Monday, 17 March 2014

በሀረር ለ2ኛ ጊዜ የተነሳውን የእሳት አደጋ መንስኤ በተመለከተ የክልሉ መንግስትና ህዝቡ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጠ ነው

በሀረር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ህዝቡ መንግስትን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ መንግስት በበኩሉ ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሀይሎችን ያደረሱት ቃጠሎ ነው ይላል።
ቅዳሜ ምሽት ሲጋራ ተራ እተባለ በሚጠራው የንግድ ማእከል ላይ በተነሳው እሳት በርካታ ንብረት ወድሟል። ከሳምንት በፊት መብራት ሃይል እየተባለ በሚጠራው የንግድ ማእከል በደረሰው ቃጠሎ ደግሞ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚቆጠር ሀብት ወድሟል።





በመጀመሪያው ቃጠሎ ወቅት ብስጭታቸውና ቁጣቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ የወጡ የሃረር ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበው ሲበተኑ ከ40 ያላነሱ ወጣቶች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለው እስከ ዛሬ አልተፈቱም።
ባለፈው ቅዳሜ የተነሳውን እሳት ሰበብ በማድረግ ዝርፊያ ሊፈጽሙ ሲሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መታሰራቸውን የመስተዳድሩ ሹማምንት ለመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ሲገልጹ፣ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከፍተኛውን ዝርፊያ ሲፈጽሙ የነበሩት ፖሊሶች ናቸው ይላሉ። እነዚህ ሰዎች እንደሚሉት ፖሊሶች በተለይም የሞባይል ስልኮችን ሲያሸሹ ነዋሪው በትዝብት ያያቸው ነበር።
አብዛኛው የሃረር ህዝብ እሳት አደጋው መንስኤ መስተዳደሩ ነው ብሎ ያምናል። የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ቦታዎችን ለሚፈለጉ ሰዎች ለመስጠት በማሰብ ቃጠሎውን እንደሚያስነሱ ይገልጻሉ
የሃረሪ መስተዳድር የኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ  ” ከደረሰው አደጋ ጋር በተያያዘ ህዝብና መንግሥትን ለማጋጨትና ድብቅ የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማራመድ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ከመንግሥት ጎን በመሆን እንታገላቸዋለን ” በማለት የእሳቱን መንስኤ በስም ያልተጠቀሱት ድብቅ ሃይሎች ያስነሱት ነው በማለት በመስተዳድሩ ላይ የሚሰነዘረውን ወቀሳ ለማስተባበል ሞክሯል።
እንደ ታዛቢዎች ከሆነ ሀረር ከተማ ከመቼውን ጊዜ በላይ በሃዘን ድባብና በቁጭት ተሞልታለች። ህዝቡ ምን ማድረግ እንደሚገባው ግራ ተጋብቶ እንደሚገኝ ታዛቢዎቹ ይገልጻሉ።
በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን የጦር መኮንኖች መካከል ውጥረት ነግሷል:: ጄኔራል አበባውን ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት የመቀየር እቅድ ተይዟል::
በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን የጦር መኮንኖች መካከል ውጥረት ነግሷል:: ጄኔራል አበባውን ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት የመቀየር እቅድ ተይዟል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ህገመንግስታዊ ጥያቄ ባነሱ ከጄኔራልነት እስከ ሻምበልነት ማእረግ ባላቸው የቀድሞው የኢሕ...ዴን ታጋዮች እና የአሁን የብኣዴን የጦር መኮንኖች እና በሕወሃት ጄኔራሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ያማከለ እና ህገመንግስታዊ ስርኣትን ተከትሏል የተባለለት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን የመከላከያ ምንጮቻችን ጠቁመዋል::
ባለፉት ሰሞናት የተደረጉት ስብሰባዎች በከፍተኛ አለመግባባት የተበተኑ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በስፋት የፓርቲ ስራዎች እንጂ ሃገራዊ ስራዎች እየተሰሩ አይደለም የሚሉ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱ ለህገመንግስቱ መከበር ተገኢ መሆን አለበት በአሁን ወቅት ለአንድ የፓርቲ አመራር እና ለፕሮፓጋንዳ ተገኢ ሆነናል የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን የእድገት የትምህርት እና የደምወዝ መብትን በተመለከተም ከፍተኛ ክርከር ቢደረግም ካለመግባባት መኮንኖቹ ጥርስ እንደተነካከሱ ወደየመጡበት ተበታትነዋል::
የሰራዊት አባላትን ለመቀነስ በተደረገው ጥናት መሰረት ለምን ሁለት ብሄር ላይ አተኮረ የሚሉ ጥያቄ እንዲሁም የስኮላርሺፕ አድሏዊነት በተመለከተ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአንድ ብሄር ለትምህርት ተመርጠው የሚላኩ መኮንኖች በዛው ሳይመለሱ ይቀሩና ነገሩ ይድበሰበሳል የሚሉ አስጨናቂ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢነሱም ከመድረኩ መልስ ሳይሰጥባቸው ተድበስብሰው አልፈዋል::ከአንድ ብሄር ብቻ ተመርጠው ለትምሕርት አውሮፓና አሜሪካ ከሄዱት መኮንኖች 80 ከመቶ ያልተመለሱ ሲሆን ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ሌላው ብሄር ስኮላሺፕ እንዳያገኝ ምክንያት እየተፈጠር በዚያው ስለምትከዱ ሃገር ውስጥ በቂ አካዳሚ ስላለ እዚህ እንድንማር ይደረጋል::ስኮላሺፕ የሚሰጣቸው ለማይመለሱ መኮንኖች ነው የሚሉ አቤቱታዎች ተሰምተዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ
በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል የተነሳውን ፍጥጫ ተከትሎ ጄኔራል አበባውን ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ለማዘዋወር የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮሽች በአሁን ሰአት ጄኔራሉ እንደ ቁም እስረኛ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያሳልፉ እና ወደ ቢሯቸው አልፎ አልፎ እንደሚገቡ ታውቋል::
የሳሞራ የኑስን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጄኔራል አበባው ጄኔራል ዮሃንስን ወደ ሳሞራ ሕወሓት በሹመት አቅርቦ ካመጣቸው በኋላ ይተለያየ ተጽእኖ እየተደረገባቸው ቢሆንም የብኣዴን ፓርቲ አመራሮች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው ቢባልም ምንም አይፈጥሩም የአሽከርነት ሚና ካልሆነ በስተቀር ሲሉ ምንጮሹ ገልጸዋል::የጄኔራል አበባው ስልጣን ማቆም እና ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት መቀየር በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንዳይኖር ሁኔታዎች እየተገመገሙ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት ወደ ውጪ ለእረፍት ለመሄድ ጥያቄ ያቀረቡት ጄኔራል አበባው በተለያየ ምክንያት ሲሰናከልባቸው የቆየ ሲሆን እሳቸውን እና መሰላቸውን ከሰራዊቱ በዘዴ እና በብልሃት ገፍቶ ለማስወጣት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ካሁን ቀደም ሜጄር ጄኔራል የነበሩት አባዱላ ገመዳ አቶ ተብለው ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ሲዘዋወሩ ሁለት ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ደግሞ ወደ እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም::

