Tuesday, 29 December 2015

ስብአዊነት ከጎስኝነት ይቅደም (ኦባንግ ሜቶ)

እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን ከጎሳ ይልቅ ሰብአዊነት ቅድሚያ መስጠት አለብን፡ ታላቅ ህዝብና የታላቅ ሃገር ባለቤት መሆን የምንችለው በዚህ ብቻ ነው።
ይህን ለማሳካት የመጀመሪያው ትልም እግዚአብሄር አንተን እንደሚወድህና እንደሚቀበልህ ሁሉ አንተም ራስን መውደድ፤ ራስን ማክበርና የራስን ማንነትን በጸጋ መቀበል ነው፤ ይህም በተሻለ መልኩ ቤተሰብህን፤ አካባቢህን፤ የየወጣህበትን ማህበረሰብ፤ ሃገርህንና ማንኛውንም ሰብአዊ ፍጡር ለመውደድና ለመንከባከብ ያስችልሃል፡
ህወሃት የተዘራውንና በሃገራችን ተንሰራፍቶ ያለውን ይህንን ሁሉ የዘር ጥላቻ፤ ኢፍትሃዊነት በአንድ መሳሪያ ብቻ ማሸነፍ እንችላለን፡፡ይህም መሳሪያ ፍቅር ነው።
የዚህን ጽነሰ ሃሳብ የማይረዱ፤ ይልቁንም የነሱ ህልውና የሚወሰነው ለግል ጥቅማቸው ሌላውን በመጫንና በመደፍጠጥ፤ ባዶ ልባቸውንና መንፈሳቸውን በቁሳቁስ ለመሙላት የሚፈልጉ እንዳሉ መረዳት ያስፈልጋል። ባዶነታቸውን ይሞላልናል ያሉት ቁሳቁስ ግን በፍጹም እርካታን አይሰጣቸው። እኛ ግን ጥሪያችን እግዚአብሄርንና ሌሎችን ራሳችንን የምንወደውን ያህል መውደድ ነው።
ወደፊትስ፤ ለራሳችን ብቻ እናለቅሳለን ወይስ የሌሎችንም ሃዝን ተካፋይ ሆነን የሰቃያቸው ምንጭ የሚደርቅበትን መንገድ ለመፈለግ ከጎናቸው እንሰለፋለን?
በኔ እምነት እያንዳንዳችንን ነጣጥሎ የሚያጠቃንንና የሚረጋግጠንን ዘረኛውን የህወሃት አፓርታይድ ስርዓት ማስቆም የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
ለዚህም ህዝቦች ወደ አንድ መምጣት አለብን፤ እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፡ ኢትዮጵያ የሚጎላት ይህ ነው፡ አፍሪቃን የሚርባት ይህ ነው። (ኦባንግ ሜቶ)

በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

በሸዋ በባሌ እና ወለጋ ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬#MinilikSalsawi # Oromo
በወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የታጠቁ የወያኔ ወታደሮች ግቢያችንን ለቀው ይውጡልን ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ጥያቄያቸውን ተሰሚነት ባለማግኘቱ ተጨማሪ ወታደሮች በግቢው ውስጥ ገብተው ተማሪዎችን ሲያባርሩ ሲደበድቡ እና ሲይዙ ተስተውሏል:: በርካታ ተማሪዎች ክፍኛ መጎዳታቸውን እና አንቡላንሶች ሲመላለሱ ነበር ተማሪዎች የዩንቨርስቲውን ግቢ በመልቀቅ ወደየቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ይገኛሉ:: ተቃውሞ በሚካሄድባቸው
አከባቢዎች ኦሮሚኛ ተናጋሪ ያልሆኑ እና ስለ አከባቢው ምንም አይነት እውቀቱ የሌላቸው ወታደሮች በየአከባቢው እየሰፈሩ ይገኛሉ::
እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ሂዳቡ አቦቴ ከተማ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ::በዚሁ ሰሜን ሸዋ ቱሉ ሚልኪ የወያኔ ወታደሮች የእርዳታ
ድርጅቶችን መኪና በመጠቀም ቤት ለቤት እየዞሩ ወጣቱ በማፈስ ላይ ይገኛሉ::በተጨማሪም በባሌ አጋርፋ ዳግም ተቃውሞ ተቀስቅሷል::በሰበታ
መምሕር እና ደራሲ የሆነው ለሚ ግርማ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነ ሲሆን ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል::ተቃውሞውን ወያኔ በቁጥጥር ስር አአዋልኩት ቢልም ከቀድሞውበበለጠ ሁኔታ ተፋፍሞ ቀጥሏል:: # ምንሊክሳልሳዊ

በጋራ ከማልቀስ፣ በጋራ መታገል

በጋራ ከማልቀስ፣ በጋራ መታገል
በአበበ ገላው
ከ66ቱ አብዮት ወሳኝ ትምህርት መቅሰም አለብን። የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች መሬት ላራሹ እና ዳቦ ለተራበው ነበሩ። የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት አልባ አድርጎ ሲያስገብር የነበረው ፊውዳላዊ ስርአት የተንኮታኮተው እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመነሳታቸው ብቻ አልነበረም። ኢትዮጵያውያን ሁሉ በገዥዎችና በተገዢው ጭቁን ህዝብ ያለውን የመደብ ትግል ተረድተው ከዳር እስከዳር በአንድነት መነቃነቅ በመቻላቸው ነበር።
በርግጥ ያለመታደል ሆኖ ያ ህዝባዊ አብዮት በወታደራዊ ሃይል ተቀልብሶ ሌላ አስከፊ አንባገነናዊ ስርአት ተተካ።ከዛ ዘመን በከፋ መልኩ ዛሬ የኢዮጵያን ህዝብ ከመሬቱና ከቀዬው እያፈናቀለ በረሃብ የቀፈደደውን የህዝብ ደም እየመጠጠ በዘር ከፋፍሎ እየቀጠቀጠና እየገደለ የሚገዛ ዘረኛ የውስጥ... ቅኝ ገዢ አስተሳሰብ ያለው የጥቂቶች ዘውጋዊ ስርአት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል እየፈጸመ ህዝብን በመግዛት ላይ ይገኛል።
ስለዚህም ነው የስርአቱ ሰለባ ሁሉ ልዩነቱን አቻችሎ በዘር ቆጠራ ላይ የተመሰረተውን የህወሃቶች ስርወ መንግስት ከስር መሰረቱ ለመጣል በጋራ መነሳትና መታገል የሚገባው። ሰሞኑን በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ አመጽም በድጋሚ ሊያስተምረን የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ ህወሃቶች የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም የማይፈጽሙት ወንጀል የለም። የህዝብ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ህዝብ በአሸባሪነት ፈረጆ ጦርነት ማወጅ የስርአቱን ቀቢጽ ተስፋነት በግልጽ አጉልቶ ያሳየ እውነታ ነው።
የህወሃቶች ስርወ መንግስት በስልጣን ላይ እስካለ ድርስ የየትኛው ህዝብ የመብትና የፍትህ፣ የእኩልነትና የነጻነት፣ የመሬትና የዳቦ ጥያቄ ፈጽሞ ሊመለስ እንደማይችል ግልጽ ነው። በመሆኑም በየአቅጣጫውና በየክልሉ የሚደረገውን ትግል ከፍ አድርጎ ብሄራዊ ንቅናቄ መጀመር የግዜው አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ከውጭም ከውስጥም በህብረት ለመታገል ሁላችንም ልዩነቶቻችንን አቻችለን በቅን ልቦና እንነሳ።
በተለይ ደግሞ አክቲቪስቶችና የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎች ለሚቀርቡላችሁ የጋራ የትግል ጥሪ ፈጣንና አወንታዊ መልስ እድትሰጡ በጭቁ ህዝባችን ስም እማጸናለሁ።
አንድነት ሃይል ነው!


Monday, 28 December 2015

ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ

ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ
አንዳንድ አካባቢዎች ተቀጣጥሎ ይገኛል
========================
ከኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም ትናንትና ዛሬ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል :: ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት አሳፍሪ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሴት ተማሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:፡

ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣

Hiber radio: ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃት በመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ፣ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ፣ ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩን ጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ ፣አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ፣የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ፣ ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙት የኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ እና ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉንhttp://www.hiberradio.com/archives/1556

የካራቶሪው ባለቤት መሬቴን ትነኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናትን አስጠነቀቁ


 በጋምቤላ 300 ሺ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ለማልማት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው የካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ
 መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ከሪፖርትር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የጋምቤላ ክልል መንግስት በግድ ሳይፈልጉ በፈለጉት ዋጋ ከፍለው 300 ሺ 
ሄክታር መሬት እንደሰጧቸው ተናግረዋል። እኔ የጠየቁት 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ያሉት ባለሃብቱ፣ እነሱ ግን 300 ሺ ሄክታር ካልወሰድ ብለው ሰጡኝ ብለዋል። 
መሬታቸውን ማንም እንደማይነጥቃቸው የተናገሩት ባለሀብቱ "መሬቴን ንኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ። ይሄ ማስጠንቀቂያ ነው። የእስካሁኑ የሚበቃ መሰለኝ። ራሴን 
መከላከል አያስፈልግኝም። ባለስልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት ውጤቱን ያገኙታል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ 
ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት 
እንደሚሰጡኝ ይልቁንም እኔ በማምንበት ዋጋ እንድከፍል፣ ከዚያ ያነሰ መሬት ግን እንደማይሰጡኝ አስታወቁ፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፡፡" ተቀበልኩ የሚሉት ባለሃብቱ፣ 
በመካከለኛ ደረጃ ያሉ ባለስልጣናት ፖለቲካውን ተገን አድርገው ሊያሰሩኝ አልቻሉም ብለዋል። ሼክ ሙሃመድ አላሙዲንንም በኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን የቻሉ መንግስት
 ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

Saturday, 26 December 2015

እነ ጌታቸው ሺፈራው 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

እነ ጌታቸው ሺፈራው 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው
በሽብር ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪያቸው ተናግሯል
‹‹ካሁን በፊት ይዝቱብኝ ነበር፤ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የታሰርኩት›› ጌታቸው ሺፈራ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ትናንት ታህሳስ 15/2008 ዓ.ም በያሉበት ታድነው የታሰሩት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ዳንኤል ተስፋየ እና ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ዛሬ ታህሳስ 16/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡...
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በሽብር ተጠርጥረው መታሰራቸውን በመግለጽ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ፖሊስ ታሳሪዎቹ የተጠረጠሩበትን ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪዎች ‹‹የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን፣ በመመልመል፣ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ወንጀል ሊፈጽሙ ሲሉ ተይዘዋል›› ብሏል፡፡
ተጠርጣሪዎች ስለተጠረጠሩበት ወንጀል እና ስለተጠየቀባቸው የጊዜ ቀጠሮ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ይዝቱብኝ ነበር፤ እኔ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የተያዝኩት፡፡ ቤቴ ሲፈተሽ የተገኘውም የህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ሰማያዊና መድረክ) መግለጫዎችና ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ ከተባለው ወንጀል ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ በነጻ ልሰናበት ይገባል›› ሲል ተናግሯል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባሉ አቶ ዳንኤል ተስፋየ በበኩሉ ‹‹በፍተሻ የተያዙብኝ ባንዲራ፣ ሲዲ እና ስልክ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለምርመራ የተጠየቀውን ያህል ጊዜ መፈቀድ የለበትም፤ አጭር ቀጠሮ ይሰጠን›› ሲል ጠይቋል፡፡
ሦስተኛው ተጠርጣሪ አቶ ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ደግሞ ‹‹እኔ በቂርቆስ ክ/ከተማ በኢህአዴግ ተደራጅቼ የምሰራ ሰው ነኝ፡፡ ፖሊስ ከገለጸው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ ድርጅቱን ጭራሽ አላውቀውም፤ የልጅ አባት ስለሆንኩ አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ›› በማለት አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ፖሊስ የጠየቀውን 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለጥር 14/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ከሁለት ወራት በፊት ከአርባምንጭ ተይዘው ወደማዕከላዊ የመጡት በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እነ ሉሉ መሰለ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ለእስር ከተዳረጉት መካከል የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አቶ ኤርሚያስ ጸጋየ፣ አቶ ፍሬው ተክሌ እና አቶ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


"ሰላም በመግባባት እንጂ በሃይል ሊጠበቅ አይችልም!"

