ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው የድንበር ሊካለል ነው ተባለ።
በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ የድንበር ማካለሉ ስራ ሙሉ በሙሉ እንደሚከናወን ባለፈው አመት መጨረሻ አለያም በዚህ አመት መጀመሪያ አካባቢ ተካሂዶ በነበረው የአልበሽር በአለ ሲመት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለሱዳን ባለስልጣናት ማረጋገጫ ሰጥተው እንደተመለሱ በጊዜው በደረሰን መረጃ መሠረት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ አሳውቀን ነበር ። አሁን ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ የድንበር ማካለሉ ስራ በሚቀጥለው ወር ውስጥ እንደሚከናወን ገልፆ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የሱዳኑ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ መግባታቸውን ገልጿል። ከኤርትራ እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ድረስ 1600 ኪሎ ሜት ርዝመት ባለውና ወደ ኢትዮጵያ ከ40 ኪሎ ሜትር በላይ ዘልቆ ወደ ውስጥ የሚገባው የሱዳን የድንበር ይገባኛል ጥያቄ አብዛኛውን የሀገሪቱን ለም መሬት በስፋት ለሱዳን የሚሰጠውና ከዚህ ወር መጠናቀቅ በሗላ የሚተገበረው ስምምነት ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅናና ይሁንታ ውጪ በህውሃት/ኢሕአዴግ ጁንታ ባለስልጠናት ውሳኔ የሚተገበር ነው። ይህ የድንበር ማካለል በትግበራ ላይ ከዋለ በህውሃት የአገዛዝ ዘመን ከተፈፀሙና ታሪክ ከማይዘነጋቸው በርካታ ስህተቶች መካከል አሰብ ለኤርትራ ከተሰጠበት መራር እውነት ቀጥሎ በጥቁር ቀለም የቀለመ ሁለተኛው ግዙፍ ስህተት ሆኖ ይመዘገባል፡፡
No comments:
Post a Comment