የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

በሰራዊቱ ውስጥ የታየው መነቃቃት ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲፋጠን፣ በተለይም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ተቀራርቦ የመስራት ድርድር እንዲፋጠን እንደሚያደርገው ሳለቃ አክሊሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል።የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ መድረስ ዜና ይፋ ከሆነ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ህዝብ እየጨመረ መምጣቱንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕ/ር ብርሃኑ ግንቦት7ትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተው ፣ አርበኞች ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ የውህዱ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነዋል። በውህደቱ ላይ ለመገኘት የነበራቸው ውጥን ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ፣ ለመሪነት የተመረጡት በሌሉበት ነው። ይሁን እንጅ በውህደቱ ወቅት ለጉባኤተኛው በስልክ ባስተላለፉት መልክት፣ አንዳንድ ችግሮች ተፈተው በቅርቡ በረሃ ወርደው እንደሚቀላቀሉዋቸው ቃል ገብተው ነበር።
በምርጫ 97 በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከሁለት አመት ላለነሰ ጊዜ በእስር ቤት አሳልፈዋል። ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው በክኔል ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው ከወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።
No comments:
Post a Comment