Abebe Gellaw
"ሰላም በመግባባት እንጂ በሃይል ሊጠበቅ አይችልም!"
ጦርነት አትቀስቅሱ በሰላም እንኑርበት የምትሉ አንዳንድ ወገኖች የሰላምን ምንነትን የተረዳችሁ አይመስለኝም። በርግጥ "ሰላማችንን ለማደፍረስ እድገታችንን ለማደናቀፍ" የሚል ወያኔዊ ዲስኩር ያለምንም ጥያቄ ዘውትር የሚጋት ሰው የሰማውን ማስተጋባቱ አይቀሬ ነው። ለአለፉት ፵ አመታት በህወሃት ፋሺስታዊ ጦርነት የታወጀበት ህዝብ ምን ሰላም አለው? ለስደት፣ ለእስር፣ ለግድያ፣ ለዝርፊያ፣ ለስቃይና ለውርደት የተዳረገ ህዝብ ምን ሰላም አለው? መሬቱን እየተቀማ ከነቤተሰቡ ከቀዬው የሚባረር ገበሬ ምን ሰላም አለው? በዘረኞች ከፋፍሎ የመግዛት የጥላቻ መርዝ ሰላባ ሆኖ በአገሩ ላይ የመኖር መብት ተነፍጎት ቤቱና ንብረቱ የሚቃጠልበት ብሎም በጠራራ ጸሃይ የሚገደል ምስኪን ምን ሰላም አለው? በስንት... በስዋእትነት የጥንት አባቶቹ ያስከበሩትን ድንበር ላልጠየቀው ሁሉ በችሮታ እና ገጸ በረከት እያደሉ በአገሩ ላይ የመኖር መብት የተነፈገው ህዝብ ምን ሰላም አለው? ጥቂቶች እንዳሻቸው እየዘረፉና እየቀሙ የሚኖሩበት አገር ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በርሃብ በሚያልቁበት አገር ላይ ምን ሰላም አለ? አገር ለዜጎቿ ምድራዊ ሲኦል ሆና የሚሸሸው ወገኔ ለበረሃ አሞራ በየባህሩ ስጋው የሻርክ ቀለብ የሆነበት ህዝብ ምን ሰላም አለው? እውት የተናገረ፣ የጻፈ፣ ያነበበ፣ የነቃና ያነቃ እንደጠላት እየታደነ ለሰቆቃና ግድያ የሚዳረግበት ህዝብ ምን ሰላም አለው?
ህዝባችንን የደም እንባ እያስነቡ በአገሩ ላይ ባይተዋር አድርገው ግፍና በደል እየፈጸሙ ሰላም አታደፍርሱ ማለት ሞኝነት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በሰላም ተኝተው ህዝብ በሰቀቀን እና በሰቆቃ ሊኖር አይችልም። የኢትዮጵያ ህዝብ ለጦርነት እንግዳ አይደለም። እስካሁን ብዙዎችን ግራ ያጋባው እርሱን በመሰሉ የውስጥ ወራሪዎች ሰላም ማጣቱ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጠላቶቹን ተንቅቆ አውቋል። ነጋሪት ጎስሞ ለነጻነቱ ተዋግቶ ማንነቱን ካላስከበረ ሰላም አግኝቶ ሊኖር አይችልም። እኛም ከሩቅ ሆነን "እኔም አገር አለኝ" እያልን የምናንጎራጉርበት ግዜ ማክተም አለበት።
ፋሺስት ጣሊያንም በዘመኑ ሰላም ያደፈረሱ አሸባሪዎች እያለ ብዙ አርበኛ ባደባይ ሰቅሏል። ስለዚህም ነው የዚህ ዘመን ባንዳዎች የአሸባሪነት ክስ ፋይዳ የሌለው የጭንቀት ጣር መሆኑ ግልጽ የሆነው። ነጻነት ወይንም ሞት ብሎ የተነሳን ህዝብ በሃይል ማንበርከች እንደማይቻል ታሪክ ደጋግሞ መስክሯል። አንስታይን ባንድ ወቅት እንዳለው "ሰላም በመግባባት እንጂ በሃይል ሊጠበቅ አይችልም!"
ይህ ትውልድ ዳግም ከፊቱ የሞትና የሽረት ታሪካዊ ጥሪ ተደቅኖበታል። ነጻነት ወይንም ሞት!


Friday, 25 December 2015

ጥቂት ስለ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው - በላይ ማናዬ


Millions of voices for freedom - UDJ's photo.ጥቂት ስለ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው - በላይ ማናዬ
በፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ በተመረቀበት ዘርፍ በመንግስታዊ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ በአጥኚነት ከሁለት አመት በላይ አገልግሏል፡፡ ሆኖም ግን ...የዛሬ አራት አመት በፖለቲካ አመለካከቱ ልዩነት ከመስሪያ ቤቱ አባረውታል፡፡
ጌታቸው ይሰራበት ከነበረው መስሪያ ቤት ሲባረር ተመልሶ ወደ መንግስታዊ መስሪያ ቤት ቅጥር ማመልከትን አልመረጠም፡፡ ይልቁንስ አብዝቶ ወደሚወደው የሚዲያ ስራ አጋደለ እንጂ! በዚህም በቀድሞዎቹ መሰናዘሪያ ጋዜጣ እና ላይፍ መጽሄት (በኋላ ስሟ ተቀይሮ ‹ፍቱን› ተብላለች) በአምደኝነት ሰርቷል፡፡ ከዚያም የዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ ለ26 እትሞች ያህል ከሄደች በኋላ በጫና ከህትመት መውጣቷን ተከትሎም ጋዜጣዋን በማህበራዊ ድህረ ገጽ እንድትቀጥል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ዛሬ ጠዋት ለእስር እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በጋዜጠኝነት ስራው ላይ ደፋ ቀና ከማለት አልቦዘነም፡፡ በተያዘበት ወቅት እንኳ የፍርድ ቤት ውሎ ለመዘገብ ወደ ስራ እያመራ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ጌታቸው በማህበራዊ ሚዲያም ንቁ ተሳታፊ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ጌች ማዕከላዊ በእስር የሚገኝ ሲሆን የታሰረበትን ምክንያት ግን እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም፡፡

Thursday, 24 December 2015

ጀግና ነሽ ለኔ !!

ጀግና ነሽ ለኔ !!
=====================
እየሩ ዘረኞቹ ኢትዮጵያዊያን አጉረው በሚያሰቃዩበት ተከተሽ ስለ አንድነት ስለ እኩልነት ስለ ፍትህ ስለ ነጽነት ስለ ኢትዮጵያ ክብር ክፍ አርገሽ በመዘመርሽ ከእንዴም ሁለት ሶስቴ በነዚ አውሬወች የተለያዬ መከራወች ደርሰውብሻል !!..... ይሄን መከራና ግፍ ግን ዝም ብዬ ከምጋት እንደ አባትና እናቶቼ አርበኞች " ላረከሱት ሀገር ለናዱት ነጻነት መልሱ ሆኖ መጥትዋል ደረቴን ለአረር ...." ብለሽ ከትግል እጋሮችሽ ጋር የግንቦት 7 አርበኞችን ለመቀላቀል ጥቂት ሲቀርሽ ከመሀል ሱሬ ባላርገ አሜከላ ሆኖ በበቀለ ባንዳ በአውሬወቹ ዘረኞች እጅ እንድትወድቁ አርግዋል ይሄ ባንዳ ከመንገድቹህ በሆዱ ቢይሰናክላቹህም ከአላማቹህ ልንቺ ነው ኢትዮጵያ ከሚለው አርበኝነታቹህ ፎቅ አላረጋቹህም የአርበኞቹ ልጆች !!
እነ... ሰርካለምን እነ እማዋይሽን እነ እርዬትን እነ ኤዶምን እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ያሰቃየ ይንገላታ የዘርኝነት እጅ እውር ድንብር እየሩ ባንቺ ላይም እንደሚበርታ ሳስብ ያመኛል ጽናትሽ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ማለትሽ ያጀግነኛል !!!
እነዚ የዘር ሽሎች የናትን የህትን የሴት
ልጅ ፍቅርን ክብርን አያውቁትም ሀገር በናት ስትመስል ወባ እንደያዘው ያሳብዳቸዋል ለዚም ምስክር እየሩ እናተ ናቹህ በተጨማሪም " የሀበሻ ጀብዱ " የሚለው መጽሐፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያነበው እመክራለው !!
እናተ በስቃይ ውስጥ ያላቹህ ታጋ ጉዋዶቼ የምትከፍሉለት እየከፈላቹህ ያላቹህት መከራ እና እንግልት ከግብ ለመድረስ የመጨርሻው ምእራፍ ላይ ነው በትግል እጋሮቻቹህ ኢትዮጵያ ከዘርኛች እጅ እስክትፈታ የሚቆም ታጋይ የለም !!
ኢትዮጵያ በልጆችዋ ለዘላለም ተክብራ ትኖራለች !! ድል ለአርበኛው ልጆች !!
ሰናይ ቀን......ዱዲ


Wednesday, 23 December 2015

አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ ተገለፀ

አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ እጁ፣ እግሩና ጆሮው ላይ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እጁን ታስሮና ተሰቅሎ በተገረፈበት ወቅት የግራ እጁ አጥንት የተሰበረ ሲሆን የእግር ጥፍሮቹም ተነቅለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጆሮው ላይ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
በተለይ እጁ ላይ ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ተነግሮት የነበር ቢሆንም ከክኒን ውጭ ሌላ ህክምና እንዳልተሰጠው ቤተሰቦቹ ገልፀዋል፡፡ የ17 አመት ፍርደኛ የሆነውና በዝዋይ እስር ቤት የታሰረው አቶ ዘሪሁን በአሁኑ ወቅት ለህክምና ቃሊቲ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ህክምና እንዳላገኘ ቤተቦቹ ገልፀዋል፡፡ የዝዋይ እስር ቤትን ህክምና እንዲያገኝ በጠየቀበት ወቅት ‹‹ከቃሊቲ እስር ቤት ጋር እየተነጋገርን ነው፣ መኪና የለም›› በሚሉ ሰበቦች ህክምና ሳያገኝ ቆይቷል ያሉት ቤተሰቦቹ ወደ ቃሊቲ ከመጣ በኋላም ፖሊስ ሆስፒታል ተመርምሮ መድሃኒት ቢታዘዝለትም የታዘዘለትን መድሃኒት ‹‹ሀኪም አላየውም፡፡ ሀኪም ያረጋግጠው›› እየተባለ ህክምና እንዳያገኝ ተደርጓል ብለዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን የፀረ ሽብር አዋጁ በወጣ በወራት ውስጥ ከታሰሩት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Saturday, 19 December 2015

የትግራይ ሽፍቶች ለምን ወንድሞቻቸውን ይገድላሉ?

