበጥ ተዘውታሪና ተራ ነገር ነው›፣ ‹በአፋር
ባጀት መቀለጃ ሆኗል›፣ ‹በሐረር ቤተሰባዊ ኢምፓየር ተገንብቷል›፣ ‹ቤንሻንጉል በድህነት ማቀቀ›፣ ‹ሶማሌ ክልል የአስተዳዳሪው አብዲ
ርስተ-ጉልት ሆነ› ጂኒ ቁልቋል እያሉ ሮሮዎችን ማሰማት ለውጥ አያመጣም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ህወሓትን እንደ ‹‹ግል አዳኝ››
በመቀበላቸው ብቻ ‹‹የአስተዳዳሪነት›› ካባ የተደረበላቸው ምስኪን የአመራር አባላት በቀላል ጉዳይ ላይ እንኳ የመወሰን ሥልጣን
የላቸውምና ነው፡፡

ይህ እንግዲህ በቀጥታ ከኢህአዴግ ስነ-ተፈጥሮ ጋር የሚጋመድ ችግር ነው፡፡ ሆኖም የመንግስት ሥልጣን መዘውር ከጨበጠ በኋላ
የጨፈለቃቸውን የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች ተከትሎ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የደረሱ የአያሌ ሰላማዊ ዜጐች ግድያ፣ እመቃ፣
ከስራና ቤት ንብረት መፈናቀል፣ ስደትን… አንድ በአንድ ጠቅሰን ለማውገዝ ብንሞክር ሰማይ-ብራና፣ ቀይ ባህር-ቀለም ሆነው
ካልተመቻቹልን በቀር የሚደፈር አይመስለኝም፡፡ በርግጥ በኢህአዴግ ውስጥ ታላቅና ታናሽ ንጉሠ-ነገሥት የሆኑት ህወሓትና ብአዴን
ብረት ነክሰው፣ ሳንጃ ወድረው በትጥቅ ትግል ያለፉ ከመሆናቸው አኳያ ለየትኛውም አይነት ቅራኔም ሆነ ልዩነት ከመግደልና መጋደል
ውጪ ያለ ሌላ ሰላማዊ አማራጭ ላይዋጥላቸው እንደሚችል መዘንጋት የለበትም፡፡ ኦነግ ከሽግግር መንግስቱ ከተገፋበት ጊዜ አንስቶ
በኦሮሚያ፣ በአዋሳ፣ በሶማሌ… ግፉአን ያለቁበትን፤ እንዲሁም በድህረ-ምርጫ 97 የታየው የጎዳና ላይ ጭፍጨፋ ይህንኑ ሀቅ ያስረግጣሉ፡፡
ኩነቱም ግንባሩ በመጣበት አይነት የነፍጥ የበላይነት ያለፉት ሶቪየት ህብረት፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ኩባ፣ ኤርትራ ባሉ ሀገራት ከታየው
የሕዝቦች እልቂት፣ የተቀናቃኝ ድምፆች መታፈን፣ የጋዜጠኞች መጨፍለቅ… ጋር ቀጥታ ዝምድና አለው፡፡ እነዚህ ሀገራትንም ሆነ
ኢህአዴግን የተለየ ሃሳብ ለማስተናገድ ትዕግስቱም ፍላጎቱም እንዳይኖራቸው ያደረገው ይህ ከውልደታቸው ጀምሮ ከደም-አጥንታቸው
ጋር የተዋሃደው ተፈጥሮአቸው ይመስለኛል፡፡

