Tuesday, 29 December 2015

ስብአዊነት ከጎስኝነት ይቅደም (ኦባንግ ሜቶ)

እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን ከጎሳ ይልቅ ሰብአዊነት ቅድሚያ መስጠት አለብን፡ ታላቅ ህዝብና የታላቅ ሃገር ባለቤት መሆን የምንችለው በዚህ ብቻ ነው።
ይህን ለማሳካት የመጀመሪያው ትልም እግዚአብሄር አንተን እንደሚወድህና እንደሚቀበልህ ሁሉ አንተም ራስን መውደድ፤ ራስን ማክበርና የራስን ማንነትን በጸጋ መቀበል ነው፤ ይህም በተሻለ መልኩ ቤተሰብህን፤ አካባቢህን፤ የየወጣህበትን ማህበረሰብ፤ ሃገርህንና ማንኛውንም ሰብአዊ ፍጡር ለመውደድና ለመንከባከብ ያስችልሃል፡
ህወሃት የተዘራውንና በሃገራችን ተንሰራፍቶ ያለውን ይህንን ሁሉ የዘር ጥላቻ፤ ኢፍትሃዊነት በአንድ መሳሪያ ብቻ ማሸነፍ እንችላለን፡፡ይህም መሳሪያ ፍቅር ነው።
የዚህን ጽነሰ ሃሳብ የማይረዱ፤ ይልቁንም የነሱ ህልውና የሚወሰነው ለግል ጥቅማቸው ሌላውን በመጫንና በመደፍጠጥ፤ ባዶ ልባቸውንና መንፈሳቸውን በቁሳቁስ ለመሙላት የሚፈልጉ እንዳሉ መረዳት ያስፈልጋል። ባዶነታቸውን ይሞላልናል ያሉት ቁሳቁስ ግን በፍጹም እርካታን አይሰጣቸው። እኛ ግን ጥሪያችን እግዚአብሄርንና ሌሎችን ራሳችንን የምንወደውን ያህል መውደድ ነው።
ወደፊትስ፤ ለራሳችን ብቻ እናለቅሳለን ወይስ የሌሎችንም ሃዝን ተካፋይ ሆነን የሰቃያቸው ምንጭ የሚደርቅበትን መንገድ ለመፈለግ ከጎናቸው እንሰለፋለን?
በኔ እምነት እያንዳንዳችንን ነጣጥሎ የሚያጠቃንንና የሚረጋግጠንን ዘረኛውን የህወሃት አፓርታይድ ስርዓት ማስቆም የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
ለዚህም ህዝቦች ወደ አንድ መምጣት አለብን፤ እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፡ ኢትዮጵያ የሚጎላት ይህ ነው፡ አፍሪቃን የሚርባት ይህ ነው። (ኦባንግ ሜቶ)

No comments:

Post a Comment