የትግራይ ሽፍቶች ለምን ወንድሞቻቸውን ይገድላሉ?
ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም !!
አፄ ምኒልክ ጦራቸውን ሰብስበው በእግርና በበቅሎ ከደቡብ ተነስተው ትግራይ እስቲደርሱ ኤርትራና ትግራይ ምን አድርገው ጠበቁዋቸው? የኢጣልያ ጦር ትግራይን ሰንጥቆ አምባ አላጌ እስቲደርስ ማን ሊያቆመምው ሞከረ? የኢጣሊያ ጦር መቀሌ ገብቶ ሲመሽግ ማን ተከላከለው? ስብሓት እስከዛሬ ሳይገለጥለት ቀርቶ ከሆነ የኢጣልያንን ጦር ከአምባ አላጌ ያስወጣው የምኒልክ ጦር ነው፡፡ ከመቀሌም ምሽግ ያስወጣው የጣይቱ ዘዴና የምኒልክ ጦር ነው፡፡ በኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ተሸፋፍኖ የቆየውን እናፍረጥርጠው ከተባለ ለማን አሳፋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡
...
ስለአድዋው ጦርነት ምስክርነት የሚሰጠን ገለልተኛ ታዛቢ እስክናገኝ ስለማይጨው ጦርነት የነበረ የዓይን ምስክር አንድ በቅርቡ ያነበብሁት መጽሐፍ ትዝ አለኝ፤ አንድ የቼኮዝላቫኪያ ጎበዝ የጻፈውን የሃበሻ ጀብዱ የሚል መጽሐፍ ተጫነ ጆብሬ መኮንን የተባለ ሰው የተረጎመውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳትሞታል፤ አቶ ስብሓት ብቻ ሳይሆን ማንበብ የሚችል ሁሉ ሊያነብበው የሚገባ መጽሐፍ ነው፤ እኔ ፈረንጅ ስለኢትዮጵያ የፃፈውን ማንበብ ከተውሁ ብዙ ዓመታት ሆኖኛል፡፡ ይህንን ግን በአንድ ቀን ተኩል ጨረስሁት፤ የኢትዮጵያን ዘማቾች ከኋላ እያጠቁ ስለነበሩት “የትግራይ ሽፍቶች” ማን ይናገር? የነበረ፤ ነውና እንዲህ ይላል፡-
“ የትግራይ ሽፍቶች ለምን ወንድሞቻቸውን ይገድላሉ?… ከመሀል አገር ስድስትና ሰባት ወር ሙሉ ፍዳውን እያየ ሲጓዝ ከርሞ እዚህ የደረሰው ወንድማቸው፣ የነዚህን ምስኪኖች ህይወትና ንብረት ከጠላት ለመከላከል የገዛ ህይወቱን አልጋ ላይ ጥሎ፣ ቤት ንብረቱን በትኖ መከራውን ባየ ለምን ይገድሉታል?”
እነዚህ ሽፍቶች ወንድሙን የገደሉበት አብቹ የሚባል የአስራ ስድስት ዓመት የሰላሌ ዘማች በጣም ተናዶ የራሱን የግል ቡድን አቋቁሞ ያሳድዳቸው ነበር፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው የአርበኞች ግንቦት 7 መዋቅር ቅድሚያ ሰጥቶ ሊተገበራቸው የሚገቡ ስድስት ተግራት።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው የአርበኞች ግንቦት 7 መዋቅር ቅድሚያ ሰጥቶ ሊተገበራቸው የሚገቡ ስድስት ተግራት። 
.............................................................................................................
አርበኞች ግንቦት 7 በሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ዙርያ የተቀናጀ ትግል እንዲካሄድ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ጥሪ ያደርጋል።
1. በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተካሄደ ያለው ትግል ከአሁኑ በተሻለ ተጠናክሮ እንዲቀጥል! ለዚህም በነኝህ አካባቢዎች ያለው የነኝህ ማህበረሰብ አባላት ብቻ ሳይሆን ባካባቢዎቹ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ትግሉን በስፋት እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን! በትግሉ ሂደትም በአሮሞና በአማራ ሕዝብ መካከል የትግል አጋርነትና የግብ ተመሳሳይነት መኖሩን ማጉላት ይገባናል። በአሁኑ ሰዓት ግፉና ስቃዩ እጅግ ለበረታበት የኦሮሞ ሕዝብ “አለንልህ፣ ከጎንህ ነን” ማለትና በርግጥም ከጎኑ ተሰልፎ መገኘት ይኖርብናል።
2. በሌሎች ክልሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን ትግሉን በያሉበት ባስቸኳይ እንዲቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን! ሌሎች ክልሎችና አካባቢዎች የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች በየአካባቢያቸው ባሉ የአስተዳደር በደሎችና የነጻነት ፍላጎት ላይ ያተኮሩ እንዲሆን ማድረግ ይገባል፤ ሆኖም ግን ለአካባቢያዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው የአገራችን የፓለቲካ ሥርዓቱ ሲለወጥ ብቻ መሆኑ በትግሉ ሂደት ማሳየት ይጠበቅብናል!
3. የኢትዮጵያ መከላከያና ፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም በያካባቢው ስርዓቱን እንዲያገለግሉ የተመለመሉ ሚሊሺያዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የወጡ፤ ራሳቸውም የወያኔ አገዛዝ ሰላባ የሆኑ መሆኑን ሁሌም ማስታወስ ይገባል። አርበኞች ግንቦት 7 ይህ የኢትዮጵያ ሰራዊት በወንድሞቹ፣ እህቶቹና ወላጆቹ ላይ እንይተኩስ ይልቁንም አፈሙዙን በዚህ እኩይ ስርዓት ላይ እንዲያዞር በደተደጋጋሚ ጥሪ አድርጓል፤ አሁንም በዚህ ባስራ አንደኛው ሰዓት ይህንን ህዝባዊ ጥሪ በድጋሚ እናደርጋለን! በትግሉ ውስጥ የምትሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ጥሪ በየትግሉ አደባባይ ማስተጋባት፤ በጎናችን ለምናገኘው ጎረቤታችን፤ ዘመዳችን ወይንም ጓደኛችን ለሆነ የዚህ ያፈና መዋቅር አባል ሁሉ በተደጋጋሚ መንገር አንርሳ!
4. ለኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴድና ህወሓት መካከለኛና አነስተኛ ካድሬዎች እንዲሁም ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለሆናችሁ ሁሉ! እናንተ ዛሬ ከሕዝብ ትግል ጎን ቆማችሁ ራሳቸሁንም ሆነ አገራችሁን መታደግ የምትችሉበት ወቅት መሆኑን እወቁ። ዛሬ የሕዝብን ጥሪ ሳትሰሙ ሥርዓቱን ለመታደግ ግፍ መፈፀማቸሁን ከቀጠላችሁ ነገ ዘራፊ አለቆቻቸሁ የዘረፉትን ለመብላት ሲሮጡ እናንተን የማያስጥሏችሁ መሆኑን መረዳት ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰባችሁ ዘለቄታዊ ጥቅም ይበጃል። አሁኑኑ ሰልፋችሁን አሳምሩ! ነገ አብሮአችሁ ከሚኖረው ህዝብ ጋር አትጣሉ! በትግሉ ውስጥ የምትሳተፉ ኢትዮጵያውያንም ከሕዝብ ትግል ጎን ለመቆም ለሚፈልጉ ለነኝህ ወገኖች መንገዱን አመቻቹላቸው!
5. ደም እየበዛ ሲሄድ ሀሞት እየመረረ እንደሚሄድ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጊዜው ሳይመሽ ቢገነዘቡት ይበጃቸዋል! የኢህአዴግ ባለሥልጣናት አገራችን መመለሻ የሌለው ቀውስ ውስጥ ከመግባቷ በፊት እና የዘረፉትን ንብረት በሰላም ለመብላት በፍጹም የማይችሉበት ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት እየሄዱበት ያለውን የእውር ድንብር መንገዳቸውን ቆም ብለው እንዲያስቡ እንመክራቸዋለን! ለሀገራችን ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚያሻግር ሁሉንም ያሳተፈ ድርድር አሁኑኑ ቢጀምሩ ለራሳቸውም ላገሪቱም እንደሚበጅ ልናሳስባቸው እንወዳለን! ይህን ለማድረግ ደግሞ በቅድሚያ ሰላማዊ ሰዎች መግደልና ማፈንን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፤ የፓለቲካ እስረኞችን በሙሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱና አፋኝ ህጎችን በመሰረዝ ለእንዲህ አይነት ሰላማዊ ሽግግር ዝግጁ መሆናቸውን በተግባር እንዲያሳዩ እንጠይቃቸዋለን!
6. በመጨረሻም በመሳሪያም ሆነ በሌላ መንገድ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኃይሎች ሁሉ እንዲሰባሰቡና ይህን ስርዓት ለማንበርከክም ሆነ በይበልጥም ከዚህ ስርዓት ባሻገር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያ አገራችንን በእውነተኛ እኩልነት፤ በፍትህና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገና የምትታነጽበትን መንገድ በጋራ ለመተለም ባስቸኳይ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ እናደርጋለን!.
ዶር/ታደሰ ብሩ

