Sunday, 13 December 2015



በአዳማ የተጠራው ሰልፍ ላይ አቶ በቀለ ገርባ የተገኙ ሲሆን የለበሱት ቲሸርት ላይ ያለውን ምስል ያልተመቻቸው የወያኔ ፓሊሶች አቶ በቀለ ገርባን ከስብስቡ በማግለል ቲሸርታቸውን እንዲያወልቁ ጠይቀዋቸው ሲሆን አቶ በቀለ ገርባም አላወልቅም
( ከቲሸርቱ ስር ምንም አለመልበሳቸው ቲሸርቱን ቢያወልቁት እራቁታቸውን እንደሚሆኑም ገልፀዋል ) በማለት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ።
ሰልፉን ማድረግ አልቻላችሁም ቀጣዩ መፍትሄ ምንድነው ተብለው ለተጠየቁት ትግሉ በጣም አስፈላጊ መሆኑን እና የሰራ ማቆም አድማና ገበሬው ደግሞ ምርቱን ለገበያ ባለማውጣት በሰላማዊ ትግል እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።
አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ ቀደም 4 ዓመት በእስር የቆዩ ሲሆን ፤ እንደተፈቱም በቀጥታ ወደ ትግላቸው ያመሩ ናቸው ። አቶ በቀለ ገርባም ስርዓቱ በህዝ የተመረጠ አለመሆኑ እና ለህዝብ የማያገለግል ባለመሆኑ መለወጥ እንዳለበት አሳስበዋል ።

No comments:

Post a Comment