በአናቱም ኢህአዴግ ከአባላቱ ይልቅ የአመራሩ ‹‹ፓርቲ›› ብቻ ስለመሆኑ ለመረዳት የውስጥ አሰራሩን መፈትሽ የተሻለ ይሆናል፤
እናንተም በቅርበት እንደምታውቁት በድርጅቱ ያልተፃፈ ሕግ ከላይ ወደታች የሚወርድ መመሪያን ትክክል ሆነም አልሆነ ‹‹ለምን?›› ብሎ
መጠየቅ የሚያስቀስፍ ሀጢያት ነው፡፡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመወያየት መሻት፣ ጥያቄ ማቅረብ፣ ሃሳብን መቃወም፣ ስህተቶችን
ማጋለጥ… አሳድዶ በድንጋይ የሚያስወግር አሊያም ከሀገር ሀገር የሚያሰድድ ታላቅ ጥፋት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ይህ ሁናቴም ነው
የአስተዳደር ድክመቶቹንም ሆነ አውዳሚ ጉድለቶቹን በፍጹም ለሕዝብ እንዳይደርሱ ገትሮ መያዝን የማይዘናጋበት ዋነኛ መንግስታዊ ስራ
ያደረገው (የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በውሃ ቀጠነ ወደ እስር ቤት ሲያግዝ መክረሙን ልብ ይሏል)
በጥቅሉ ድርጅቱ ለአመራሮቹ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በተደረገባቸው ዘመናዊ “V8” መኪናዎች እንዲምነሸነሹ እና በቢሊዮን
የሚቆጠር የሀገር ሀብት እንዲዘርፉ የሚያስችል ስልጣን ከማጎናፀፉ ባለፈ፤ እናንተ (ብዙሀኑ አባላት) ያተረፋችሁት ምንድር ነው?
በአነስተኛና ጥቃቅን ከመደራጀት፣ ‹‹ኮብል-ስቶን›› ፈልጦ ከመደርደር የዘለለስ ማን ምን ሊጠቅስ ይችላል? እስቲ! የተራቆተችና በድህነት
ወጀብ የተንገላታች ሀገራችሁን በዓይነ-ልቦናችሁ ለማስተዋል ሞክሩ፡፡ ያን ጊዜም ገና ጀንበር ስታዘቀዝቅ ስጋቸውን ለመቸርቸር ጎዳናዎችን
የሚያጥለቀልቁ እምቦቀቅላ እህቶቻችን፣ ‹‹ማምሻም ዕድሜ ነው›› እንዲሉ የመፅዋች ዓይን እየገረፋቸው በልመና ቁራሽ ሕይወታቸውን
ለማቆየት የሚውተረተሩ አዛውንትና ህፃናት፣ በየጎዳናው በየሰፈሩ ሲንገላወዱ የሚውሉ ስራ-አጥ ወጣቶች፣ በቀን አንዴ ለመመገብ ላይ
ታች የሚማስኑ ለፍቶ አዳሪዎች… ምድሪቷን እንዳጨናነቋት ይገለፅላችኋል፡፡ የዚህ ሁሉ መንስኤም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ፅንፈኛው
ድርጅታችሁ በሚከተለው በተግባር ያልተፈተነ (የሀገሪቱን ተጨባጭ እውነት ያላገናዘበ) ርዕዮተ-ዓለም፣ ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሰራር፣
ሙስና እና ለኃላፊነት የማይመጥኑ ‹‹አስፈፃሚዎች›› ችግር ስለመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ጥርጣሬ አይግባችሁ፡፡ እናም ጉዳዩ የሀገር ነውና
በግልፅ እንወቃቀስ (እንነጋገር)፤ ስለምንድነው በአባልነት በምታገለግሉት ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ‹ዛሬም በስኬት ጎዳና
እየጋለብኩኝ ነው› ብሎ እንደ ቁራ እየለፈፈ በተግባር ግን፡- መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ፣ ኔት-ወርክ እንደ አደይ አበባ በዓመት አንዴ ብቻ
ብቅ የሚለው? በአገልግሎት ተቋማት መጠቀምስ እንዲህ የአሲምባን ያህል ያራቀው ማን ነው? ፍትሕን የጠሉትን መበቀያ መሳሪያ
አድርገው ያረከሱት እነማን ናቸው? ሰርቶ መብላት የማይጨበጥ ጉም የሆነብንስ በማን የተነሳ ነው? …በርግጥ ይህንን ጥያቄ ለጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ብናቀርብለት እንደ መለስ ዜናዊ በተረት መሳለቁ ባይሆንለትም፣ ‹‹ሰለሜ ሰለሜ››ን እየጨፈረ፤
እነ‹‹ሚካኤል ስሁል›› በቀደዱለት ልክ ዳናኪራውን እያስነካው ‹‹ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም!›› ብሎ ከመዘባበት አይመለስም፡፡
መቼስ እንደዚህ ሕዝብ የተናቀ የትም አይገኝም፡፡

ኢህአዴግ መፍረስ ያለበት ለምንድን ነው?