Friday, 18 December 2015

ፌደራል ፖሊስ የሳተላይት ዲሽን ማዉረድ ጀመረ

ፌደራል ፖሊስ የሳተላይት ዲሽን ማዉረድ ጀመረ
አዲስ አበባ ፦(ታህሳስ 08/2008 )
መብራት በማጥፋት የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያን ለመዝጋት የሚሞክረዉ የኢትዮጵያ መንግስት የፌስ ቡክ የመረጃ ፍስትን ለማመናመን ኔትዎርክን ይዘጋል ሲሉ ኢትዮጵያ ያሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ይከሳሉ። ኢትዮጵያ ሚዲያን አፋኝ ተብላ በተለያዩ የስብዓዊ መብት ድርጅቶች ተደጋጋሚ ክስ የሚቀርብባት አገር መሆኗ ይታወቃል።
የሱልልታ ምንጮች ዛሬ እንደገለጹን በአካባቢዉ ላይ የተሰማሩት የፌደራል ፖሊሶች የግለሰብ ንብረት የሆኑን የሳተላይት ዲሾች እየነቀሉ መዉሰድ መጀመራቸዉን አሳዉቀዋል። ከዉጪ የሚተላለፉ ሚዲያዎችን እየተከታተላቹ ትረብሻላቹ በማለት የሳተላይት ዲሾችን መዉሰድ የጀመሩት የፌደራል ፖሊሶች ያለምንም ማዘዣ የግለሰብ ንብረትን መዝረፍ መጀመራቸዉ ነው የታወቀዉ። ፈዴራል ፖሊሶች ዛሬ ነቅለዉ መዉሰድ የጅመሩትን የሳተላይት ዲሽ ለግላቸዉ ያርጉት ወይም ወደ መንግስት መጋዘን ለማጠራቀም ይዉሰዱት የሚታወቅ ነገር የለም።
ዛሬ በሱልልታ አካባቢ የፌዴራል ፖሊሶች የሳተላይት ዲሾችን እየነቀሉ መዉሰዳቸዉን የገለጹት የሱልልታ ነዋሪዎች መንግስት እየተፋፋመ ያለዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ለማስቆምና የመረጃ ፍሰትን ለማመናንመን ምን አልባት ተመሳሳይ የሳተላይት ዲሽ ዘረፋ በተለያየ የኢትዮጵያ ክልል ሊፈጽም ይችላል ሲሉ ስጋታቸዉን ቢናገሩም በሳተላይት ዲሽ ዘረፋ ሳቢያ የመረጃ ገደብ መፈጠሩ የነጻነት ትግሉን የበለጠ ያፋፍመዋል ሲሉም ገልጸዋል። አክለዉም የኢትዮጵያ መንግስት እየፈጸመ ያለዉ አፈና፣ዘረፋ፣ማፈናቀል፣ማሰር፣መግደል ከኢትዮጵያ ህዝብ ያልተሰወረ በመሆኑ ክእንግዲህ በሗላ ነጻነታችንን በድል ለመቀዳጀት ቁርጠኝነታችንን ማዳበር እንጂ በሳተላይት ዲሽ ዘረፋ የምንገታ አይደለንም ብለዋል።ፌደራል ፖሊስ የሳተላይት ዲሽን ማዉረድ ጀመረ

በዛሬው እለት በኖርዌይ ኦስሎ 18, December, 2015 (ታህሳስ 8, 2008 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ ።

በዛሬው እለት በኖርዌይ ኦስሎ 18, December, 2015 (ታህሳስ 8, 2008 ዓ.ም ) በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ያደረሰውን ግድያ እና በምዕራብ ኢትዮጵይ በጎንደር ክልል ለሱዳን ተላልፎ የሚሠጠውን መሬት ምክንያት በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ፣ ኦስሎ ተደረገ ።
ይህንንም ተከትሎ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ በኦስሎና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የድጋፍ ድርጅቱ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሰልፉ በተጀመረበት ቦታ በመገኛት በግፍ ለሞቱት ...የኦሮሞ ተማሪዎች ዘረኛውና አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በመቃወም ድምጻቸውን አሰምታዋል ::
ሰላማዊ ሰልፉ በኖርዌይ የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 14:00 ጀምሮ እስከ 15:30 የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያኖች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ሲጠይቁ በነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ጥይትን በማዝነብ ኢሰብሃዊ ድርጊት የፈጸመውን ግድያ እንዲሁም ለሱዳን ያለ አግባብ በሚስጥር ተላልፎ ሊሠጥ ስለታሰበው መሬት የተነሳ በጎንደር ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና በጎንደር እስር ቤት ውስጥ ለተገደሉ ወገኖቻችን በመቃወም ቡዙዎችን የገደለውን የወያኔን መንግስት የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በማያዝ እና በማሰማት ተቃውሞቸውን በሀይል ገልጸዋል::
በሰልፉ ላይ ሰልፈኞቹ ያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል የወያኔ መንግስት ገዳይ መንግስት ነው፣ የኦሮሞ ተማሪዎችን በጅምላ መግደል ይቁም፣የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የእኛም ደም ነው፣ በኢትዮጵያ በጅምላ ስለተገደሉት የኦሮሞ ተማሪዎች አዝነናል፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ መንግስት በሚስጥር የሚሰጠው የመሬት ውል ተቀባይነት የለውም የሚሉ ይገኙበታል:: ሰልፈኞቹ በቀጥታ ወደ ኖርዌይጃውያን ፓርላማ ጽህፈት ቤት በመሄድ ለኖርዌይ መንግስት ጉዳዩን በግልጽ ያሳወቁ ሲሆን ኖርዌይ ከወያኔ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረም ጠይቀዋል::
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አመራር አቶ ዳንኤል አበበ፣ የአርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዶ/ር ሙላለም አዳም፣ ከኖርዌይ ሸንጎ አቶ ግደይ ዘራፅዬን፣የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ አመራር ወ/ሮ ዙፋን አማረ የተገኙ መሪዎችና ተወካዪች የወያኔን ግፍ በመቃወም ንግግር አድርገዋል::በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ አቶ ዳንኤል አበበ ወያኔ በዘር ከፋፍለህ ግዛ ስርአት ከታሪካዊ ጠላታችንን ከወያኔ ለመጋላገል የኦሮሞ ወንድሞቻችን የጀመሩትን ህዝባዊ እምቢተኝነት አሁኑኑ በመቀላቀል የምናደርገውን ወገናዊ ግዴታችን ብቻ ሳይሆን ለራሳችንና ለኢትዮጵያ ህልውናም ጭምር የምናደርገው ታሪካዊ የትውልድ ጥሪ ነው በማለት አስተላልፈዋል።
በዚህም ድርጅታቸው በድርጊቱ በጣም እንዳዘኑና በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑና ለሞቱ ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን በመመኘት የታሰሩ ወጣት የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኮይ እንዲፈቱ፣ የዚህም ድርጊት ፈጻሚ አንባገነኖች በአስቸኮይ ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቅ የድርጅቱን የአቋም መልክት ለኖርዌይጃውያን ምክር ቤት ተወካይ ያስረከቡ ሲሆን የምክር ቤቱም ተወካይ ንግግር አድርገው ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ሰአት ተጠናቋል::
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

ከ6ኪሎ ዩኒቨርስቲ 2 ተማሪዎች ታፍነው ተወሰዱ

ከ6ኪሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታፍነው ተወሰዱ
--------
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች የነበሩ ሁለት ሴቶች ምሽቱን በደህንነቶች ከዶርማቸው ታፍነው መወሰዳቸውና የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ስለተማሪዎቹ መሰወር ተጠይቀው "አያገባኝም "የሚል ምላሽ መስጠታቸው በግቢው ውስጥ ተቃውሞ አስነስቷል ።
ሁለቱ ተማሪዎች ሲቪል በለበሱ ሰዎች በተወሰዱበት ወቅት ከለሊት ልብስ በቀር ምንም አለመልበሳቸው ተነግሯል ።
በአሁኑ ሰዓትም ዩኒቨርሲቲው በፖሊሶች ዙሪያውን ተከቦ ይገኛል ።

Thursday, 17 December 2015

ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት በቋራ ህዝብ ውርደት ተከናንበው ተመለሱ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች በዛሬው ዕለት ወደ ቋራ አምርተው ህዝቡን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ ህዝቡ በአንድነት አምፆ ከእነሱ ጋር ፈፅሞ መነጋገር እንደማይፈልግ ገልፆ የውርደትና ሀፍረት ጉንጉን አበባ አንገት አንገታቸው ላይ አስሮ መልሷቸዋል፡፡
የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ አጥንት ፍላጭ የሆነው ጀግናው የቋራ ህዝብ አሳፍሮ የመለሳቸው እነ አባይ ፀሐዬ በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ የፀጥታ ኃይሎችን፣ የዞኑን አመራሮች፣ ወሬ ለማዳመጥና እግር ጥሎት የገባውን ህዝብ ለማወያየት ሞክረው ነበር፡፡ ባለስልጣናቱ ፀረ ሰላም ኃይሎችና አሸባሪዎች ያሏቸውን ጠብመንጃ ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ህዝቡ እንዳይደግፍ ሲያሳስቡ ህዝቡ “ቢመጣ ቢመጣ ከእናንተ የባሰ አይመጣ…” ሲል ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በስማቸው እየነገደ ከሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ጋር እንዳቆራረጣቸው በመግለፅ ህወሓትን ከሰውታል፡፡ ከዚህ በኋላ የህወሓት ደጋፊም እንዳልሆኑ የአቋም ለውጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ በበኩላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ወጡበት ህዝብ አፈሙዝ አዙረው ምላጭ መስበር እንደማይሹና አገዛዙ ወደ ወገናቸው ተኩሱ የሚላቸው ከሆነ አስቀድሞ የጦር መሳሪያቸውን እንዲረከባቸው ጠይቀዋል፡፡

