የወያኔ ቡድን ለህዝብ ደንታ እንደሌለው በተለያዩ አጋጣሚዎች እያሳየ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ስደትን በይፋ የጀመረው ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም፤ የሴቶች መብት ይከበር፤ ዲሞክራሲ ያለገደብ፤ እና የተለያዩ የእኩልነት እና የነጻነት ጥያቄ በማንሳታቸው በፖለቲካ አስተሳሰባቸው እና ያለውን መንግስት በመቃወማቸው የደርግ ስርአት ያደርግ የበነበረውን አሰቃቂ ግርፋት ግድያ በአጠቃላይ ስርዓቱ የፈጠረውን አፈናና እና ግፍ ሽሽት እንደሆነ ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ በአይነቱም ሆና በብዛቱ ተባብሶ ይገኛል። ህዝባችን ሃገሩ ያለውን ችግር ቢሸሽም ሸሽቶ የሚሄድባቸው ሃገራት ያለውን ሃገር አጥፊ ስርዓት ደጋፊ በመሆናቸው እንደዚሁም የተለያዩ ሃገራት መፈራረስ እና የተለያዩ አሸባሪ ቡድኖች በየቦታው መፈልፈል ከሃገራቸው በስርዓቱ በደል የተሰደደው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሄደበት መንገድም ሆነ በደረሰበት ሃገር ሁሉ እየተገፋ እና እየተሰቃየ መራራ እና አስከፊ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።
ህዝባችን በተለያዩ ሃገራት ለምሳሌ በየመን የተለያየ ግፍ እና መከራ ሲያሳልፍ መቆየቱ የሚታወስ ነው።በአሁኑ ሰአት ደግሞ የisis ወደ የመን መግባት አስጨንቆት የይድረሱልን ጥሪ እያሰማ ይገኛል።በደቡብ አፍሪካ ያለውም ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እንዳልተረጋጋ እዛው ያሉ ወገኖች ይናገራሉ። በሊቢያም ሌሎች ዜጎቻችን በቅርቡ ያሳለፉትን አሰቃቂ ድርጊት እንዳይደግሙ የብዙዎቻችን ስጋት ነው። በአረብ ሃገራትም የሚኖሩ እህቶቻችን እየደረሰባቸው ያለውን መቋቋም እያቃታቸው እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች እየጨመሩ ናቸው።በአውሮፓም ቢሆን የሚደርስብን እንግልት ቀላል የሚባል አይደለም።ባለውለታቸው ነን ብንቸገር ይደርሱልናል ብለን የምናስባቸው ሃገራት ጭራሽ የችግራችን አባባሽ ሆነው ተገኝተዋል ሲሰደዱ የተቀበልናቸው በችግራቸው የደረስንላቸው ውለታችን ከምንም እንደማይቆጥሩት በተግባር አሳይተውናል።
እዚህ ላይ የሚገርመው ከየአቅጣጫው ህዝባችን ለሚደርስበት ችግር የድረሱልኝ ጥሪ የሚያሰማው በተቃዋሚ ሚዲያዎች እንደነ ኢሳት እና ፍኖተ ሬድዮ ላይ መሆኑ ነው። ይህ የሚያሳየው ህዝባችን ባለው ስርአት ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጠ ነው።ህዝባችን መንግስት አልባ ነው የሚለውንም ማረጋገጫ ነው።
በመንግስት ስም የተቀመጠው የወያኔ ቡድን ለህዝብ ደንታ እንደሌለው በተለያዩ አጋጣሚዎች እያሳየ ይገኛል። እንኳንስ ለወገን ሊቆረቆር በሃገር ውስጥ በውጭ ሃገራት የሚደርስብንን በደል ለመቃወም የሚወጡትን የወገን ተቆርቋሪዎች በመደብደብ እና በማሰር ከህዝብ ጎን ከመሰለፍ ይልቅ ህዝብን ከሚያንገላቱት ጎን መቆሙን አሳይቶናል።በሳኡዲ የተቃወሙት ላይ ያደረሰውን ድብደባ ሳንረሳ በሊቢያ isisን ለመቃወም በወጡት ላይ ደግሞታል ይባስ ብሎ ለህዝብ መቆርቆር እና ለወገን ማልቀስን እንደአሸባሪነት ቆጥሮ እየደነፋ ይገኛል።የተለያዩ ሃገራት ከየመን ዜጎቻቸውን በቻሉት ሁሉ እያወጡ ወገንተኛነታቸውን እያሳዩ ባለበት ሰአት ወያኔ የመረጠው በቃላቀባዩ የፌስቡክ ለበጣን ሆኖ ተገኝቷል።ዳሩከዝንብ መቼስ ማር ይጠበቅ እና
ታዲያ የሚያሳዝነው ህዝባችን ይህን ሁሉ መስዋእትነት የሚከፍለው በአምባገነኖች በጠባቦች በባንዳዎች በሆድ አደሮች በንዋይ ናፋቂዎች እና በባእዳኖች መሆኑ ነው። እንደነዚህ አይነት ጥርቅሞች ደግሞ ለወገን ይቆረቆራል ወይም ለሃገር ያስባል ማለት ቀሚሰ ተስፋ ነው።ባእዳኖቹም ቢሆኑ የራሳቸውን ጥቅምትተው ለሃገራችን ያስባሉ ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።
እንደማንኛውም የህብረተሰብ ጥርቅም እንደነዚህ አይነቶች በሃገራችን ቢኖሩም እራሳቸውን ለሃገራቸው ያሳለፉ እድሜያቸውንም በትግልእየጨረሱ ያሉ እንዳሉ ማወቁ ተገቢ ነው። በአሁኑ ሰአት እንደሚታየውም ከሆዳሞቹ ከባንዳዎቹ ከጠባቦቹ ቁጥር ይልቅ የሃገር ተቆርቋሪው የአንድነት ሃይሉ ሚዛን እየደፋ መጥቷል። ወያኔም እርቃኑን መቅረቱም በቅርቡ ያየነው እውነታ ነው። በመሆኑም የተጀመረው የህዝብ ትግል ከዳር ይደርስ ዘንድ በየቦታውየሚሰቃየው የህዝባችን ሰቆቃ ይቆም ዘንድ የራሳችን የሆነ የሚቆረቆርልን በህዝብ የተመረጠ መንግስት ይኖረን ዘንድ ከእስከዛሬው በበለጠ ተደራጅተን እና አንድ ሆነን ትግላችንን በማጠናከር ይህን ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳው የወያኔ ቡድንን እስከመጨረሻው እናስወግደው።
ህዝብ ያሸንፋል!!!!!!!!!!!!
No comments:
Post a Comment