ይህንን አጀንዳ ለማንሳት መግፍኤ የሆነው ከላይ ለማሳያ ያህል የተጠቀሱት ስርዓታዊ ጥፋቶች በግላጭ የመታየታቸው እውነታ ብቻ
አይደለም፤ ይልቁንም ድርጅቱ ከስሁት መንገዱ ለመታረም (ለመታደስ) ፍፁም ዝግ-በር የመሆኑ ጉዳይ ጭምርም ነው፡፡ አዎን፣ እነዚህ
አሁን ሁላችንንም እያማረሩ ያሉ አብዛኞቹ ችግሮች የተከሰቱት አንጋፋው ድርጅታችሁ የ‹‹ኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ
ግንባር›› የሥልጣን መሰረቱን ለማፅናት ይሁነኝ ብሎ ከደፈጠጣቸው መብቶች ጋር ተያይዘው ከመሆናቸው በዘለለ ለኢኮኖሚያዊ
ጥያቄዎች በቂ ምላሽም ሆነ ሁነኛ መፍትሔ የሌለው ፀረ-ሕዝብነቱ የተረጋገጠ፣ ለመታረም ዝግጁ ያልሆነ፣ ተስፋችንን ያሟጠጠ ስርዓት
ስለሆነም ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ እነበረከት ስምኦን ልባቸው ከኢህአፓ ለመኮብለሉ አብይ ምክንያት አድርገው ያቀረቡትን ችግር
ታዬ የተባለ ታጋይ ‹‹ሞናሊዛ›› በሚለው ግጥሙ ግሩም አድርጎ ገልጦት እንደነበረ በ1993 ዓ.ም ‹‹ፅናት›› በሚል ርዕስ የተጋድሎ
ታሪካቸውን ባሳተሙበት መጽሐፍ ላይ ተርከውታል፡፡

‹‹አንተ ሌዎናርዶ የሮማ ጅል
የሰራሀትን ልታሻሽል
ልታፈርሳት ልትገነባት
ደግመህ ደጋግመህ ልትሰራት
ሰልሰህ ልትሰራት ስትችል
ጣኦት አደረግካት በሞትህ አጉል አጉል
ለራስህ ፍጡር እግዚኦ ልትል››

ይህ ግጥም በሰፈረበት ገፅ ላይ የተጠቀሰው የግርጌ ማስታወሻ ደግሞ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት እንዲህ በማለት አብራርቶታል፡-
‹‹ታዬ የሚባል የኢህአፓ ታጋይ ‹ራሳችን የፈጠርነውን ድርጅት ማስተካከል አለብን› የሚል እምነት የነበረው ሲሆን፣ ዳ ቪንቺ እራሱ
ለሳላት ሞናሊዛ ፍቅር እንደተማረከ ሁሉ እኛም የፈጠርነውንና የተበላሸውን ድርጅት አመለክነው፤ ማስተካከልም ተሳነን በማለት ፓርቲው
ላይ እምነት ማጣቱን ‹ሞናሊዛ› በሚል ርዕስ በፃፈው ውብ ግጥም ገለፀ፡፡›› (ገፅ 61)