Wednesday, 16 December 2015

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ እንዳደረጋት ገለጸች

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ እንዳደረጋት ገለጸች
በአንድ ወቅት “ደሃ ነኝ… ከዓለማችን የደሃ ሀገር መሪዎች መካከል እኛ አንደኞቹ ነን” ስትል የነበረችው የቀድሞው ሟች ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በገንዘቧና በቤተሰቧ ላይ ያሳደረውን ስጋቷን በፌስቡክ ገጿ ገለጸች::
Screen Shot 2015-12-16 at 3.54.28 AM
ወ/ሮዋ በፌስቡክ ገጿ እንዳለችው “በሰሞኑ በሚሆነው ነገር በጣም በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ እንግዲህ አስራ ሰባት አመት ትግል ቦኅላ ለዚህ ድል በቅተን ደርግን ገርስሰን ለመላው ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲ ያለባት አገር መስርተናል። እና መለስ ልጅነቱን በሙሉ የለፋበትን... አላማ ዛሬ በዚህ ብጥብጥ ባነሱ አደገኛ ቦዘኔዎች ከልማት ታቅበን መቀመጥ በጣም ያሳዝናል በእውነቱ። ስራ አቁሞ ሰልፍ ሲሰለፉ መዋል ምን ይባላል? ብንሰራ አይሻልም? እንደ የድሮ ስርአት ነፍጠኞች ያሁኑ አገር ባይበጠብጡ ይሻላል።”
ወ/ሮዋ አክላም ” ትልልቅ አዋቂ ሰዎች የመለስ አይምሮ ያፈለቀውን ራእይ የሚያስፈፅሙ አሉ ተመርጠው በህዝብ መቶ ድምፅ ተሰጥቷቸ እያሉ አሁን ለምን አገር ይረበሻል? እኔ በእውነቱ ከሆነ ለቤተሰብ ለንብረቴ ማሰብ ጀምሬያለሁ። እርግጠኛ ነኝ ብዙዎች እንደኔው ማሰብ መስጋት ጀምረዋል። ጥሩ አይደለም ሰላም እና መረጋጋት ያስፈልጋል በመጀመሪያ።” ብላለች::
ስለ ባሏ ራዕይ ከሞተ በኋላም እንዲነገር የምትፈልገው ወይዘሮ አዜብ ሕዝብ የመለስን ፓርክ በማቃጠሉ የተሰማትን ስሜት ስትገልጽም “የመለስ እሚያህል ትልቅ ሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ እማይታወቅ ሰው፣ ከዚህ በፊትም እንዳልኩት በፔሮል የሚተዳደር ፕሬዚደንት በሶስት ሺህ ብር ደሞዝ የትም አለም የለም። እና ዛሬ ለመታሰቢያ አንድ ፓርክ ቢሰራ እነዚ ሰልፍ ወጡ የተባሉ አደገኛ ቦዘኔዎች አቃጠሉ አሉ። ሀዘኔ መሪር ነው በእውንት ከሆነ። መለስ ቢያየን ያፍርብናል። ራእይ ሰጥቶን ያ ሁሉ አይምሮ ጨምቆ አውጥቶ እኛ እንዲ ወደ ድንቁርና ስንሄድ ያሳዝነዋል። በቶሎ መንግስ ፀጥታ ሊያስከብር ይገባዋል። እነዚ ቦዘኔዎችም ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።” ብላለች::
የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ ካደረጋት ቀጣይ እቅዷ ገንዘቧን አሽሽታ ወደ ሌላ ሃገር መፈርጠጥ? ይህ የሕዝብ ጥያቄ ነው::


Tuesday, 15 December 2015

Crowd devastated Dutch companies in Ethiopia.

Crowd devastated Dutch companies in Ethiopia.
Everything is destroyed or burned at Sola Grow, a company that grows seedlings.
When protests in Ethiopia, three Dutch agricultural businesses as well as destroyed. A rose grower, a seed company and a grass and livestock farm were targeted by violent protesters.
“Our guards have their guns empty shot in the air, but the attack was unstoppable,” says Jan van der Haar Sola Grow, a company that grows seedlings. ”The office, the machines, the pilot, almost everything is destroyed or burnt and the rest they have looted. A large group of hundreds of insurgents, they were overjoyed.”
No ethnic conflict Van der Haar was not present at the assault. The staff at his company fled into the mountains. A guard was severely beaten by the rebels and is covered with bruises and contusions.
According to the Dutchman goes in the riots not about hatred against whites or Westerners. ”This is the result of political unrest. That is actually permanently in the area west of the capital Addis Ababa. If the federal capital will expand at the expense of the region, they do not pick it.
Heavy damage, the damage for Sola Grow is about two to three tons. ”There was seed where we had grown to four years. Some 50 tons of seed potatoes has gone up in smoke.
Besides Sola Grow is also a rose nursery and attacked the grass and cattle farm Graz Land.Marleen Wassink Graz Land itself was not in her company when it was attacked.
”We were in church Sunday morning when we got a text message from the superintendent that our company was attacked.” Wassink lives with her husband and three children in a town 200 kilometers from their business. ”It was getting restless, so we’re going to live way beyond what a precaution.”
15,000 bales of straw away
Wassink has been three years in Ethiopia. Graz Land is a company that grass and other crops cultivated for entraining cattle. The Wassinks also own a herd: “We had most fortunately brought cows to another dairy company, but our accumulated stock of 15,000 bales of straw is gone, burned or taken away.”
Wassink also thinks that violence is not necessarily directed against whites and Westerners. The problem lies in the ground that have been awarded to the Dutch by the Ethiopian government “. That land was previously used by the locals in their eyes was the land of everyone it now looks like we have usurped it.”.
“Now do not run away”
Despite the risks Graz Land does not plan to leave. ”We can run away now, but the country remains as it is now. It’s a matter of persevering, and setbacks belong.” She wants to pick up the thread as soon as possible.

Monday, 14 December 2015

ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ ወሮበላ መንግስት መከላከያ ሰራዊት ለሁለት ተከፈለ!



Selam Andinat Le Ethiopia's photo.
ሰበር ዜና ! ! ! ምንጭ Gudish weyane
ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ ወሮበላ መንግስት መከላከያ ሰራዊት ለሁለት ተከፈለ!
ዛሬ ከወታደራዊ ደህንነት ቢሮ የወጣዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሰራዊቱ የህወሐትና ፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሚል ተከፍሏል...።፣ በሰሜን በምስራቅ እዝ፤ በደቡብና በምእራብ እዝ ዉስጥ የሚገኙ የእግራኝና የሜካናይዝድ አባላቶች ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ ከጥያቄዎቹ በጥቂቱ
* በአሁኑ ወቅት በመላዉ ሐገሪቱ እየሆነ ስላለዉ ያለመረጋጋት ገለጻ ይደረግልን?
* እኛ ወደ በረሐ ወጥተን የምንንከራተተዉ ለዚህ ደሐና እንክርት እዝብ ሉአላዊነት ነዉ ለምንድን ነዉ ፌደራል ፖሊስና ፖሊስ ሰራዊት ላይ እርምጃ የማይወሰደዉ?
* ቤተሰቦቻችንን ጥለን ሐገር ስንጠብቅ እናነተ ከተማ መሐል ያሉ ቤተሰቦቻችንን ትገድላላችሁ ምን ማለት?
* አርበኞች ግንቦት 7፣ ኦነግ እያላችሁ አታጨቅጭቁን መጀመሪያ ህዝቡ የሚፈልገዉን አድርጉለት ከዚያ ወዲህ ስለ ዉጊያዉ እንነጋገራለን!!
* በጎንደርና በትግራይ በኦጋዴን በተለያዩ ስፍራዎች በጦርነት እየተመታን ነዉ እኛ እንኳን አማጺያንን ልንመክት ቀርቶ በቤተሰቦቻችን ሐሳብ አልቀናል!!
ሌሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነን ህዝባችን ላይ አንዘምትም በማለታቸዉ። በመንግስት ላይ መከላከያዉን አሳምጸዋል በሚል ዉንጀላ ከ20 በላይ አባላት የተከሰሱ ሲሆን የመቶ አለቃ ሪቁቱ ከምስራቅ እዝ በወታደራዊ ደህንነቱ በወጣ ትእዛዝ ትናንት ተወስደዉ የደረሱበት ባለመታወቁ ዉስጥ ለዉስጥ ዉጥረቱ ተባብሷል።
በተያያዘ መረጃ የብሐራዊ ደህንነት የተባለዉ ወንጀለኛ ክፍል ከ001 ቁጥር በወጣ ትእዛዝ መሰረት በመንግስት ጉያ ስር ተቀምጠዉ ከግንቦት 7 እና ኦነግ ጋር በመሳጠር ሁከት ሊያስነሱ ይችላሉ ያላቸዉን 124 የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰራዊት አባላት እንዲያዙ ትእዛዝ ቢተላለፍም!!!~ 84 ቱን በቁጥጥር ስር እንዲያዉል የተላከዉ ሐይል ሁሉንም ሊያገኛቸዉ አለመቻሉን አሳዉቋል።
በተጨማሪአዲስ አበባ ዉስጥ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎችን በማከናወንና የህዝቡን የነጻነት ጥያቄ ለማስቀልበስ ጌታቸዉ አሰፋ የተባለዉ የደህንነቱ ቢሮ ዳይሬክተር ክፉኛ እየተጋ እንደሆነ ያሳወቁን ግለሰብ እንደገለጹት ህዝቡ ከዚህ በኋላ ቦንብ አይደለም ምንም ቢፈነዳ የሚመለስ አይነት ባለመሆኑና በራሱ በደህንነት መስሪያ ቤት ዉስጥ የሚገኙ ትግሬ ያልሆኑ የተለያየ ብሐረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያኖች እንዲህ ባለዉ ነገር ባለመስማማታቸዉና ልዩነት በመፈጠሩ የተነሳ ነዋሪነታቸዉ ጉለሌ አካባቢ የሆኑ አንድ የደህንነት ቢሮዉ ስርጭት ክፍል ( program facilitator ) ግለሰብ በዳይሬክተሩ ትእዛዝ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
ወያኔ ይዉደም! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ
ዛሬ ከወታደራዊ ደህንነት ቢሮ የወጣዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሰራዊቱ የህወሐትና ፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሚል ተከፍሏል...።፣ በሰሜን በምስራቅ እዝ፤ በደቡብና በምእራብ እዝ ዉስጥ የሚገኙ የእግራኝና የሜካናይዝድ አባላቶች ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ ከጥያቄዎቹ በጥቂቱ
* በአሁኑ ወቅት በመላዉ ሐገሪቱ እየሆነ ስላለዉ ያለመረጋጋት ገለጻ ይደረግልን?
* እኛ ወደ በረሐ ወጥተን የምንንከራተተዉ ለዚህ ደሐና እንክርት እዝብ ሉአላዊነት ነዉ ለምንድን ነዉ ፌደራል ፖሊስና ፖሊስ ሰራዊት ላይ እርምጃ የማይወሰደዉ?
* ቤተሰቦቻችንን ጥለን ሐገር ስንጠብቅ እናነተ ከተማ መሐል ያሉ ቤተሰቦቻችንን ትገድላላችሁ ምን ማለት?
* አርበኞች ግንቦት 7፣ ኦነግ እያላችሁ አታጨቅጭቁን መጀመሪያ ህዝቡ የሚፈልገዉን አድርጉለት ከዚያ ወዲህ ስለ ዉጊያዉ እንነጋገራለን!!
* በጎንደርና በትግራይ በኦጋዴን በተለያዩ ስፍራዎች በጦርነት እየተመታን ነዉ እኛ እንኳን አማጺያንን ልንመክት ቀርቶ በቤተሰቦቻችን ሐሳብ አልቀናል!!
ሌሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነን ህዝባችን ላይ አንዘምትም በማለታቸዉ። በመንግስት ላይ መከላከያዉን አሳምጸዋል በሚል ዉንጀላ ከ20 በላይ አባላት የተከሰሱ ሲሆን የመቶ አለቃ ሪቁቱ ከምስራቅ እዝ በወታደራዊ ደህንነቱ በወጣ ትእዛዝ ትናንት ተወስደዉ የደረሱበት ባለመታወቁ ዉስጥ ለዉስጥ ዉጥረቱ ተባብሷል።
በተያያዘ መረጃ የብሐራዊ ደህንነት የተባለዉ ወንጀለኛ ክፍል ከ001 ቁጥር በወጣ ትእዛዝ መሰረት በመንግስት ጉያ ስር ተቀምጠዉ ከግንቦት 7 እና ኦነግ ጋር በመሳጠር ሁከት ሊያስነሱ ይችላሉ ያላቸዉን 124 የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰራዊት አባላት እንዲያዙ ትእዛዝ ቢተላለፍም!!!~ 84 ቱን በቁጥጥር ስር እንዲያዉል የተላከዉ ሐይል ሁሉንም ሊያገኛቸዉ አለመቻሉን አሳዉቋል።
በተጨማሪአዲስ አበባ ዉስጥ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎችን በማከናወንና የህዝቡን የነጻነት ጥያቄ ለማስቀልበስ ጌታቸዉ አሰፋ የተባለዉ የደህንነቱ ቢሮ ዳይሬክተር ክፉኛ እየተጋ እንደሆነ ያሳወቁን ግለሰብ እንደገለጹት ህዝቡ ከዚህ በኋላ ቦንብ አይደለም ምንም ቢፈነዳ የሚመለስ አይነት ባለመሆኑና በራሱ በደህንነት መስሪያ ቤት ዉስጥ የሚገኙ ትግሬ ያልሆኑ የተለያየ ብሐረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያኖች እንዲህ ባለዉ ነገር ባለመስማማታቸዉና ልዩነት በመፈጠሩ የተነሳ ነዋሪነታቸዉ ጉለሌ አካባቢ የሆኑ አንድ የደህንነት ቢሮዉ ስርጭት ክፍል ( program facilitator ) ግለሰብ በዳይሬክተሩ ትእዛዝ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
ወያኔ ይዉደም! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ጠረፍ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ጠረፍ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል።
================================
45 ሱዳናውያን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ተወሰዱብኝ ስትል ጸረ ሰላም ያለቻቸውን በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ዓውግዛለች፥ በተጨማሪም ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጠርፍ ተሻግረው ሸፈቱ ሲል እሄው የሱዳን አረብኛ ጋዜጣ ዘግቧል።
ጋዜጣው እንደዘገበው 45 ሱዳናውያን ዜጎቿ በታጣቂዎች ተይዘው፥ በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ በመተማ ዓካባቢ እንደሚገኙና የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዓሳውቋል ሲል ይገልጻል፥
የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ከሚሰጠው የድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሱዳን ተወልደው ያደጉና በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድንበር ተሻግ...ረው በርሃ መግባታቸው ታውቋል።
በሰሜን ጎንደር የሱዳን ጠረፍ ዙሪያ ከፍተኛ የዓመጽ እንቅስቃሴ እንዳለና የሕዝቡ ቁጣ ግለቱ እየበረታ መሆኑ ከዓካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፥