Sunday, 16 March 2014

አንድነት ለቀጣዩ ምርጫ ቅድመ ሁኔታዎች አስቀመጠ
march 15/2014

ነገ የሦስት ወር ንቅናቄውን በአዲስ አበባ ይጀምራል

 
  ከመድረክ ጋር ያለውን ጥምረት አቋርጦ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የውህደት ድርድር የጀመረው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤በመጪው ዓመት ምርጫ የሚሳተፈው የምርጫው አስፈፃሚ አካላት ነፃና ገለልተኛ መሆናቸው ከተረጋገጠ ብቻ እንደሆነ  ሊቀመንበሩ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ገለፁ፡፡

በ97 ምርጫ ቅንጅት የነበረውን ጥንካሬ ፓርቲያቸው መድገም እንደሚፈልግ የገለፁት ኢ/ር ግዛቸው፤ ህዝቡ ብሶት ላይ ስለሆነ በምርጫው ተቃዋሚዎች በቀላሉ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፓርቲያቸው ወደ ምርጫው የሚገባው ግን ለምርጫው ነፃና ፍትሃዊ መሆን አስፈላጊ የሚባሉት ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ፣ ሚዲያ እና የፍትህ ተቋማት መኖራቸውን ካረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ይህ ጥያቄያችን ከተመለሰ በምርጫው በእርግጠኝነት እናሸንፋለን” ብለዋል የፓርቲው መሪ፡፡

