Tuesday, 30 September 2014

ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።
ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት በመኮብለል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የሚቀላቀሉ አባላት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት መካከል የአየር ኃይል ባልደረባ ይገኝበታል።
በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለውን የአንድ ቡድን የበላይነትን እና ሠራዊቱ የሀገርና ሕዝብ አገልጋይ መሆኑ ቀርቶ የወያኔ ቅጥረኛነትን በመቃወም በተለያዩ የሠራዊቱ ክፍል ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በተለያዩ ጊዜያት መቀላቀላቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን የደብረዘይት አየር ኃይል ባልደረባ ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ የተባለ የተዋጊ ጦር ሄሊኮፕተር አብራሪ የሀገራችን ኢትዮጵያን የግፍና የመከራ ጊዜን ለማብቃት እየተደረገ ያለውን ትግል ለመደገፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅሏል።ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ ለአርበኞች ድምጽ ሬዲዮ እንደገለጸው ከሆነ "የአየር ኃይሉ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በሕ.ወ.ሓ.ት ሰዎች የተያዘ ሲሆን እንኳንስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሊያስከብር ቀርቶ እንደተቋም በሁለት እግሩ መቆም ተስኖት በውጪ ቅጥረኞች ትከሻ ላይ የተመሰረተ" መሆኑን ገልጿል።
የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝን በትጥቅ ትግል ለመፋለም በተለያዩ ጊዜያት የወያኔ አየር ኃይል አባላት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን የተቀላቀሉ ሲሆን ከወራት በፊት ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሺዋስ የተባለ የተዋጊ ጦር ጀት አብራሪ ግንባሩን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው።
ሰሞኑን ግንባሩን ስለተቀላቀለው የአየር ኃይል ባልደረባ ምክትል መቶ አለቃ ጣይብ ቃዲ ሰፊ ዘገባ ይዘን እንደምንመለስ ከወዲሁ እናስታውቃለን።
ሰበር ዜና !!
መምህራንን ከስራ ቦታችው ማፍናቅል ትጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ከሰሞኑ በተካሄደው ስልጠና እናተያያዥ ጉዳዮች ከመምህራን ጋር መስማማት ያልቻልው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎቸ በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ የተለያዩ ወጣት መምህራንን ስልጠናው በተሳካ ምክንያት እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቸ ውስጥ ድብቅ አጀንዳ ይዛቹህ ስትንቅሳቅሱ ተገኝታቹሀል በሚል ምክንያት የተነሳ ህወሀት መራሹ መንግስት የሚከተሉትን መምህራን ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ያለፍላጎታችው ተነስተው ወደ ገጠራማ ስፍራዎች እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባገኘው መረጃ መሰረት በግዴታ ዝውውር የተሰጣቸው መምህራን የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. መ/ር ይማም ሐሰ
2. መ/ር ሙለታ ዲንቃ
3. መ/ር ኤርሚያስ ተገኝ
4. መ/ር ሐይለ አምላክ ይገዙ
5. መ/ር ደምስ ግዛቸው
6. መ/ር አንዳርጋቸው ምህረቴ
7. መ/ር አንተነህ ንጉሱ
8. መ/ር ይስሀቅ ጉደታ
9. መ/ር መላኩ አበበ
10. መ/ር ዮሐንስ ካሳሁን
11. መ/ር ዳዊት የሺጥላ
12. መ/ር ዘሪሁን አላምረው ሲሆኑ ከትላንትናው እለት ማለትም 19/01/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ያለፍቃዳቸው መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በተመሳሳይ መንገድ በርካታ መምህራን ከስራ የመባረር እና ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መመደባቸው ይታወሳል

Thursday, 25 September 2014

ጄ/ል አበባው ታደሰ መከላከያን ለቀቁ

ጄ/ል አበባው ታደሰ መከላከያን ለቀቁ
መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-98 በመቶ የሚሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል ሰአረ መኮንን ጋር በመነጋገር ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በመከላከያ ውስጥ የሚታየውን ሙስና አልተቆጣጠሩም በሚል ሊገመግሙዋቸው ነበር የሚል ሪፖርት ቀርቦባቸው ከሃላፊነት ዝቅ እንዲሉ መደረጉን ኢሳት ከ9 ወራት በፊት ” የመተካካቱ ተውኔት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ” በሚል ርእስ ባቀረበው የምርመራ ዘገባ ገልጿል። በጊዜው እንደተዘገበው ጄ/ል ሳሞራ የኑስን የሚተካው ኢታማዦር ሹም ከህወሃት እጅ እንዳይወጣ ለማድረግ ተፎካካሪ ሆነው ይቀርባሉ ተብሎ የተገመቱትን ጄ/ል አበባውን ጠልፎ ለመጣል ሁለቱ ጄኔራሎች የቤት ስራውን ወስደው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፤ ጄ/ል አበባው ግሳጼ ደርሶባቸው ከሃላፊነት እንዲለቁ ሲደርግ የህወሃቶቹ ጄ/ል ሰአረ መኮንንና ጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው ከፍተኛ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። በአንጻሩ ጄ/ል አበባው ከሃላፊነት ተቀንሰው ያለፉትን 9 ወራት ንብረቶቻቸውን በመሸጥ ውጭ የሚወጡበትን አጋጣሚ ሲያፈላልጉ ከርመዋል።
ጄ/ል አበባው በባህርዳር ከተማ የሚገኘውን አልዋቅ ሆቴልና ሌሎች ድርጅቶቻቸውን ለሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ከሸጡ በሁዋላ ከአገር ለመውጣት ቢያስቡም መከልከላቸውንና የቁም እስረኛ መሆናቸውን ምንጮች ገልጻል።
የጄ/ል አበባው የቁም እስረኛ መሆን በብአዴንና በህወሃት የመከላከያ የሰራዊት አባላት መካከል ያለውን ሽኩቻ ሊያባብሰው ይችላል የሚሉት ምንጮች፣ አንዳንድ ምልክቶች መታየታቸውን ተከትሎ በመካከለኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ የአማራተወላጅ መኮንኖች ለይ ጥበቃ እና ክትትሉ ጨምሯል። የብአዴን አባል የሆኑ መኮንኖች በሰራዊቱ ውስጥ የሚታየውን የህወሃት ፍጹም የባላይነት በተደጋጋሚ ይቃወማሉ።