ሞት ለወያኔ፥ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Sunday, 13 December 2015

ቋራ ዛሬም በተኩስ ስትናጥ አደረች

ቋራ ዛሬም በተኩስ ስትናጥ አደረች:: የጎንደር ግጭት የደም ጎርፍ ፈጠረ:: በህወሃት የተጠነሰሰዉ ሴራ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ አካባቢዉን ሙሉ በሙሉ የጦር አዉድማ አድርጎታል:: በነፍስ ገብያ ያሉ ቁጥር 4 እና ቁጥር 3 የሰፈራ ጣቢያ ያሉ ህፃናት እና ሴቶች ህይወት ተቀጥፎል:: የተረፊት በቋራ ገበሬዎች ጥበቃ
እየተደረገላቸዉ ነዉ:: በአካባቢዉ ገነዉ የነበሩ እና የህወሃትን ስዉር ሴራ ሲያስፈጥሙ የነበሩ የህወሃት ባለሃብቶች እሳቱ እያቃጠላቸዉ ነዉ:: የቋራ ገበሬዎችን በአካባቢዉ ሚኒሻወች በመታገዛቸዉ ግጭቱ መስመሩን እንዳይስት በገበሬዎቹ በኩል ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነዉ:: ከዚህ ጋር በተያያ ግጭቱ በአማራ እና
በቅማንት ማህበረሰብ የተነሳ ለማስመሰል ህወሃት ትጥቅ ለቅማንት በማቀበል ደም ማፍሰሱን ለማስቀጠል ቢሰራም ሊከሽፍበት ችሏል::የቋራ ገበሬዎች በህወሃት ባለሃብቶች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል:: በተያያዘ ዜና በቅማንት እና በአማራ መሃከል ግጭት ተፈጠረ ብሎ መናገር
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለህወሃት ሴራ ማገዝ ነዉ ሲሉ በአካባቢዉ ያሉ ኑዋሪዎች ተናግረዋል::
ቁጥራቸዉ አነስተኛ የሆኑት የዘረኛዉ ትግሬ ቡድን ባለሃብቶች የቅማንት ማህበረሰብ ከጎናቸዉ ለማሰለፍ ያደረጉት ሙከራ ቀላል እንዳልነበር ተናግረዋል:: የቋራ ገበሬዎች የራሳቸዉን መሪ መርጠዉ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸዉ::3/4/2008 Tesfahun Alemneh

ሰማያዊ ፓርቲ ለተገደሉት እና ጉዳት ለደረሰባቸው አጋርነቱን ገለፀ

ሰማያዊ ፓርቲ ለተገደሉት እና ጉዳት ለደረሰባቸው አጋርነቱን ገለፀ
• ከመድረክ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ወስኗል
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ታህሳስ 3/2008 ዓ.ም በካሄደው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ከ‹‹ማስተር ፕላኑ›› ጋር በተያያዘ ለተገደሉትና ጉዳት ለደረሰባቸው የህሊና ፀሎት ያደረገ ሲሆን አጋርነቱን መግለፁንም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
የፓርቲው ብሄራዊ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ውይይት ያደረገ ሲሆን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በተቃወሙት ኢትዮጵያውያን ላይ መንግስት እየወሰደ ያለው ኢ-ሰብአዊ እርምጃ እና ለሱዳን በሚሰጠው መሬት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ ውይይቱ ከመጀመሩ በፊትም ማስተር ፕላኑን በመቃወማቸው በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ለገደሉትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የህሊና ፀሎት እንደተደረገ ሰብሳቢው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ማስተር ፕላኑ አርሶ አደሮችን የሚያፈናቅል እና ለመሬት ቅርምት የሚዳርግ መሆኑን በመግለፅ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ለተገደሉትና ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን አጋርነት የገለፀው ሰማያዊ ፓርቲ በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለና የተደራጀ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግም ተገልጾአል፡፡ ፓርቲ ከመድረክ ጋር ለመስራት ውይይት መጀመሩን የገለፁት አቶ ይድነቃቸው ከበደ በቀጣይም ከመድረክና ከሌሎች በወቅታዊ ችግሮች ላይ ለመስራት ፈቃደኛ ከሆኑ ፓርቲዎች ጋር እንዲሰራ ብሄራዊ ምክር ቤቱ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ኀዳር 27 ቀን 2008 ዓ.ም ‹‹በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል !›› በሚል ባወጣው መግለጫ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙት ኢትዮጵያውያን ላይ መንግስት የወሰደውን ኢ-ሰብአዊ እርምጃ ማውገዙ ይታወሳል፡፡


በአዳማ የተጠራው ሰልፍ ላይ አቶ በቀለ ገርባ የተገኙ ሲሆን የለበሱት ቲሸርት ላይ ያለውን ምስል ያልተመቻቸው የወያኔ ፓሊሶች አቶ በቀለ ገርባን ከስብስቡ በማግለል ቲሸርታቸውን እንዲያወልቁ ጠይቀዋቸው ሲሆን አቶ በቀለ ገርባም አላወልቅም
( ከቲሸርቱ ስር ምንም አለመልበሳቸው ቲሸርቱን ቢያወልቁት እራቁታቸውን እንደሚሆኑም ገልፀዋል ) በማለት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ።
ሰልፉን ማድረግ አልቻላችሁም ቀጣዩ መፍትሄ ምንድነው ተብለው ለተጠየቁት ትግሉ በጣም አስፈላጊ መሆኑን እና የሰራ ማቆም አድማና ገበሬው ደግሞ ምርቱን ለገበያ ባለማውጣት በሰላማዊ ትግል እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።
አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ ቀደም 4 ዓመት በእስር የቆዩ ሲሆን ፤ እንደተፈቱም በቀጥታ ወደ ትግላቸው ያመሩ ናቸው ። አቶ በቀለ ገርባም ስርዓቱ በህዝ የተመረጠ አለመሆኑ እና ለህዝብ የማያገለግል ባለመሆኑ መለወጥ እንዳለበት አሳስበዋል ።