ፓርቲያቸው ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት የተጠየቁት ኢ/ር ግዛቸው፤ አንድነት ከቢሮ እና ከመግለጫ ፖለቲካ ተላቆ ትግሉን ወደ ህዝብ ለማውረድ  ያደረገው እንቅስቃሴ የመድረክ አመራሮችን እንዳስኮረፈና እገዳው እንደተላለፈ ጠቅሰው “እገዳው ትክክል አይደለም፤ አንሱትና ባቀረብነው የውህደት ጥያቄ መሰረት አብረን እንስራ ብለናቸዋል” ብለዋል፡፡

“መድረክ ከአንድነት የተሻለ ጥንካሬ እንደሌለው ገምግመናል” ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ውህደቱን አንፈልግም ቢሉም እንኳን በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ በቅንነት አብረን ልንሰራ እንደምንችል ነግረናቸዋል ብለዋል፡፡

ከእዚህ በኋላ አንድነት በቀጥታ ውህደት ከመፈፀም ውጪ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ግንባርና ቅንጅት የመፍጠር ፍላጎት እንደሌለውም ኢ/ር ግዛቸው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ፓርቲው በነገው እለት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ በአዲስ አበባ የሚጀምር ሲሆን  አጀንዳውም መሬት የግል እንዲሆን የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡ ለ3 ወር ይዘልቃል የተባለውን ይሄን ንቅናቄ በተመለከተ የተጠየቁት ኢ/ር ግዛቸው፤“በአንድነት ፕሮግራም ውስጥ ከመንግሥት ይዞታና ከአንዳንድ ተቋማት ይዞታ በስተቀር መሬት የግል መሆን አለበት በሚል በግልፅ አስቀምጠናል፡፡ ይህን መነሻ አድርገን በመሬት ጉዳይ ላይ ህዝብ ተወያይቶ የራሱን አቋም የሚይዝበት ትልቅ ንቅናቄ አዘጋጅተናል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

 አሁን ያለው የመሬት ፖሊሲ ለኑሮ ውድነቱ መባባስ አስተዋፅኦ አበርክቷል ያሉት ኢ/ር ግዛቸው፤ “የኑሮ ውድነቱ ካለን የመሬት ሃብት ተጠቃሚ ያለመሆናችን ውጤት ስለሆነ፣ ጥያቄያችን የኑሮ ውድነት አጀንዳንም በበቂ ሁኔታ የያዘ ነው” ብለዋል፡፡ መንግስት በበኩሉ፤ መሬት የህዝብና የመንግስት ነው የሚል ፖሊሲ እንደሚያራምድ ይታወቃል፡፡ 
ጋዜጠኛችን ነቢዩ ሲራክ በክፉ ቀን ከወገኑ ጋር በመቆም የሚታወቀው መጠጥ ያለበት ቤት ተገኝተሃል በማለት አሁን በሳኡዲ አረብያ ታስሯል::
በሰው አገር ላይ ወገኔ በማለት እውነተኛውን ከሐሰተኛ እየለየ ለምን ወገን ይጨቆናል እህት ወንድሞቻችን ይበደላሉ በ...ማለት ከኢትዮጵያ ኢምባሲ እስከ አገሪቱ የሳውዲ አረቢያ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቶቾ በመግባት ፍርድ ተጓደለ ደሃ ተበደለ በማለት ለአለም ሕዝብ በማለዳው ወጎቹ እያዋዛ የስደተኛው በደል ያስተጋባልን የነበረ ወንድማችን ነው
አሁን በደረሰበት ነገር በተራችን ድምጻችንን የምናሰማበት ወቅት ነው ከጎኑ በመቆም ልንደግፈው ይገባል

Friday, 14 March 2014




የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተጨማሪ አራት ቀን እስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

 ባለፈው ሰኞ ፖሊስ መረጃ ለማሰባሰብ በሚል ፍርድ ቤት የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆ 5 ቀናት እንደተፈቀደለት ይታወቃል፡፡ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ብዙ ህዝብ ችሎቱን ለመከታተል ተግኝቶአል ዛሬም በዋለው ችሎት የ4 ቀናት ቀጠሮ ተሰጦባቸዋለ

