Thursday, 16 July 2015

ስዊድን፥ ጠቅላይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ መልስ ሆስፒታል ገቡ

ስዊድን፥ ጠቅላይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ መልስ ሆስፒታል ገቡ
የስዊድኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ሽቴፋን ሎፍቨን ከኢትዮጵያ ወደ ስዊድን በመብረር ላይ ሳሉ ስለታመሙ ሀገራቸው ሲደርሱ ሐኪም ቤት መግባታቸውን የሚንሥትሩ ቃል አቀባይ አኔ ኤክበርግ ገለጡ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ አውሮፕላናቸው የስቶክሆልም አየር ማረፊያን እንደነካ በአምቡላንስ በፍጥነት ወደ ሐኪም ቤት መወሰዳቸው ተዘግቧል። አዲስ አበባ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የልማት ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የስዊድኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ወደ ስዊድን ሲበሩ «ብርቱ ማቅለሽለሽ» እንደገጠማቸውም ተጠቅሷል። የጠቅላይ ሚንሥትሩ ቃል አቀባያዋ አኔ ኤክበርግ፣ ሚንስትሩ «የተወሰኑ ምርመራዎች ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ» ሲሉ ለፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ስለጠቅላይ ሚንሥትሩ ኅመም ግን ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የ57 ዓመቱ የሶሻል ዴሞክራት ፖለቲከኛ ከዘጠኝ ወራት በፊት አንስቶ የስዊድን ጠቅላይ ሚንሥትር ናቸው።

1 comment:

  1. Thanks for making the honest attempt to publish regarding this. It might be extremely helpful for me as well as my friends.
    ranjang pasien

    ReplyDelete