Thursday, 10 December 2015

‹‹እኔ ስያዝ ያየ የ4 አመት ህጻን ለቀናት በፍርሃት ይቃዥ ነበር›› ጦማሪ ዘላለም ወርቃገኘሁ

‹‹እኔ ስያዝ ያየ የ4 አመት ህጻን ለቀናት በፍርሃት ይቃዥ ነበር›› ጦማሪ ዘላለም ወርቃገኘሁ
ዕለቱ ሀምሌ 1/2006 ዓ.ም ነበር፤ ሦስት ሰዓት አካባቢ ይሆናል፡፡ ገና ከእንቅልፌ መነሳቴ ነበር፡፡ እስከ ሰኔ 30/2006 ዓ.ም ድረስ የማስተርስ ዲግሪ መመረቂያ ጽሁፌን እየሰራሁ ስለነበር የተጠራቀመ ድካም ነበረብኝ፡፡ በዚህ ጠዋት አንድ የማውቀው ሰው ደውሎ ‹‹ፈልጌህ ነበር፣ አንዴ ወደ በር ወጣ በልልኝ›› አለኝ፡፡
ከዚያ በቅጡ እንኳ ሳልለባብስ ዓይኖቼን እያሻሸሁ ወደ በር ስወጣ አካባቢው ተከብቧል፡፡ ዞር ዞር ስል ፖሊስና ደህንነት ከቦኛል፡፡ ለሰከንዶች ያህል በድንጋጤ ተሞላሁ፤ በቃ ድርቅ ነበር ያልኩት፡፡ ወዲያው ግን ተመልሼ ተረጋጋሁ፡፡ የሆነ ስሜ ያለበት ወረቀት አጠፍ አድርገው አሳዩኝ፡፡ ከእኔ ስም በተጨማሪ ዳንኤል ሺበሺ የሚል ስም ማየቴ ትዝ ይለኛል፡፡ ሁኔታው ሁሉ ስለገባኝ ድንገት፣ ‹‹ታዲያ ውሰዱኛ!›› አልኳቸው፡፡ በቅጽበት የመጣልኝ ሀሳብ ከዚያ ቦታ ቶሎ ይዘውኝ መሄድ አለባቸው የሚለው ነበር፤ ምክንያቱም እናቴ ይሄን ካየች በድንጋጤ ትሞትብኛለች ብዬ ፈርቼ ነበር፡፡ ደግነቱ በሰዓቱ እናቴ ቤት አልነበረችም፤ ስለዚህ ቶሎ ይዘውኝ ከሄዱ በእንዲህ ያለ ሁኔታ በፖሊስ ተከብቤ ልታየኝ አትችልም፣ ያ ደግሞ ለእኔ ትልቅ እፎይታ ነበር፡፡
ሆኖም ከአካባቢው ቶሎ መሄድ የሚለው ሀሳቤ አልተሳካልኝም፤ ፖሊሶችና ደህንነቶች አካባቢውን ሁሉ ከዘጋጉ በኋላ ወደቤት ገቡ፡፡ ልክ ሲገቡ ፖሊሶቹ መሳሪያቸውን አነጣጥረው ነበር የሚራመዱት፡፡ ለመተኮስ የተዘጋጁ ነበር የሚመስሉት፡፡ በሰዓቱ ከእኔ ሌላ ሁለት የእህቴ ልጆች ግቢው ውስጥ ነበሩ፤ እየተጫወቱ ነበር፡፡ መሳሪያ የለበሱ ሰዎችን ውክቢያ አይተው ህጻናቱ በጣም ደነገጡ፤ አለቀሱ፡፡ አንደኛው ህጻን 4 አመቱ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ባየው ሁኔታ ለቀናት ማታ ሲተኛ ይቃዥ ነበር፡፡ እንዲያውም ወንድሜ ይሄን ተመልክቶ እንዴት ህጻን ልጅ ፊት እንዲህ ታደርጋላችሁ በማለቱ ታስሮ ነበር፤ በበነጋታው ቢፈታም፡፡
ቤት እንደገቡ ፍተሻ ጀመሩ፡፡ እያንዳንዷን ነገር አስሰዋል፡፡ እያንዳንዷ ወረቀት ላይ አስፈርመውኛል፡፡ በጣም ረጂም ጊዜ የወሰደ ፍተሻ ነበር ያደረጉት፡፡ እናቴ ሳትመጣ ቶሎ እንዲጨርሱ ብመኝም ሊጨርሱ አልቻሉም፡፡ ስልክ እየተደዋወሉ ስለሚያገኙት ወረቀት ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ አንድ ‹‹ቃሊቲን በጨረፍታ›› የሚል ጽሁፍ ያለበት ጋዜጣ ሲያገኙ፣ ‹‹ይሄ ምንድነው የሚለው?›› አሉኝ፡፡ ‹‹ቃሊቲን በጨረፍታ›› አልኳቸው፡፡ እነሱም የፌዝ እየሳቁ ‹‹በጨረፍታ ሳይሆን በደንብ ታየዋለህ›› አሉኝ፡፡ ለማስፈራራት የተጠቀሙት እንደሆነ በማሰብ ዝም አልኳቸው፡፡
ሶስት ሰዓት የጀመረው ፍተሻ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ዘልቋል፡፡ ሳትመጣ እንዲወስዱኝ ብፈልግም እናቴ መጣች፡፡ በህይወቴ እናቴ እንዲያ ፊቷ ሲለዋወጥ አይቼያት አላውቅም፡፡ በጣም ደነገጠች፡፡ በኋላ ቀስ እያለች እየተረጋጋች መጣች፤ እንዲያውም በኋላ ላይ ምኝታ ቤቷን ቆማ ያስፈተሸችው ራሷ ናት፡፡ ፍተሻው ሲያልቅ ከነጋ ስላልበላሁ በጣም እርቦኝ ነበር፡፡ ትዝ ይለኛል...ፓስታ ነገር ነበር እሱን በላሁ፡፡ ‹‹እንሂድ›› ሲሉኝ እናቴ ‹‹ልጄን የት ነው የምትወስዱት?›› አለቻቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ‹‹ማዕከላዊ›› አላት፡፡ እኔም በዚሁ የምሄድበትን አወቅሁ፡፡
መኪና ላይ ወጥቼ ከፊትና ከኋላ በታጠቁ ሰዎች በመኪና ታጅቤ ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝ፡፡ እኔን ለመያዝ ወደ አስራ ሁለት ፖሊሶችና አራት ደህንነቶች ነበሩ የተሰማሩት፡፡ ማዕከላዊ እንደደረስን ተመዝግቤ ወደ ውስጥ እንድገባ ተደረግሁ፡፡ መጀመሪያ የገባሁበት ቤት ውስጥ የተቀበለኝ ድምጽ በኦሮምኛ ቋንቋ ስለነበር አልተረዳሁትም፡፡ እኔ የገባሁበት ክፍል ውስጥ የነበሩት እንዳለ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡ ‹‹እስር ቤቶች ቋንቋቸው ኦሮምኛ ነው›› የሚለው ዓረፍተ ነገር በአዕምሮየ መጣ፡፡ ሁሉም በኦሮምኛ ሲያወሩኝ ኦሮምኛ እንደማልችል ነገርኳቸው፤ አማርኛ የሚችሉት አወሩኝ፡፡ ከመካከላቸው አበበ ኡርጌሳ የሚባል ልጅ በጣም አረጋጋኝ፡፡ አወራን፡፡ የሚያወራኝ ስላገኘሁ ደስ አለኝ፡፡

Wednesday, 9 December 2015

ወያኔ በራሱ ወጥመድ -ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም

ኅዳር 2008
ራስን ሳያታልሉ ሌላውን ማታለል አይቻልም፤ ለራስ ካልዋሹ ለሌላ ሰው መዋሸት አይቻልም፤ ዞሮ ዞሮ ወደቤት እንደሚባለው ዞሮ ዞሮ ማታለልም ሆነ ውሸት ማደሪያ ሲያጡ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፤ ያኔ ፈጣሪና ፍጡር ይፋጠጣሉ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ይቆማል፤ በከመረው ውሸት መጠን ነቀፌታ ተሸክሞ ያቃስታል፡፡