Thursday, 13 March 2014


በጅጅጋ 300 እስረኞች መንገድ ላይ ተጣሉ

በጅጅጋ 300 እስረኞች መንገድ ላይ ተጣሉ


በጅጅጋ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከነበሩ ቁጥራቸው በውል ከማይታወቅ እስረኞች መካከል 300 ያክሉ ከአራት ቀናት በፊት በጅጅጋ መንገድ ላይ መጣላቸው ታውቀ።
የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ያላከውን መረጃ በመንተራስ ኢሳት ባደረገው ማጣራት፣ ባለፈው ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ አካላቸው በምግብ እጦት የከሳ፣ አይናቸው የታወረ፣ እግሮቻቸው ሽባ የሆኑ፣ የአእምሮ መታወክ የደረሰባቸውና አሰቃቂ የእስር ቤት ህይወት እንዳሳለፉ የሚናገሩ እስረኞች በጅጅጋ ጎዳናዎች ላይ ተጥለዋል።
ከተጣሉት መካከል ወላጅ አልባ የሆኑ ምናልባትም በእስር ቤት ውስጥ የተወለዱ ህጻናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች ይገኙበታል።
አብዛኞቹ እስረኞች ከሰውነት ተራ የወጡና በበሽታ የተጠቁ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት ውስጥ የቆዩ ናቸው። ኢሳት ለማረጋገጥ ባይችልም፣ የኦብነግ መረጃ እንደሚያሳየው ከተፈቱት እስረኞች መካከል 20ዎቹ በሶስት ቀናት ውስጥ በበሽታ ሞተዋል።
ከአንድ ወር በፊት ኢሳት ከጅጅጋ ከተማ 25 ኪሜትር ርቆ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ በኮሌራ በሽታ ከ40 በላይ ሰዎች ሞተው በእስር ቤቱ አካባቢ አግባብ ባልሆነ መንገድ በመቀበራቸው አስከሬናቸውን ጅቦች እያወጡ በመብላታቸውና እና አካባቢው በበሽታ በመበከሉ በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ዘግቧል።
የክልሉ መንግስት አሁን የወሰደው እርምጃ በእስር ቤቶች ውስጥ የተነሳውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል እንደሆነ እየተነገረ ነው።
በሶማሌ ክልል የተካሄደውን የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ የክልሉን ገጽታ ያበላሻሉ የተባሉ ከ700 በላይ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችና መታወቂያ የሌላቸው ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ ይታወቃል።