እነሆም አብዮታዊ ግንባሩ፣ ከመስራቾቹ አንዱ የሆነው ኢህዴን/ብአዴን፣ ያን ጊዜ ኢህአፓን መክሰሻ ባደረገበት ‹‹ድርጅታዊ አምልኮ››
ራሱም ተጠልፎ ከወደቀ ዓመታት ነጉደዋል፡፡ ታዬ እንዳለውም መሪዎቹ ኢህአዴግን ናቡከደናፆር አሰርቶት እንደነበረው አይነት እጅግ
ግዙፍ ‹‹አምላክ›› (ጣኦት) አድርገው ሀገርና ሕዝብን እየገበሩለት (እየሰዉለት) ነው፡፡ ርዕዮተ-ዓለምም ሆነ ፖሊሲ (በተለይ መሬትን
በተመለከተ) ‹‹የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው›› ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ፖሊሲውም እንዲህ ትውልድን
እየገደለም እንዲሻሻል ያልተሞከረው በዚሁ እምነታቸው ይመስለኛል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው እናንተም የምትስማሙባቸውን ታላላቅ ሀገራዊ
ችግሮችን ለመፍታት ኢህአዴግን ከማፍረስ ውጪ አማራጭ እንዳይኖር ያደረገው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያም ከጥፋቱ ታርሞ ለሀገር የሚጠቅም
ዲሞክራሲያዊ የህዝብ ሥርዓት ሊያነበር ይችላል ብሎ ተስፋ ማድረግ ተላላነት ነው፡፡ እንኳን እናንተ ከተማ ላይ የተቀላቀላችሁት አባላት
ቀርቶ፣ ከበርሃ አቅፈው ደግፈው እዚህ ያደረሱት አንጋፋ ታጋዮችና አንዳንድ አመራሮቹም በድርጅቱ ተስፋ ቆርጠው ጥለውት መሄድ
ከጀመሩ ሰንብቷል፡፡ ታጋይ የውብዳር አስፋው ‹‹ፊኒክሷም ሞታ ትነሳለች›› በሚለው መጽሐፏ እውነታውን እንዲህ በማለት ገልፀዋለች፡-
‹‹የድርጅቱ አመራር የወሰዳቸውን የተሳሳቱ እርምጃዎች ቀድሞ ከነበረኝ የድርጅቱ ግንዛቤ ጋር በማጣመር ለዓመታት የታገሉለትንና
የደከሙለትን አባላት በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ያላስቻለ ድርጅት፣ ለሕዝብ ነፃነትና ለዲሞክራሲ እታገላለሁ ቢል ከይስሙላ የማያልፍ ከንቱ
መፈክር መሆኑን ደምድሜ፣ ከመጋቢት 5 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ ራሴን ከድርጅቱ አገለልኩ፡፡ ይህም በሕይወቴ ጉዞ ዋነኛውና ወሳኝ
እርምጃ ነበር፡፡›› (ገፅ 16)

እንግዲህ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የድርጅት፣ የሴቶች ጉዳይና የመንግስት ሥራዎች ተሰማርታ ልጅነቷን በትግል የጨረሰችው የአቶ
ገብሩ አስራት ባለቤት፣ የውብዳር አስፋው እንዲህ አይነቱን ከባድ ውሳኔ በማሳለፍ ከኢህአዴግ ከተቆራረጠች እነሆ አስራ ሶስት ዓመታት
ነጉደዋል፡፡ በግልባጩ እናንተ ደግሞ እስካሁን ድረስ አንቀላፍታችኋል-ገና አልነቃችሁም፡፡ እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ከዚህ
በላዔ-ሰብ ሥርዓት ለመገላገል የምንችለው፣ ዛሬውኑ ይህንን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ዋነኛና ወሳኝ እርምጃ በቆራጥነት መውሰድ
ስትችሉ ብቻ ነው፡፡ አለበለዚያ…

(የዚህ ጽሑፍ ሃሰበ-መልዕክትን በቅንነት ትቀበሉታላችሁ በሚል መተማመን አፈፃፀሙን፡- በምን አይነት መንገድ ተቀራርበን ልንወያይ እንችላለን? በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ መግባባት ይቻላል? ሃሳቡንስ ከግብ ለማድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? የሚሉትንና መሰል ጥያቄዎችን በሌላ ዕትም ተገናኝተን በስፋት እንመክርባቸዋለን)

አትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Sunday, 23 March 2014

ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ አለማቀፍ የሳይንቲስቶች ሽልማት ተቀበሉ
የሎሬትነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል
ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ፣ በተለያዩ የምርምር መስኮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምርጥ የአለማችን ሴት ሳይንቲስቶች በየአመቱ የሚሰጠው የሎሪያል ፋውንዴሽንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለማቀፍ የሴት ሳይንቲስቶች ሽልማት የ2014 ተሸላሚ ሆኑ፡፡
ተቀማጭነቱን በናይሮቢ ኬኒያ ያደረገው ‘ኢንተርናሽናል ሴንተር ፎር ኢንሴክት ፊዚዮሎጂ ኤንድ ኢኮሎጂ’ የተባለ አለማቀፍ ተቋም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ፤ አፍሪካንና የአረቡን አለም በመወከል ተሸላሚ መሆናቸውን ሲስኮን ሚዲያ የተባለው የፈረንሳይ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ ዶ/ር ሰገነት ለ16ኛው የሎሪያል ፋውንዴሽንና የተባበ...ሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለማቀፍ የሴት ሳይንቲስቶች ሽልማት የበቁት፣ በእጽዋት ምርምር ዘርፍ ባደረጉት ጥናት በተለይ አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶአደሮች ዘንድ ስነ-ምህዳርን የማይጎዳ የሰብል አመራረት ዘዴ ለማስፋፋት ሁነኛ መፍትሄ የሚለግስ ተጨባጭ ውጤት በማግኘታቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ሴቶች በሳይንስ ዘርፍ ለሚያደርጉት ምርምር እውቅና የመስጠትና የማበረታታት ዓላማ ያለው ይህ አመታዊ አለማቀፍ ሽልማት፤ ዘንድሮም ከተለያዩ አህጉራት ለተመረጡና በተለያዩ የምርምር ዘርፎች የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አምስት የአለማችን ምርጥ ሴት ሳይንቲስቶች ባለፈው ረቡዕ ምሽት በፈረንሳይ ፓሪስ በተከናወነ ደማቅ ስነስርአት ላይ የተበረከተ ሲሆን ለተሸላሚዎችም የሎሬትነት ማዕረግ ተሰጥቷል።
የዘንድሮዎቹ አምስት ተሸላሚ ሴቶች፤ ልዩ ተሰጥኦ የታደሉ፣ በሙያቸው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነትና በትጋት የሰሩና አሁንም ድረስ በአብዛኛው ወንዶች በተያዘው የሳይንስና ምርምር መስክ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ በመሆናቸው ለሽልማቱ መመረጣቸውንም ዘገባው ያመለክታል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ያተረፉ ሳይንቲስቶች በሰጡት ጥቆማ መሰረት፣ ራሱን የቻለ ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሞ በተደጋጋሚ ዙር ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ከመዘነ በኋላ በሰጠው ውጤት ነው፣ አምስቱ ተሸላሚዎች ለመጨረሻው ዙር ደርሰው ለሽልማት የበቁት፡፡
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ትምህርታቸውን በአሜሪካ ካጠናቀቁ በኋላ፣ በኮሎምቢያ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ወደ አፍሪካ ተመልሰው፣ ኢንተርናሽናል ሴንተር ፎር ኢንሴክት ፊዚዮሎጂ ኤንድ ኢኮሎጂ በተባለውና ዘርፈ ብዙ ተጨባጭ ተግባራትን እያከናወነ በሚገኘው አለማቀፍ የሳይንሳዊ ምርምር ተቋም ውስጥ በሃላፊነትና በምርምር ዘርፍ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡
ላለፉት 16 አመታት በየአመቱ ሲሰጥ የቆየውን ይህን አለማቀፍ ሽልማት፣ ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ አገራት ሴት ሳይንቲስቶች የተቀበሉት ሲሆን፣ በዘንድሮው አመትም ከኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ከዶ/ር ሰገነት ቀለሙ በተጨማሪ የአሜሪካ፣ የአርጀንቲናና የጃፓን ዜግነቶች ያሏቸው አራት ሴት ሳይንቲስቶች ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡
አንተነህ ይግዛው
ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ አለማቀፍ የሳይንቲስቶች ሽልማት ተቀበሉ
 የሎሬትነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል

         ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ፣ በተለያዩ የምርምር መስኮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምርጥ የአለማችን ሴት ሳይንቲስቶች በየአመቱ የሚሰጠው የሎሪያል ፋውንዴሽንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለማቀፍ የሴት ሳይንቲስቶች ሽልማት የ2014 ተሸላሚ ሆኑ፡፡
ተቀማጭነቱን  በናይሮቢ ኬኒያ ያደረገው ‘ኢንተርናሽናል ሴንተር ፎር ኢንሴክት ፊዚዮሎጂ ኤንድ ኢኮሎጂ’ የተባለ አለማቀፍ ተቋም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ፤ አፍሪካንና የአረቡን አለም በመወከል ተሸላሚ መሆናቸውን ሲስኮን ሚዲያ የተባለው የፈረንሳይ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡  ዶ/ር ሰገነት ለ16ኛው የሎሪያል ፋውንዴሽንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለማቀፍ የሴት ሳይንቲስቶች ሽልማት የበቁት፣ በእጽዋት ምርምር ዘርፍ ባደረጉት ጥናት በተለይ አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶአደሮች ዘንድ ስነ-ምህዳርን የማይጎዳ የሰብል አመራረት ዘዴ ለማስፋፋት ሁነኛ መፍትሄ የሚለግስ ተጨባጭ ውጤት በማግኘታቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ሴቶች በሳይንስ ዘርፍ ለሚያደርጉት ምርምር እውቅና የመስጠትና የማበረታታት ዓላማ ያለው ይህ አመታዊ አለማቀፍ ሽልማት፤ ዘንድሮም ከተለያዩ አህጉራት ለተመረጡና በተለያዩ የምርምር ዘርፎች የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አምስት የአለማችን ምርጥ ሴት ሳይንቲስቶች ባለፈው ረቡዕ ምሽት በፈረንሳይ ፓሪስ በተከናወነ ደማቅ ስነስርአት ላይ የተበረከተ ሲሆን ለተሸላሚዎችም የሎሬትነት ማዕረግ ተሰጥቷል።
የዘንድሮዎቹ አምስት ተሸላሚ ሴቶች፤ ልዩ ተሰጥኦ የታደሉ፣ በሙያቸው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነትና በትጋት የሰሩና አሁንም ድረስ በአብዛኛው ወንዶች በተያዘው የሳይንስና ምርምር መስክ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ በመሆናቸው ለሽልማቱ መመረጣቸውንም ዘገባው ያመለክታል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ያተረፉ ሳይንቲስቶች በሰጡት ጥቆማ መሰረት፣ ራሱን የቻለ ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሞ በተደጋጋሚ ዙር ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ከመዘነ በኋላ በሰጠው ውጤት ነው፣ አምስቱ ተሸላሚዎች ለመጨረሻው ዙር ደርሰው ለሽልማት የበቁት፡፡
ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ትምህርታቸውን በአሜሪካ ካጠናቀቁ በኋላ፣ በኮሎምቢያ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ወደ አፍሪካ ተመልሰው፣ ኢንተርናሽናል ሴንተር ፎር ኢንሴክት ፊዚዮሎጂ ኤንድ ኢኮሎጂ በተባለውና ዘርፈ ብዙ ተጨባጭ ተግባራትን እያከናወነ በሚገኘው አለማቀፍ የሳይንሳዊ ምርምር ተቋም ውስጥ በሃላፊነትና በምርምር ዘርፍ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡
ላለፉት 16 አመታት በየአመቱ ሲሰጥ የቆየውን ይህን አለማቀፍ ሽልማት፣ ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ አገራት ሴት ሳይንቲስቶች የተቀበሉት ሲሆን፣ በዘንድሮው አመትም ከኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ከዶ/ር ሰገነት ቀለሙ በተጨማሪ የአሜሪካ፣ የአርጀንቲናና የጃፓን ዜግነቶች ያሏቸው አራት ሴት ሳይንቲስቶች ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡
አንተነህ ይግዛው
Teddy Afro to represent Africa  for 2014 FIFA Coca Cola  world cup