የታወሩት ዓይኖቹ ይከፈቱና ሕይወት ነጠላ አለመሆኑን፣ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ውጣ-ውረድ መኖሩን፣ ጥላቻና ፍቅር፣ ጤንነትና ሕመም፣ ደስታና ሐዘን መፈራረቃቸውን፣ የግለሰብ ሕይወት በሞት ተሸንፎ መሻሩን፣ ገንዘብ የማይገዛው ነገር መኖሩን፣ ገንዘብ በከበደ መጠን ማቅለሉን አለማወቅ፣ ገንዘብ የማይመክተው ጦርና በገንዘብ ሊታጠቀው የማይችል መሣሪያ መኖሩን አለማወቅ፣ የደከመ እንደሚያይልና ያየለ እንደሚደክም፣ ዓለማችን በጣም የተያያዘና የተቆራኘ በመሆኑ አንዱን ሲያስነጥሰው ሌላውን እንደሚነዝረው የወያኔ ጎረምሶች አልተረዱም፡፡
ዛሬ ፈጣሪና ፍጡር ተፋጠጡ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ቆሟል፤ በከመረው ውሸት መጠን ውርደትን ተሸክሞ ያቃስታል፤ እያታለሉ ውሸትን መጠምጠም እያታለሉ ውሸትን እንደመተርተር ቀላል አይደለም፤ ውሸት ያከሳል፤ ውሸት ያዋርዳል፤ ውሸት መደገፊያ ያሳጣል፤ ውሸት ወዳጆችን ያሳፍራል፤ ጠላቶችን ያፈነድቃል፡፡
በውሸት ለሌሎች የተገነባው ወጥመድ ሲከፈት ማንም፣ ምንም የለበትም፤ ባዶ ግን አይደለም፤ ባለቤቱ አለበት! ባለቤቱ በገዛ ወጥመዱ ውስጥ! ታለለ የተባለው ሁሉ ዳር ቆሞ አታላዩ መታለሉን እያየ ይስቃል፤ አታላዩ የውሸት ምሰሶው መውደቁን ገና አልተረዳም፤ ውሸቱን አይቶ ወዳጁ እንደከዳው አታላዩ አልገባውም፡፡
ማታለልና መዋሸት በሃያ አምስት ዓመታት ጉዞ ዙሪያውን ገደል አደረገው፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአስታራቂነት ጥረት ከብዙ ዓመታት ጦርነት ወጥቶ በሰላም የነበረው ሱዳን አሁን ለሁለት ተገመሰ፤ ለሁለት መገመሱ አልበቃ ብሎ እንደገና ሊገማመስ እየተደባደበ ነው፤ የሶማልያ ትርምስ እየባሰበት ሄደ እንጂ አልተሻለውም፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደተኳረፉ ናቸው፤ ከዚያም በላይ በውክልና እየተቆራቆዙ ነው፤ የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች መጋጨታቸውና ጥቂቶች መሞታቸው አዲስ የሰላም ጠንቅ ነው፤ ጂቡቲ በፈረንሳይና በአሜሪካ ጦር የምትጠበቅ ስለሆነ አይበገሬ ትሆናለች፤ ሆኖም የአዲስ አበባ-ጂቡቲ ባቡር መቆም በጂቡቲ ሕዝብ ላይ የሚያስነሣው ግም ስሜት የለም ለማለት ያስቸግራል፡፡
የምዕራባውን ኃይሎች ፍላጎት ኢትዮጵያ ሰላም የሰፈነባት፣ ከነሱ ምጽዋት የማትወጣ ፍጹም ደሀ፣ ያለምንም ስጋት አካባቢውን በሞላ ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ሁኔታ የተመቻቸበት እንድትሆንላቸው ነበር፤ አሁን ግን ሰላም የሰፈነባት አገር እንደማትሆን ምልክቶችን እያዩ ነው፤ እንዲያውም በመሀከለኛው ምሥራቅ በግልጽም ይሁን በስውር እየበረታ የሚሄደው ጸረ-አሜሪካን ስሜት በአፍሪካ ቀንድ ላይ የተተከለ እንደሆነ ምዕራባውያን በመሀከለኛው ምሥራቅ ዘይት አምራች አገሮች ላይ ያላቸውን ጥቅም ሁሉ ክፉ ስጋት ላይ የሚጥልባቸው ሊሆን እንደሚችል የተገነዘቡ ይመስላል፤ በተጨማሪም ከኤርትራ ጋር በጠላትነት የተፋጠጠች ኢትዮጵያ ለምዕራባውያን የምትመች አለመሆንዋንም እየተገነዘቡ ነው፤ ስለዚህም ከኢትዮጵያ አገዛዝ ጋር በመሆን አሻክረውት የነበረውን ግንኙነት ለማለስለስ እየሞከሩ ነው፤ ይህ ሁሉም እየሆነ የኢትዮጵያ አገዛዝ ገና አልነቃም፤ በአፍሪካ ኅብረት በኩል ቀስቃሽ ተልኮለታል፡፡
በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ለወግም እንኳን መጥፋቱን የአፍሪካ ኅብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተገነዘበው ይመስላል፤ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ለዓመታት የማይቋጭ ሆኖ የቆየውን የእስላሞች ጉዳይ ለማየት ውሳኔ ላይ ደርሷል፤ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አለመኖሩን የአፍሪካ ኅብረት ውሳኔ ዋና ማረጋገጫ ነው፤ ዙሪያው ገደል መሆኑ የምዕራባውያን (አሜሪካና አውሮፓ) ኃይሎች ተማምነውበት የነበረውን የኢትዮጵያ አገዛዝ ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል፤ ዙሪያው ገደል መሆኑ የኢትዮጵያ አገዛዝ የሰላም አራማጅ መስሎ እንዳይታይ አድርጎታል፤ እንዲያውም የኢትዮጵያ አገዛዝ በአካባቢው ካሉት አገዛዞች ጋር የሻከረ ዓይነት ግንኙነት ስለሚያሳይ አሜሪካና አውሮፓ የሚወድዱት አይመስልም፤ ይህ ውጪውን ሲታይ ነው፡፡
ከውስጥ ሲመለከቱት ደግሞ ሌሎች የግጭት መድረኮችና ሌሎች ጉዳዮች ይታያሉ፤ ዋናውና መሠረታዊው ግጭት አገዛዙ በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉትን ነጻነቶችና መብቶች ሰርዞ ምንም ዓይነት ልዩነት በቃልም ይሁን በጽሑፍ መግለጽ እንደሽብርተኛነት የሚያስቆጥርና የሚያስወነጅል መሆኑ ነው፤ ፕሮፌሰር ስርግው ሐብለ ሥላሴ ዓጼ ምኒልክ፣ የአዲሱ ሥልጣኔ መሥራች በሚለው መጽሐፉ ኢትዮጵያውያን አእምሮ የሚባለውን ጋዜጣ መግዛት እንዲለምዱ በማለት አጼ ምኒልክ ጋዜጣውን ይዘው በአደባባይ እንደሚወጡ ይነግረናል፤ ዛሬ በአዳፍኔ አገዛዝ፣ መቶ ዓመታት ወደኋላ ሄደን ታዋቂ ጋዜጠኞች ሁሉ በእስር እየማቀቁ ጋዜጦች ሁሉ ጠፍተዋል፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተከልክለውና ታፍነው ባሉበት የወያኔ አገዛዝ፣ የፖሊቲካ ቡድኖች ተኮላሽተው አልጋ ላይ በዋሉበት ሁኔታ፣ ፖሊሶች፣ ዓቃቤ ሕጎች፣ ዳኞችና የወህኒ ቤት አዛዦች እንደፈለጉ በሚሠሩበት አገር ግጭቶች ያለማቋረጥ እንደሚፈጠሩ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ የፖሊቲካ ውይይት፣ ክርክርና ንግግር በተከለከለበትና አንድ ድምጽ ብቻ ለማዳመጥ በተፈቀደበት ሥርዓት ብዙ እምቢ-ባዮች ይኖራሉ፤ አዳፍኔ ጎራዴውን እየሳለ በሄደ ቁጥር ሰላማዊ የፖሊቲካ ውይይትም በተስፋ-ቢስነት አላስፈላጊ አማራጭ ውስጥ ይገባል፤መለስ ዜናዊ ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ›› ብሎ ተቀናቃኝ ቡድኖችን ከመረቀ ሃያ አምስት ዓመታት ተቆጠሩ፤ አሁን ምርቃቱ የደረሰ ይመስላል፤ ዛሬ ላይ ሆኖ ሲታሰብ መለስ ዜናዊ ራሱን የረገመ ይመስላል፡፡
ወሬው ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ አለመረጋጋት የሚያመለክት ነው፤ ከጎንደር አስከቦረና ከኦጋዴን አስከጋምቤላ ወሬው ሁሉ የግጭት ነው፤ አንድም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ፣ በውይይትና በስምምነት መደምደሚያ ሲያገኝ አይታይም፤ አይሰማም፤ ሁሉንም ነገር በጡንቻ በማስገደድ ለማስፈጸም የሚደረገው ሙከራ ያረጀና ያፈጀ መሆኑን ለማስታወቅ ተቀዋሚውም የጡንቻውን መንገድ እየተላመደው ነው፤ ጡንቻ ለጡንቻ መቆራቆዙ ደም እያፋሰሰ ጡንቻን ያነግሣል እንጂ ሕዝብን አይገነባም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የጡንቻ ግጭት መስፋፋት በሰሜን በኤርትራና በትግራይ፣በትግራይና በጎንደር፣ በትግራይና በወሎ፣ በምሥራቅ በሱማሌና በኦሮሞ፣ በሱማሌና በሐረሬ፣ በኦሮሞና በሐረሬ ፣ በደቡብና በምዕራብ በተለያዩ ጎሣዎች መሀከል የተጫረው እሳት ሲቀጣጠል ማብረዱ እንደማቀጣጠሉ ቀላል አይሆንም፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ እንደሚባለው ይሆናል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ የሚቀጣጠለው እሳት ድንበር ጥሶ የሚወጣና ጦሱ የማይበርድ ይሆናል፤ወያኔም ሆነ ለወያኔ ወንበር ያሰፈሰፉ ሁሉ፣ በጎሠኛነት ስሜት እየነደዱ የማመዛዘን ችሎታቸውን ያጡ ሁሉ የሰነዘሩት የጥላቻ ስለት በነሱው ላይም ሲያርፍ የተመኙትን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ እንደሚያጋጥማቸው ከመሸ በኋላ ይረዱታል፤ ለሌሎቹ አዲስ ይሆናል እንጂ ለወያኔ ከመሸ በኋላ መረዳት የባሕርይ ነው!
ከሶርያ በሶማልያና በኬንያ በኩል እያደፈጠ የሚገሰግሰው የሽብር ቡድን ወደኢትዮጵያ አይደርስም ማለቱ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እንደተለመደው ለከመሸ በኋላ ማሰብ ማስተላለፉ የመጨረሻው ስሕተት ሊሆን ይችላል፤ የመጨረሻው ስሕተት የተሠራውን አሰፋልት መንገድ አፍርሶ የባቡር ሀዲድ እንደመሥራት አይቀልም፤ የውጮቹን አካባቢ ኃይሎች እንደውስጡ አመራር በጡንቻ (የአሜሪካን ድጋፍ ቢኖርበትም) ለማስተናገድ ማሰብ ማሰብ አይደለም፤ ማሰብ የጎደለው መሆኑም በገሃድ እየታየ ነው፤ በኢትዮጵያ ዙሪያ ያሉ አገሮች በሚከተለው ሰንጠረጅ ተዘርዝረዋል፡፡
ወደአሥራ አንድ የሚጠጉ ጎረቤቶች እንኳን ለአላዋቂዎች አምባገነኖችና ለአዋቂ መሪዎችም ቢሆን በጣም ፈታኝ ነው፤ የኢትዮጵያ አገዛዝ አሜሪካንን ከመጠን በላይ በመተማመን የውጩን አመራር ልክ እንደውስጡ በጉልበትና በማታለል ላይ የተመሠረተ አድርጎታል፤ ይህ ሁኔታ ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል አድርጎታል፤ በዚህም ምክንያት እንዳይደርስ ከተባለበት ከጂቡቲ በቀር ከኢትዮጵያ ጋር በግጭት ያልተላከፈ አገር የለም፤ የኃያል አሽከር መሆን ኃያል የሆኑ የሚያስመስል ሕመም አለ፤ ጃንሆይ አማኑኤል ሆስፒታልን ሲጎበኙ አንዱን ያገኙትና ስሙን ይጠይቁትና ይነግራቸዋል፤ ቀጥሎም በተራው ያንተስ ስም ይላቸዋል፤ የኛማ ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነው ብለው ሲመልሱለት ከት ብሎ ይስቅና እኔንም ሲጀምረኝ እንዲህ ነበር ያደረገኝ ይላቸዋል! መማር የፈለገ አምባገነን እብድ ከተባለ ሰውም መማር ይችላል! አሜሪካኖች የኢትዮጵያን አገዛዝ የአካባቢው ሰላም ጠባቂነት በጥርጣሬ እንዲመለከቱት ያደረጋቸው ይኸው ሳይሆን አይቀርም፤ አንዱና ዋናው የማሰብ ችግር ነው፡፡
ኢትዮጵያና ጎረቤቶችዋ
2008 ዓ.ም.
ተ፣ቁ. አገሮች የኢትዮጵያ ጦር ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት የውስጥ ሰላም
1 ኢትዮጵያ የለም
2 ሱዳን1 አለ አለ የለም
3 ሱዳን2 አለ የለም
4 ሱዳን3? ?
5 ኬንያ ? አለ አለ
6 ሰማልያ አለ የለም
7 • ስባሪ1 የለም
8 • ስባሪ2 የለም
9 • ስባሪ3 የለም
10 ጂቡቲ አለ
11 ኤርትራ አለ አለ
ምናልባት ከባሕር ማዶ ያለው ጎረቤታችን፣ የመን በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ የተለየ መዘዝ ይዞላቸው ይመጣ ይሆናል፡፡
አሁን ደግሞ ከሁሉም የባሰው መጋለጥ መጣ፤ ማንም በማይደርስበት ፍጥነት እያደገ ነው የተባለው ኢኮኖሚ አከርካሪቱን ተመታ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በችጋር ጥቃት ስር ወደቀ፤ የወያኔ የኢኮኖሚ እድገትም ሆነ የአገሩን ሕዝብ ያቀጨጨው የወያኔ ጡንቻ ውሀ ሆኑ፤ ኢኮኖሚ በጡንቻ አያድግም፤ ችጋር በጡንቻ አይገፋም፤ ሕጸናትንና አሮጊትና ሽማግሌዎችን የገጠር ነዋሪዎች እያመነመነ በመጣል የሚጀምረው ችጋር አይደበቅም፤ ከወራት በኋላ ማምለጥ ያልቻሉትን ሁሉ ችጋር እየበላ በያለበት ሲጥላቸው በዓለም ጋዜጦች ይወጣል፤ ያኔ መዋሸትና ማታለል ዋጋ ያጣሉ! ያኔ ጡንቻ ዋጋ ያጣል! ያኔ ስለእድገት ማቅራራት ዋጋ ያጣል!
ዓላማው ሁሉ ታወቀ፤ ዘዴው ሁሉ ታወቀ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓላማውም ዘዴውም ሰለቸው፤ ምዕራባውያን ኃይሎች ውሸትን መጠገን ሰለቻቸው፤ የአፍሪካ ሕዝቦች የጎሠኛነት በሽታ እንዳይተላለፍባቸው ፈሩ፡፡