Tuesday, 11 March 2014

“በዴሞክራሲ” ስም የሚደረግ የመሬት ነጠቃና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ
“በዚሁ ከቀጠለ አገሪቷ ወደ እርስበርስ ግጭት ማምራቷ አይቀሬ ነው”
http://www.goolgule.com/in-the-name-of-democracy-land-grab-and-genocide-in-ethiopia/
በአይነቱ የመጀመርያ የሆነ የውይይት መድረክ የካቲት 27 2006ዓም/March 6, 2014/ በኦስሎ፣ ኖርዌይ ከተማ ተደረገ። Frontline Club Oslo በተባለ ድርጅት አማካኝነት በኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ስም እየተካሄደ ያለውን የመሬት ነጠቃ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት በመጥራት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በስብሰባውም ላይም ከውጭ ጉዳይና ከሌሎች መስሪያ ቤቶች፣ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በኦስሎ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለጉዳዩ ቅርበት ያላችው አካላት ተገኝተዋል።
ስብሰባውን የጠራው ድርጅት በመወከል ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ማርየስ ቮንዳርፈር እንደተናገሩት Fronline Club የተባለ ድርጅት በኦስሎ የተቋቋመው በያዝነው ዓመት ሲሆን አላማውም በዓለምአቀፍ ታዋቂ የፊልም እና የፎቶግራፍ ባለሙያዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ እና ምሁራንን በመጋበዝ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶች እና ዶክመንተሪ ፊልሞችን ማቅረብ መሆኑን ገልጸዋል። የዓመቱ ስራውንም የጀመረው በዚሁ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንደሆነ ተመልክቷል።
ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ጠንካራ ነቀፋና ተቃውሞ ያልተለየው መሆኑ ይታወቃል። የዚህም ውይይት ዋና አላማ በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ የሚደርሰውን ችግር ትኩረት ለመስጠትና ተጽዕኖ ለማድረግ የሚያስችሉ አካላትን ጠርቶ ማወያየት ነው። በመሆኑም በውይይቱ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የምዕራባውያን መንግስታት በተለይም የኖርዌይ መንግስት ሚና ምን መሆን እንዳለበት በስፋት ትኩረት ተሰቶበታል። በውይይቱ ላይ አራት የተለያዩ አካላት ንግግር አድርገዋል።
የውይይቱ የመጀመሪያ ተናጋሪም አቶ አብዱላሂ ሁሴን ሲሆኑ እርሳቸውም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪና የኦጋዴን ቲቪ ቻናል ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት ያሰባሰቡትን መረጃ በቪድዮ የተደገፈ ዶክመንተሪ በዚህ ስብሰባ አቅርበዋል። የቀረበው ቪድዮ በክልሉ ፕሬዝዳንት እና በክልሉ ባለስልጣናት፣ ፖሊሶችና የጸጥታ አካላት መካከል የተደረጉ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አካቷል። በክልሉ እየተደረገ ያለውን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ማሰርን፣ ማሰቃየትን፣ ግድያን እና በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ስቃይ ራሳቸው የጸጥታ ኃይሎች የሰጡትን ምስክርነት ዶክመንተሪው አካቷል። በመንግሥት ወታደሮችና ፖሊሶች አማካኝነት በክልሉ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ወንጀሎች ዶክመንተሪው በማስረጃነት የሚያሳይ በመሆኑ በቀጣይነት ሄግ ለሚገኘው አለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ አቶ አብዱላሂ አመልክተዋል።
በሶማሌ ክልል በሚሰሩበት ወቅት በተለያዩ ቦታዎች በህዝቡ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ችግር የተመለከቱ መሆኑን ከመጥቀሳቸው በተጨማሪ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ትኩረት እንዳልተሰጠው ተናግረዋል። ዓለምአቀፉ ማህበረሰብም ሆነ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን በመንግስት ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ በቂ መረጃ እንደሌላቸው አቶ አብዱላሂ አመልክተዋል። ይህ የሆነበትን ምክንያት ለማስረዳት ተናጋሪው ሁለት ነጥቦች አንስተዋል። በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ ጋዜጠኞችንና ዓለምአቀፍ ገለልተኛ ድርጅቶች ወደ ክልሉ እንዳይንቀሳቀሱ በመከልከሉ ሲሆን ይህም ድርጊት በተጨባጭ በክልሉ እየደረሰ ያለው እውነታ እንዳይሰማ፣ እንዳይታይ አድርጎታል። በሁለተኛ ደረጃ ኢህአዴግ ምዕራባዊያንን በውሸት የማሳመኑን ስልት የተካነበት በመሆኑ እስካሁን በክልሉ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሸፈኑ ተገቢውን ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል ብለዋል። የሳቸውም አላማ ይህንን የሰበሰቡትን የቪዲዮ መረጃ ለዓለምአቀፉ ህብረተሰብ በማቅረብና በክልሉ የሚደርሰውን የዝር ማጥፋት ወንጀል በማስቆም ለዚህ ተጠያቂ የሚባሉ ባለስልጣናትና የጸጥታ ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
በመቀጠል ንግግራቸውን ያደረጉት እውቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር የሆኑት የተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ የኖርዌይ ህዝብና መንግስት ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአጠቃላይ ሰብዓዊነት እያደረጉ ያለውን አስተዋጽዖ በማድነቅ ንግግራቸውን ጀምረዋል። በግጭትና በተለያዩ የፖለቲካ ቀውሶች ምክንያት በዓለማችን ተጠቂ ህዝቦች ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመሰደዱ ሁኔታ የተለመደ መሆኑን በማመልከት ብዙ ስደተኞች ወደ ኖርዌይ የሚመጡበት ምክንያት አገሪቷ ሃብታም እና የበለጸገች ስለሆነች ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና ለሰብዓዊነት ክብር ቅድሚያ በመስጠቷ መሆኑን አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የመሬት ነጠቃ ሁኔታ በመጥቀስ የኖርዌይ መንግስትና እርዳታ ሰጪዎች ሊወስዱ የሚገባቸውን እርምጃ በንግግራቸው ጠቁመዋል። በመቀጠልም ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት የሚያሳይ ምስል በማቅረብ ምን ያህል አገሪቱ በተፈጥሮ የታደለች መሆኑንና ያገሪቱ ዋና ችግር የመልካም አስተዳደር እጦት እንደሆን አስረድተዋል። በስልጣን ያለው አገዛዝ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ጭቆና አላንስ ብሎ የአገሪቱን መሬት ለህንድ፣ ለቻይና እና ለሳውዲ ኢንቨስተሮች በርካሽ እየሸጠ ይገኛል። በዚህም ምክንያት ከሚሸጠው መሬት የሚፈናቀሉ ዜጎች በአስከፊ የድህነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ በመጥቀስ የሚያፈናቀሉት ዜጎች ህይወት በመሬቱ ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ ኢህአዴግ በኢንቨስትመንት ስም የሚደርገው ድርጊት የዜጎችን ኑሮ አናግቷል። ምዕራባዊያን አገሮችም በተለይም የኖርዌይ መንግስት ይህንን አስከፊ የህዝቡን ስቃይ እና ችግር እያዩ እንዳላዩ በመሆን ለአምባገነናዊ መንግስት የሚያደርጉትን ድጋፍ እና ድጎማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ይገኛሉ። ይህም የምዕራባዊ መንግስታት ዕርዳታ ህዝቡ እራሱን በራሱ ከአምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ እንዳያወጣና ለማውጣት የሚያደርገውን ጥረት ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደሆኑበት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል።
ይህ ሁኔታም በዚሁ ከቀጠለም አገሪቷ ወደ እርስ በርስ ግጭት የማምራት ሁኔታ አይቀሬ መሆኑን በማመልከት ምዕራባዊ አገሮች በተለይ የኖርዌይ መንግስት ይህ ከመሆኑ በፊት የህዝቡ ስቃይ እና እንግልት የሚቆምበትን መንገድ በማፈላለግ እና በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲያብብ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳልባቸው አቶ ኦባንግ አሳስበዋል።
በሶስተኛ ደረጃ ንግግራቸውን ያደረጉት ዮሃን ሂላን የተባሉ የማህበራዊ ምሁር ሲሆኑ በሰሜን እና በምስራቅ አፍሪቃ በልማት ዘረፍ የማማከር እና የምርምር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ከመድረኩ ተጠቅሷል። ባሁን ወቅትም በርገን በሚገኘው በክርስትያን ኤይድ ኢንስቲትዩት ውስጥ እየሰሩ ሲሆን ይህም ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ታውቋል። እኝህ ምሁር ከኢህአዴግ ጋር ያላቸውን ቀረቤታ እና ለአምባገነናዊው መንግስት ያላቸውን አወንታዊ አስተያየት በሚያመለክት መልኩ ንግግር አድርገዋል። በስልጣን ላይ ያለው “መንግሥት” ከጎረቤት አገሮች አንጻር የተሻለ መረጋጋትና የኢኮኖሚ ዕድገት የሚታይበትን መሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን እኝህ ምሁር ባቀረቡት አስተያየት ላይ ከመድረኩም ሆነ ከተሳታፊዎች ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተገለጸው እንደ ዮሃን ሂላን የመሰሉ ምሁር ነን ባይ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝብ በምን ሁኔታ እንዳለ የማያውቁና በተጨባጭ እውነታውን የማያሳይና የተሳሳቱ መረጃዎችን በመጠቀም የምርምር ውጤቶችን የሚያቀርቡ ምሁራን እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን በዚህም የተሳሳተ የምርምር ድምዳሜ ምክንያት ምዕራባውያን መንግስታት የተወላገደ የፖሊሲ አቅጣጫ እንዲከተሉ አድርጓል።
በመጨረሻም በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ጥገኝነት ጠያቂወች ዙሪያ የሚያጠነጥን ዶክመንተሪ ቪድዮ ያቀረቡት አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተማጋች የሆኑት ሶልቬይ ስይቨርሰን ናቸው። ይህንን ዓይነቱን ጥናት ለማድረግ ያነሳሳቸው ዋናው ምክንያት የኖርዌይ መንግስት እና የኢትዮጵያ “መንግስት” ስደተኞችን ለመመለስ ያደረጉትን ስምምነት አሳስቧቸው መሆኑን ተናግረዋል። በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ የኖርዌይ መንግስትም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የጉዳዩን ውስብስብነት እንዳልተመለከተው ጠቁመዋል። ያቀረቡትን ዶክመንተሪ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያቀርቡና የተሻለ የጥገኝነት ፖሊሲ እንዲቀረጽ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አካላት ጥያቄና አሰተያየቶች ሰንዝረዋል። የስብሰባው አዘጋጆችም በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ውይይት እንደሚደረግ በመጠቆም የዕለቱን መረሃ ግብር አጠቃለዋል።
ከስብሰባው ጋር በተያያዘ የተቀናበረ ቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ https://www.youtube.com/watch?v=5X8tbN6LLJ4